የዒድ አከባበር ደንቦች... ስህተቶች እና የተክቢራ አፈጻጸም Etiquette of Eid ... آداب وسنن العيد

61 views
Skip to first unread message

Abujunaid Salah Ahmed

unread,
Jul 27, 2014, 6:50:29 AM7/27/14
to Nesiha الديــن النصيــــحة
On 4 Aug 2013 03:11, "Ibnu Mas'oud Islamic Center" <nesih...@gmail.com> wrote:


Inline image 1

Etiquette of Eid ...   (scroll down)  

آداب يوم العيد... إقرأ أسفل الصفحة 

የዒድ አከባበር ደንቦች

በጣሀ አህመድ

    በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው

   ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው፡፡ የአላህ ሰላትና ሰላም በመልእክተኛው ሙሀመድ፤ በቤተሰቦቻቸው እና በባልደረቦቻቸው ላይ ይሁን፡፡

ዒድ ጁምዓ(ዓርብ) ዕለት ከዋለ

የሳዉዲ ዓረብያ ቋሚ የፈትዋ ኮሚቴ በቁጥር  21160 ካወጣው መግለጫ ተከታዮቹን ሀሳቦች ጠቅሷል።

 

·        ኢማሙ ሰላተል ጁምዓ እንዲሰገድ የማድረግ ግዴታ አለበት። ጁምዓ ለመስገድ በቂ ሰዉ ካልተገኘ ዙህርን ያሰግዳል።

·        ሰላተል ዒድ የሰገደ ሰው የጁምዓ ሰላትን ባይገኝ ይፈቀድለታል። ዙህርን በወቅቱ ይሰግዳል። ሆኖም ግን ከሙስሊም ወንድሞቹ ጋር ጁምዓን ቢሰግድ የተሻለ ነው።

·        የዒድን ሰላት ያልሰገደ ግን ይህ ፍቃድ አይመለከተዉም። ጁምዓን የመስገድ ግዴታ አለበት።

·        በዚህ እለት ጁምዓ በሚሰገድባቸዉ መስጂዶች ሲቀር የዙህር አዛን አይደረግም።

ዒድ ማለት ምን ማለት ነው?

ኢብኑል ዓረቢዕ ‹‹ዒድ›› (ዒድ) ብሎ ስለመሰየሙ ሲናገሩ በየአመቱ አዲስ ደስታን ይዞ የሚመለስ ከመሆኑ አንፃር መሆኑን እና ‹‹ዓደ›› (ተመለሰ) ከሚለው ቃል የተወሰደ መሆኑን ይገልፃሉ፡፡ እዚህ ላይ ልብ ልንልን የሚገባው (ዒድ) ቂያማ እስቂቆም ተመላልሶ የሚመጣ ቢሆንም እኛ ግን የሚቀጥለውን ለመድረስ ምንም ዋስትና እንደሌለን ነው፡፡ ስለሆነም ከአላህ ህግ ፈፅሞ ልንወጣ አይገባም፡፡

 

عَنْ أَنَسٍ-رضي الله عنه- قَالَ: قَدِمَ رَسُولُ اللَّهِ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ- الْمَدِينَةَ، وَلَهُمْ يَوْمَانِ يَلْعَبُونَ فِيهِمَا فَقَالَ:(مَا هَذَانِ الْيَوْمَانِ؟) قَالُوا: كُنَّا نَلْعَبُ فِيهِمَا فِي الْجَاهِلِيَّةِ، فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ -صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ-: (إِنَّ اللَّهَ قَدْ أَبْدَلَكُمْ بِهِمَا خَيْرًا مِنْهُمَا يَوْمَ الْأَضْحَى وَيَوْمَ الْفِطْرِ) رواه أبو داود

 

  አነስ ኢብኑ ማሊክ እንዲህ ይላሉ ‹‹የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) መዲና ከተማ ሲመጡ የመዲና ሰዎች በመሀይምነት ዘመን (ደስታቸውን የሚገልፁባቸው) የሚጫወቱባቸው ሁለት ክብረበዓላት ነበሩዋቸው። ይህንን ባዩ ጊዜ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ አሉ፡፡ በእነዚህ በሁለቱ ምትክ  ከእነርሱ በተሸሉ  ሁለት  ክብረበዓላትን ቀየረላችሁ፤ እነሱም የፈጥር እና የአድሀ በዓላት ናቸው፡፡››  

(አቡዳውድ እና አህመድ እንደዘገቡት)

ከዚህ ሀዲስ ጋር በተያያዘ ኡለማዎች የተረዷቸዉን ሁለት ቁም ነገር ልናስተውል ይገባል።

አንደኛ ፡- ከሌሎች (ከእስልምና ውጭ) ካሉ ማህበረሰቦች ጋር መመሳሰል የተከለከለ መሆኑ እና፣

ሁለተኛ ፡- በኢስላም የተደነገጉ ክብረ በአላት ሁለት ብቻ መሆናቸውን ነው ፡፡

ከዒድ ዋዜማ ጀምሮ ልንፈፅማቸው የሚገቡ ነገሮች

   ከዚህ በላይ በአጭሩ ዒድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እንዲሁም በኢስላም የተደነገጉ ክብረ በአላት ኢድ-አልፈጥር እና ኢድ-አልአድሀ ብቻ መሆናቸውን ከተረዳን፤ በእነዚህ ሁለት ዒዶች ዋዜማ እና በእለቱ ምን ማድረግ ይወደዳል? ምንስ ይፈቀዳል? ምን ከማድረግ ልንከለከል ይገባል? ወደ ሚሉት ነጥቦች እንምጣ፡፡

በመጀመሪያ ከዒድ ዋዜማ ጀምሮ ልንፈፅማቸው ከሚያስፈልጉ ነገሮች ስንነሳ፤

1.       በኢደል-ፊጥር ዒድ መሆኑ ከተረጋገጠበት ሰዐት አንስቶ ሰላቱ እስኪጀመር በኢደል-አድሀ ደግሞ ከዙል ሂጃ የዘጠነኛው እለት ፈጅር ሰላት አንስቶ የአስራ ሶስተኛው እለት ፀሀይ እስከምትጠልቅ ድረስ ተክቢራን ማድረግ ይገባል፡፡

2.       መታጠብ እራስን ማሰማመር እና ከልብሶች መካከል የተሸለውን እና ቆንጆውን መልበስ  ከሰለፎች የተዘገበ ተግባር ነው፡፡

3.       ሴቶችን በተመለከተ በዚህ እለትም ይሁን በሌላ ጊዜ ከቤታቸው እንዴት መውጣት እንዳባቸው በሸሪዐ የታወቀ ነው፡፡ እናም ከመገላለጥ እና ሽታ ያላቸውን ነገሮች ተጠቅመው ከመውጣት ተቆጥበዉ ከቤታቸው ወደ መስጊድ ወይም ወደ ዒድ መስገጃ ስፍራ ሊሄዱ ይገባል፡፡

የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ለጋብቻ የቀረቡና የደረሱ እንዲሁም በወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶችን ጨምሮ ወደ ዒድ ሰላት መስገጃ ቦታ ስፍራ እንዲወጡ ትዕዛዝ ማስተላለፋቸውን ተከትሎ እንዲህ የሚል ጥያቄ ተጠይቀው ነበር ‹‹አንዳችን ጅልባብ ባይኖራት ምን ታድርግ?›› እሳቸውም እንዲህ አሉ ‹‹እህቷ (ጓደኛዋን) ታውሳት››                       

(ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)

 

عَنْ زَيْدِ بْنِ خَالِدٍ الْجُهَنِيِّ،  قَالَ : قَالَ  رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : "  لا تَمْنَعُوا إِمَاءَ اللَّهِ مَسَاجِدَ اللَّهِ ، وَلْيَخْرُجْنَ تَفِلاتٍ " رواه أحمد وأبو داود وصححه الألباني

በሌላውም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል ‹‹ሴቶችን መስጊድ ከመሄድ አትከልክሏቸው ነገር ግን ከቤታቸው ሽታ ያለው ነገርን ተጠቅመው እንዳይወጡ፡፡››    

           (አል-ኢማም አህመድና አቡዳውድ ሲዘግቡት አልባኒ ሰሂህ ብለውታል)

4.       በዒደል ፊጥር ሰጋጁ ወደ መስገጃው ከመውጣቱ በፊት ዊትር (አንድ፤ ሶስት፤ አምስት …..) ቁጥር ያላቸውን ተምሮች በልቶ መውጣት

5.       ለኢድ ሰላት ከመውጣት በፊት ዘካተል-ፊጥርን ለተገቢው ወገን መስጠት

6.       ሰላተል ኢድን ለመስገድ ከፍተኛ ፍላጎትና ጉጉት ሊኖር ይገባል፡፡ ምክንያቱም ይህ ተግባር ከታላላቅ የኢስላም መገለጫዎች አንዱ ከመሆኑም ባሻገር የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በእሳቸው ላይ ይሁንና) ሰላተል ዒድ ከተደነገገበት ጊዜ አንስቶ እስከ ሕልፈታቸው ትተውት አያውቁም በተጨማሪም በመሰረቱ መስገድን የተከለከሉትን የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች ሳይቀር በቦታው ላይ እንዲገኙ አዋዘል፡፡

7.       ሰላቱ ከተጠናቀቀ በኋላ በተቻለ አቅም ኹጥባን ማዳመጥ

8.       ወደ ዒድ ሰላት ከሄዱበት መንገድ በሌላ መመለስ

9.       የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት መለዋወጥ፡፡ ይህም ‹‹ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም›› የሚል ሲሆን የተለያዩ የኢስላም ሊቃውንት ከሰሃቦች መገኘቱን አረጋግጠዋል፡፡

10.    ከኢድ ጋር በተያያዘ ዘካተል ፊጥርን መስጠት መታዘዙ የተለያዩ ችግረኞችን ማስታወስ እና አቅም በፈቀደ መጠን ችግራቸውን ለመቅረፍ ጥረት ማድረ የሚደገፍ ተግባር መሆኑን የሚያመለክት ነው፡፡

11.   በአጠቃላይ ሸሪዐው ያዘዘባቸውን እና የፈቀዳቸውን ተግባራት በፈፀም የሚፈቀድና የሚወደድ ይሆናል

የተክቢራ አፈፃፀም

1.  ከመልክተኛው ትክክለኛ ሰነድን መሰረት ያደረገ እና የተክቢራን አባባል ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ መረጃ ባይገኝም ከሰሀቦቻቸው ግን ‹‹አላሁ አክበር አላሁ አክበር ወሊላሂልሀምድ›› እና የመሳሰሉት አባባሎች በትክክለኛ ሰለድ ተዘግበዋል፡፡ ስለሆነም ሙስሊሞች እነዚህን አባባሎች የትኞቹ እንደሆኑ ማጥናትና እነርሱን ማዘውተር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ኢብኑ ሀጀር አል-አስቀላኒ ፈትሁል ባሪ በተሰኘው ኪታባቸው እንዲህ ይላሉ ‹‹በዚህ ዘመን (ተክራን በተመለከተ) ብዙ መሰረት የሌላቸው ጭማሪዋች ተከስተዋል፡፡›› ይህ በሂጅራ አቆጣጠር ከ773-852 የኖሩት የኢስላም ሊቅ ንግግር ነው። ታዲያ ባለንበት ዘመን ምን ያህል ጭማሪ ተከስቶ ሊሆን እንሚችል ስናስተውል በጉዳዩ ላይ ከባድ ጥንቃቄ ልናደርግ እንደሚገባ ያመላክተናል፡፡

2.  በአንድ ድምፅ ወይም አንድን ሰው የአዝማች አውጪ ሌላውን ተቀባይ ሆኖ የሚደረግ ተክቢራም ሱናን የሚቃረን ተግባር ነው። በዚህ ዙሪያ እንደ መረጃ የሚጠቀሰው የዑመር ተግባር የሚያመለክተው ሚና ላይ በድንኳን ውስጥ ሆኖ ድምፁን ከፍ አድርጎ ተክቢራ ሲያደርግ ሰዎችም ተክቢውን ሰምተው ተክቢራን ማድረግ እንዳለባቸው በማስታወስ እነርሱም ተክቢራ ያደርጉ እንደነበረ እንጂ ሌላ አይደለም። የህ ክስተት፤ በጋራ ድምፅ እርሱን እንደ አዝማች እነርሱ እንደ ተቀባይ ሆነው ይቀጥሉ ነበር የሚለው እንድምታ አያስጨብጥም ሲሉ ኡለማዎች ይናገራሉ፡፡

 

ጥቂት ከዒድ ጋር በተያዘ የሚፈፀሙ ስህተቶች

1. ዒድ መሆኑ ከታወቀበት ሰአት ጀምሮ ወንዶች ከሰላተል ጀመዓ መቅረት ብሎም በረመዳን ሲሰግዱት የነበረውን ዊትር ሰላት መተው፤ አንዳንዴም አምልኮዎች በዚህ ያበቃሉ የተባለ ይመስል እርግፍ አድርጎ መተው፡፡

2. የኢዱን ዋዜማ ሌሊት በተለያዩ ዒባዳዎች ህያው ማድረግን በተመለከተ የመጡት ሀዲሶች ከሰነድ አንፃር ደካማዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ሊሊቱን በተለያዩ ነገሮች ማሳለፍ፤ በዚህም የተነሳ የፈጅር ሰላትን አለመስገድ እና ሰላተል ኢድን እንደ ቀላል በመመልከት ችላ ብሎ መተው፡፡ «ሰላተል ኢድ በእያንዳንዱ ግለሰብ ላይ በነፍስ ወከፍ ግዴታ ነው» የሚለው የአቡ ሀኒፋ እና የኢማሙ ሻፊዒይ አቋም ነው። ከኢማሙ አህመድ ከተዘገቡት ሁለት የተለያዩ ሀሳቦች አንዱ የሚጠቁመው ይህንኑ አቋም ነው። ሸይሁል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ እና በዙ ኡለማዎችም ይህ አቋማቸው መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

3. በአለባበስና መቆነጃጀት ዙሪያ ከሚከሰቱ ስህተቶች መካከል በአብዛኛው ወንዶች ፂማቸውን በመላጨትና በማሳጠር እንዲሁም ልብሳቸውን ከቁርጭምጭሚታቸው በታች እነዲወርድ በማድረግ የሚፈፅሙት ስህተት ይገኝበታ። ሴቶች ደግሞ ሽቶን በመቀባት በመገላለጥ የሚፈፅሙት ስህተትም አደገኛ ነው፡፡ እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የመጡት ነብያዊ አስተምህሮቶች እጅግ አስፈሪና አስደንጋጭ ናቸው፡፡

 

عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ عَنْ النَّبِيِّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ( مَا أَسْفَلَ مِنْ الْكَعْبَيْنِ مِنْ الْإِزَارِ فَفِي النَّارِ) رواه البخاري (5787)

ከአቡሁረይራ በተላለፈ ሀዲስ የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል ‹‹ከሽርጥ ከቁርጭምጭሚት የወረደዉ የእሳት ነው››

(ቡኻሪና በቁጥር 5787 ዘግበዉታል)

ይህ ሁሉንም ልብስ እንደሚያካትት ለመግለፅ አል-ኢማም አልቡኻሪይ ከቁርጭምጭሚት የወረደዉ የእሳት ነው›› የሚል ርዕስ ሰጥተዉታል።

‹‹ማንኛዋም ሴት ሽቶን ተነስንሳ ወደ መስጂድ የወጣች እንደሆነ እስክጣጠብ ድረስ ሰላቷ ተቀባይነት የለውም፡፡››  

          (ኢብኑ ማጃህ እና አህመድ ዘግበውታል አልባኒም ሰሂህ መሆኑን ገልፀዋል፡፡)

 

عن أبي هريرة قال: قال صلى الله عليه وسلم : "صِنفانِ مِن أهلِ النارِ لم أرَهما: قومٌ معهم سِياطٌ كأذنابِ البقرِ يَضْرِبُونَ بها الناسَ، ونِساءٌ كاسياتٌ عارياتٌ مميلاتٌ مائلاتٌ، رؤوسُهُنَّ كأسنِمَةِ البُخْتِ المائلةِ لا يَدْخُلْنَ الجنةَ ولا يَجِدْنَ رِيحَهَا، وإن رِيحَهَا لَيوجَدُ مِن مَسيرةِ كذا وكذا".        رواه مسلم (2128)

 

  ‹‹ከእሳት ሰዎች መካከል ሁለት አይነት ሰዎች እኔ ያላየኋቸውም(ወደፊት የሚመጡ)፤ ለብሰው ያልለበሱ አካሄዳቸው እና እንቅስቃሲያቸው   ወደርካሽ አላማ ያዘነበሉ፤ ሌሎችንም የሚያሳስቱ ፀጉራቸው ልክ እንደ ግመል ሻኛ የተከመረ ሴቶች ናቸው፤ እንደነዚህ አይነቶቹ ጀነትን አይገቡም ሽታዋንም አያገኙትም፡፡›› (ሙስሊም ዘግበውታል)

4. ባዕድ በሆኑ ወንዶችና ሴቶች መካከል መቀላቀል፤ አልፎም መጨባበጥና መሳሳም፡፡ ይህ ሸሪዐው ክፉኛ የኮነነው ተግባር ነው፤ የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁን) ከእለታት አንድ ቀን ከመስጂድ በመውጣት ላይ ሳሉ ወንዶች ከሴቶች ጋር በመንገድ ላይ ተቀላቅለው ተመለከቱ ይህንን ክስተት በማስመልከትም ‹‹ከወንዶች ወደ ኋላ ሁኑ፤ የመንገዱንም መሀከል ይዛችሁ ልትጓዙ አይገባም›› አሉ፡፡ ይህንን ሀዲስ የዘገበው ሰሀቢይ ‹‹ከዚህ በኋላ ሴቶች በጣም ወደ ዳር ከመውጣታቸው ልብሳቸው በአጥር ይያዝ ነበር፡፡›› በማለት ይናገራል፡፡  

(አቡዳውድ  ሱነናቸው ላይ ሲዘግቡት አልባኒ ሀሰን የሚል ደረጃ ሰጥተውታል)

ይህ ሀዲስ ሸሪዐ በጥቅሉ ወደ ሀራም የሚያደርሱ ነገሮችን የከለከለ መሆኑን ከሚያሳዩ መረጃዎች አንዱ ነው፡፡

በሌላ ሀዲስ ላይ የአላህ መልእክተኛ (ሰላትና ሰለም በርሳቸው ላይ ይሁን)  ‹‹እኔ ሴቶችን አልጨብጥም›› ማለታቸው ሰፍሯል፡፡ ሀዲሱ አንድ ሰው ምንም እንኳ የተቀደሰ አላማና ንፁህ ልቦና ነው የያዝኩት ቢልም ባዕድ ሴቶችን ከመጨበጥ ሊቆጠብ እንደሚገባ የሚያመለክት ነው፡፡

5.  እንደ ሙዚቃ እና መሰል የተከለከሉ ነገሮችን በማድጥ እንዲሁም የሴቶች ፊልሞችን መመልከት እና ጊዜን ማጥፋት፡፡ ሌሎችንም እርም የሆኑ ተግባራት መጠንቀቅ ይገባል

6. ምግብና መጠጥን ማባከን፡፡


             

ኢስላም በራሱ የተሟላ ነው

  እንደሚታወቀው ዲናችን (ሀይማኖታችን) ኢስላም ምሉዕ ነው፡፡ ስለሆነም ለሁሉም የአምልኮ ዘርፎች እንዲሁም የህይወት መስኮች  ደንቦችን ደንግጓል ስርዐቶችንም አስቀምጧል፡፡ ሕግጋቶቹ ፍትሀዊ እና ሚዛናዊ ስርዐቶቹም ለሁሉም ቦታ እና ዘመን የሚበጁ ናቸው፡፡ አላህ (ሱብሀነሁ ወተአላ) እንዲህ ይላል፡፡

 

{الْيَوْمَ أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِي وَرَضِيتُ لَكُمُ الْإِسْلَامَ دِينًا} المائدة 3

‹‹ዛሬ ሐይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ፤ ፀጋዬንም በእናንተ ላይ ፈፀምኩ፤ከሀይማኖት በኩልም ለእናንተም ኢስላምን ወደደኩ....›› (አልማኢዳ፡ 3)

 

ከዚህም በመነሳት መጨመርንም ይሁን መቀነስን አይቀበልም እንዲሁም ከሌሎች መኮረጅንም ሆነ መመሳሰልን ይከለክላል፡፡

 

ይህንን እዉነታ የአላህ መልእክተኛ (የአላህ ሰላምና ሰላት በርሳቸው ላይ ይሁን) በነዚህ ሁለት ነብያዊ አስተምህሮቶች ይገልፁታል፡፡

 

ففي حديث عائشة رضي الله عنها أنها قالت : قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : ( من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد ) رواه البخاري (2697)  ومسلم (1718)

‹‹በዚህ በዲናችን ላይ ከርሱ ያልሆንን ያመጣ (ሰው) ስራው ተመላሽ ነው፡፡ (ተቀባይነት አይኖረውም)›› (ቡኻሪ እና ሙስሊም ዘግበውታል)

 

عَنْ ابْنِ عُمَرَ قَالَ : قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ : ( مَنْ تَشَبَّهَ بِقَوْمٍ فَهُوَ مِنْهُمْ ) رواه أبو داود (4031)

‹‹ከህዝቦች የተመሳሰለ እረሱ ከነርሱ ነው፡፡›› (አቡ ዳውድ ዘግበውታል) 


Etiquette of Eid

What are the Sunnahs and etiquettes that we should act in accordance with on the day of Eid?.

Praise be to Allaah.  

The Sunnahs that the Muslim should observe on the day of Eid are as follows: 

1 – Doing ghusl before going out to the prayer. 

It was narrated in a saheeh hadeeth in al-Muwatta’ and elsewhere that ‘Abd-Allaah ibn ‘Umar used to do ghusl on the day of al-Fitr before going out to the prayer-place in the morning. Al-Muwatta’ 428. 

Al- Nawawi (may Allaah have mercy on him) said that the Muslims were unanimously agreed that it is mustahabb to do ghusl for Eid prayer. 

The reason why it is mustahabb is the same reason as that for doing ghusl before Jumu’ah and other public gatherings. Rather on Eid the reason is even stronger. 

2 – Eating before going out to pray on Eid al-Fitr and after the prayer on Eid al-Adha: 

Part of the etiquette is not to go out to pray on Eid al-Fitr until one has eaten some dates, because of the hadeeth narrated by al-Bukhaari from Anas ibn Maalik, who said that the Messenger of Allaah (peace and blessings of Allaah be upon him) used not to go out on the morning of Eid al-Fitr until he had eaten some dates… of which he would eat an odd number. Al-Bukhaari, 953. 

It is mustahabb to eat before going out to emphasize the fact that it is forbidden to fast on that day and to demonstrate that the fast has ended. 

Ibn Hajar (may Allaah have mercy on him) suggested that the reason for that was so as to ward off the possibility of adding to the fast, and to hasten to obey the command of Allaah. Al-Fath, 2/446 

Whoever does not have any dates may break his fast with anything that is permissible. 

But on Eid al-Adha it is mustahabb not to eat anything until one comes back from the prayer, so he should eat from the udhiyah if he has offered a sacrifice. If he is not going to offer a sacrifice there is nothing wrong with eating before the prayer. 

3 – Takbeer on the day of Eid 

This is one of the greatest Sunnahs on the day of Eid because Allaah says (interpretation of the meaning): 

“(He wants that you) must complete the same number (of days), and that you must magnify Allaah [i.e. to say Takbeer (Allaahu Akbar: Allaah is the Most Great)] for having guided you so that you may be grateful to Him”

[al-Baqarah 2:185] 

It was narrated that al-Waleed ibn Muslim said: I asked al-Awzaa’i and Maalik ibn Anas about saying Takbeer out loud on the two Eids. They said, Yes, ‘Abd-Allaah ibn ‘Umar used to say it out loud on the day of al-Fitr until the imam came out (to lead the prayers). 

It was narrated in a saheeh report that ‘Abd al-Rahmaan al-Sulami said, “They emphasized it more on the day of al-Fitr than the day of al-Adha.”. Wakee’ said, this refers to the takbeer. See Irwa’ al-Ghaleel, 3/122/ 

Al-Daaraqutni and others narrated that on the morning of Eid al-Fitr and Eid al-Adha, Ibn ‘Umar would strive hard in reciting takbeer until he came to the prayer place, then he would recite takbeer until the imam came out. 

Ibn Abi Shaybah narrated with a saheeh isnaad that al-Zuhri said: The people used to recite Takbeer on Eid when they came out of their houses until they came to the prayer place, and until the imam came out. When the imam came out they fell silent, and when he said takbeer they said takbeer. See Irwa’ al-Ghaleel, 1/121 

Saying takbeer when coming out of one's house to the prayer place and until the imam came out was something that was well known among the salaf (early generations). This has been narrated by a number of scholars such as Ibn Abi Shaybah, ‘Abd a l-Razzaaq and al-Firyaabi in Ahkaam al-Eidayn from a group of the salaf. For example, Naafi’ ibn Jubayr used to recite takbeer and was astonished that the people did not do so, and he said, “Why do you not recite takbeer?” 

Ibn Shihaab al-Zuhri (may Allaah have mercy on him) used to say, “The people used to recite takbeer from the time they came out of their houses until the imam came in.” 

The time for takbeer on Eid al-Fitr starts from the night before Eid until the imam enters to lead the Eid prayer. 

In the case of Eid al-Adha, the takbeer begins on the first day of Dhu’l-Hijjah and lasts until sunset on the last of the days of tashreeq. 

Description of the takbeer: 

It was narrated in the Musannaf of Ibn Abi Shaybah with a saheeh isnaad from Ibn Mas’ood (may Allaah be pleased with him) that he used to recite takbeer during the days of tashreeq: 

Allaahu akbar, Allaahu akbar, laa ilaaha ill-Allaah, wa Allaahu akbar, Allaah akbar, wa Lillaah il-hamd (Allaah is Most Great, Allaah is most Great, there is no god but Allaah, Allaah is Most great, Allaah is most great, and to Allaah be praise). 

It was also narrated elsewhere by Ibn Abi Shaybah with the same isnaad, but with the phrase “Allaahu akbar” repeated three times. 

Al-Mahaamili narrated with a saheeh isnaad also from Ibn Mas’ood: “Allaahu akbaru kabeera, Allaahu akbaru kabeera, Allaahu akbar wa ajallu, Allaahu akbar wa Lillaah il-hamd (Allaah is Most Great indeed, Allaah is Most Great indeed, Allaah is most Great and Glorified, Allaah is Most Great and to Allaah be praise).” See al-Irwa’, 3/126. 

4 – Offering congratulations 

The etiquette of Eid also includes the congratulations and good wishes exchanged by people, no matter what the wording, such as saying to one another Taqabbala Allaah minna wa minkum (May Allaah accept (good deeds) from us and from you” or “Eid mubaarak” and other permissible expressions of congratulations. 

It was narrated that Jubayr ibn Nufayr said: When the companions of the Prophet (peace and blessings of Allaah be upon him) met one another on the day of Eid, they would say to one another, “May Allaah accept (good deeds) from us and from you.” Ibn Hajar said, its isnaad is hasan. Al-Fath, 2/446. 

Offering congratulations was something that was well known among the Sahaabah, and scholars such as Imam Ahmad and others allowed it. There is evidence which suggests that it is prescribed to offer congratulations and good wishes on special occasions, and that the Sahaabah congratulated one another when good things happened, such as when Allaah accepted the repentance of a man, they went and congratulated him for that, and so on. 

Undoubtedly these congratulations are among the noble characteristics among the Muslims. 

The least that may be said concerning the subject of congratulations is that you should return the greetings of those who congratulate you on Eid, and keep quiet if others keep quiet, as Imam Ahmad (may Allaah have mercy on him) said: If anyone congratulates you, then respond, otherwise do not initiate it. 

5 – Adorning oneself on the occasion of Eid. 

It was narrated that ‘Abd-Allaah ibn ‘Umar (may Allaah be pleased with him) said that ‘Umar took a brocade cloak that was for sale in the market and brought it to the Messenger of Allaah (peace and blessings of Allaah be upon him), and said, “O Messenger of Allaah, buy this and adorn yourself with it for Eid and for receiving the delegations.” The Messenger of Allaah (peace and blessings of Allaah be upon him) said to him, “Rather this is the dress of one who has no share (of piety or of reward in the Hereafter)…” Narrated by al-Bukhaari, 948. 

The Prophet (peace and blessings of Allaah be upon him) agreed with ‘Umar on the idea of adorning oneself for Eid, but he denounced him for choosing this cloak because it was made of silk. 

It was narrated that Jaabir (may Allaah be pleased with him) said: The Prophet (peace and blessings of Allaah be upon him) had a cloak which he would wear on the two Eids and on Fridays. Saheeh Ibn Khuzaymah, 1756, 

Al-Bayhaqi narrated with a saheeh isnaad that Ibn ‘Umar used to wear his best clothes on Eid. 

So a man should wear the best clothes that he has when going out for Eid. 

With regard to women, they should avoid adorning themselves when they go out for Eid, because they are forbidden to show off their adornments to non-mahram men. It is also haraam for a woman who wants to go out to put on perfume or to expose men to temptation, because they are only going out for the purpose of worship. 

6 – Going to the prayer by one route and returning by another. 

It was narrated that Jaabir ibn ‘Abd-Allaah (may Allaah be pleased with him) said: On the day of Eid, the Prophet (peace and blessings of Allaah be upon him) used to vary his route. Narrated by al-Bukhaari, 986. 

It was said that the reason for that was so that the two routes would testify for him on the Day of Resurrection, for the earth will speak on the Day of Resurrection and say what was done on it, both good and bad. 

And it was said that it was in order to manifest the symbols of Islam on both routes, or to manifest the remembrance of Allaah (dhikr), or to annoy the hypocrites and Jews, and to scare them with the large number of people who were with him. And it was said that it was in order to attend to the people’s needs, to answer their questions, teach them, set an example and give charity to the needy, or to visit his relatives and uphold the ties of kinship.

 And Allaah knows best.


ما هي السنن والآداب التي نفعلها عليها يوم العيد ؟.

الحمد لله

من السنن التي يفعلها المسلم يوم العيد ما يلي :

1- الاغتسال قبل الخروج إلى الصلاة :

فقد صح في الموطأ وغيره أَنَّ عَبْدَ اللَّهِ بْنَ عُمَرَ كَانَ يَغْتَسِلُ يَوْمَ الْفِطْرِ قَبْلَ أَنْ يَغْدُوَ إِلَى الْمُصَلَّى . الموطأ 428

وذكر النووي رحمه الله اتفاق العلماء على استحباب الاغتسال لصلاة العيد .

والمعنى الذي يستحب بسببه الاغتسال للجمعة وغيرها من الاجتماعات العامة موجود في العيد بل لعله في العيد أبرز .

2- الأكل قبل الخروج في الفطر وبعد الصلاة في الأضحى :

من الآداب ألا يخرج في عيد الفطر إلى الصلاة حتى يأكل تمرات لما رواه البخاري عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ قَالَ كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ لا يَغْدُو يَوْمَ الْفِطْرِ حَتَّى يَأْكُلَ تَمَرَاتٍ .. وَيَأْكُلُهُنَّ وِتْرًا . البخاري 953

وإنما استحب الأكل قبل الخروج مبالغة في النهي عن الصوم في ذلك اليوم وإيذانا بالإفطار وانتهاء الصيام .

وعلل ابن حجر رحمه الله بأنّ في ذلك سداً لذريعة الزيادة في الصوم ، وفيه مبادرة لامتثال أمر الله . فتح 2/446

ومن لم يجد تمرا فليفطر على أي شيء مباح .

وأما في عيد الأضحى فإن المستحب ألا يأكل حتى يرجع من الصلاة فيأكل من أضحيته إن كان له أضحية ، فإن لك يكن له من أضحية فلا حرج أن يأكل قبل الصلاة .

3- التكبير يوم العيد :

وهو من السنن العظيمة في يوم العيد لقوله تعالى : ( ولتكملوا العدة ولتكبروا الله على ما هداكم ولعلكم تشكرون ) .

وعن الوليد بن مسلم قال : سألت الأوزاعي ومالك بن أنس عن إظهار التكبير في العيدين ، قالا : نعم كان عبد الله بن عمر يظهره في يوم الفطر حتى يخرج الإمام .

وصح عن أبي عبد الرحمن السلمي قال : ( كانوا في الفطر أشد منهم في الأضحى ) قال وكيع يعني التكبير . انظر إرواء الغليل 3/122

وروى الدارقطني وغيره أن ابن عمر كان إذا غدا يوم الفطر ويوم الأضحى يجتهد بالتكبير حتى يأتي المصلى ، ثم يكبر حتى يخرج الإمام .

وروى ابن أبي شيبة بسند صحيح عن الزهري قال : كان الناس يكبرون في العيد حين يخرجون من منازلهم حتى يأتوا المصلى وحتى يخرج الإمام فإذا خرج الإمام سكتوا فإذا كبر كبروا . انظر إرواء الغليل 2/121

ولقد كان التكبير من حين الخروج من البيت إلى المصلى وإلى دخول الإمام كان أمراً مشهوراً جداً عند السلف وقد نقله جماعة من المصنفين كابن أبي شيبة و عبدالرزاق والفريابي في كتاب ( أحكام العيدين ) عن جماعة من السلف ومن ذلك أن نافع بن جبير كان يكبر ويتعجب من عدم تكبير الناس فيقول : ( ألا تكبرون ) .

وكان ابن شهاب الزهري رحمه الله يقول : ( كان الناس يكبرون منذ يخرجون من بيوتهم حتى يدخل الإمام ) .

ووقت التكبير في عيد الفطر يبتدئ من ليلة العيد إلى أن يدخل الإمام لصلاة العيد .

وأما في الأضحى فالتكبير يبدأ من أول يوم من ذي الحجة إلى غروب شمس آخر أيام التشريق .

- صفة التكبير..

ورد في مصنف ابن أبي شيبة بسند صحيح عن ابن مسعود رضي الله عنه : أنه كان يكبر أيام التشريق : الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله والله أكبر الله أكبر ولله الحمد . ورواه ابن أبي شيبة مرة أخرى بالسند نفسه بتثليث التكبير .

وروى المحاملي بسند صحيح أيضاً عن ابن مسعود : الله أكبر كبيراً الله أكبر كبيراً الله أكبر وأجلّ ، الله أكبر ولله الحمد . أنظر الإرواء 3/126

4- التهنئة :

ومن آداب العيد التهنئة الطيبة التي يتبادلها الناس فيما بينهم أيا كان لفظها مثل قول بعضهم لبعض : تقبل الله منا ومنكم أو عيد مبارك وما أشبه ذلك من عبارات التهنئة المباحة .

وعن جبير بن نفير ، قال : كان أصحاب النبي صلى الله عليه وسلم إذا التقوا يوم العيد يقول بعضهم لبعض ، تُقُبِّل منا ومنك . قال ابن حجر : إسناده حسن . الفتح 2/446

فالتهنئة كانت معروفة عند الصحابة ورخص فيها أهل العلم كالإمام أحمد وغيره وقد ورد ما يدل عليه من مشروعية التهنئة بالمناسبات وتهنئة الصحابة بعضهم بعضا عند حصول ما يسر مثل أن يتوب الله تعالى على امرئ فيقومون بتهنئته بذلك إلى غير ذلك .

ولا ريب أن هذه التهنئة من مكارم الأخلاق والمظاهر الاجتماعية الحسنة بين المسلمين .

وأقل ما يقال في موضوع التهنئة أن تهنئ من هنأك بالعيد ، وتسكت إن سكت كما قال الإمام أحمد رحمه الله : إن هنأني أحد أجبته وإلا لم أبتدئه .

5- التجمل للعيدين..

عن عبد الله بن عُمَرَ رضي الله عنه قَالَ أَخَذَ عُمَرُ جُبَّةً مِنْ إِسْتَبْرَقٍ تُبَاعُ فِي السُّوقِ فَأَخَذَهَا فَأَتَى بِهَا رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ فَقَالَ يَا رَسُولَ اللَّهِ ابْتَعْ هَذِهِ تَجَمَّلْ بِهَا لِلْعِيدِ وَالْوُفُودِ فَقَالَ لَهُ رَسُولُ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِنَّمَا هَذِهِ لِبَاسُ مَنْ لا خَلاقَ لَهُ .. رواه البخاري 948

فأقر النبي صلى الله عليه وسلم عمر على التجمل للعيد لكنه أنكر عليه شراء هذه الجبة لأنها من حرير .

وعن جابر رضي الله عنه قال : كان للنبي صلى الله عليه وسلم جبة يلبسها للعيدين ويوم الجمعة . صحيح ابن خزيمة 1765

وروى البيهقي بسند صحيح أن ابن عمر كان يلبس للعيد أجمل ثيابه .

فينبغي للرجل أن يلبس أجمل ما عنده من الثياب عند الخروج للعيد .

أما النساء فيبتعدن عن الزينة إذا خرجن لأنهن منهيات عن إظهار الزينة للرجال الأجانب وكذلك يحرم على من أرادت الخروج أن تمس الطيب أو تتعرض للرجال بالفتنة فإنها ما خرجت إلا لعبادة وطاعة .

6- الذهاب إلى الصلاة من طريق والعودة من آخر ..

عَنْ جَابِرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا قَالَ كَانَ النَّبِيُّ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ إِذَا كَانَ يَوْمُ عِيدٍ خَالَفَ الطَّرِيقَ . رواه البخاري 986

قيل الحكمة من ذلك ليشهد له الطريقان عند الله يوم القيامة ، والأرض تحدّث يوم القيامة بما عُمل عليها من الخير والشرّ .

وقيل لإظهار شعائر الإسلام في الطريقين .

وقيل لإظهار ذكر الله .

وقيل لإغاظة المنافقين واليهود وليرهبهم بكثرة من معه .

وقيل ليقضى حوائج الناس من الاستفتاء والتعليم والاقتداء أو الصدقة على المحاويج أو ليزور أقاربه وليصل رحمه .

والله أعلم
 .
 
 

--
--
"አላህ መልካም የሻለትን (ሰው) ዲኑን ያስገነዝበዋል" (ቡኻሪና ሙስሊም)
Nesiha Ethiopian Muslims Discussion Network is looking forward to serve you.
Our focus is to acquire beneficial knowledge insha-Allah
'Uthmaan (radhi-yallaahu 'anhu) said:((Knowledge is better than wealth; Knowledge protects you and you (have to) protect wealth)).al-Khateeb in al-Faqeeh wal-Mutafaqqih - Volume 1, Page15
to post your messages please send email to nes...@googlegroups.com
to view past discussions visit http://groups.google.com/group/nesiha/topics?gvc=2
to unsubscribe send email to the Moderator
To visit our sites
http://www.nesihaa.com
----------------
Moderator,
أبو جنيد صالح بن أحمد
Abujunaid Salah Ahmed
 
---
The following physical address is associated with this mailing list:
 
Ibnu Maso'ud Islamic Center
P.O.Box- 50151
+251112781893
Addis Ababa
Ethiopia
 
 

--
--
"አላህ መልካም የሻለትን (ሰው) ዲኑን ያስገነዝበዋል" (ቡኻሪና ሙስሊም)
Nesiha Ethiopian Muslims Discussion Network is looking forward to serve you.
Our focus is to acquire beneficial knowledge insha-Allah
'Uthmaan (radhi-yallaahu 'anhu) said:((Knowledge is better than wealth; Knowledge protects you and you (have to) protect wealth)).al-Khateeb in al-Faqeeh wal-Mutafaqqih - Volume 1, Page15
to post your messages please send email to nes...@googlegroups.com
to view past discussions...
Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages