أنت تستلم هذه الرسالة لأنك مشترك
بقائمة شبكة النصيحةالبريدية راسل المشرف لإلغاء الإشتراك
you
receive this email because you are member in nesiha Group send request to unsubscribe
ነሲሀ ኢስላማዊ የዉይይት መድረክ
Assalamualaikum Warahmatullahi Wabarakatuhu
'አወዛጋቢው የመውሊድ በዓል'
(ከአታችመንት ዳውንሎድ ያድርጉ)
ከሁሉ በፊት፣ ምስጋና ለሀያሉና አሸናፊው አላህ -ሱብሃነሁ ወተዓላ- ይገባው፡፡ ከአላህ -ሱብሃነሁ ወተዓላ- በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የሌለ መሆኑንና ነብዩ ሙሀመድ -አለይሂ ሶላቱ ወሰላም- የአላህ አገልጋይና መልክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ፡፡
ከዚህ በመቀጠል... አንተ ሙስሊም ወንድሜ፣ አንቺ ሙስሊም እህቴ ሆይ! እኔ ወንድማችሁ ለምን መውሊድን እንደማላከብር ከቁርአንና ከትክክለኛ (ሶሂህ) ሀዲስ ማስረጃዬን በማጣቀስ ምክንያቶቼን አቀርባለሁ፤ ልብ ብላችሁ መጣጥፏን አንብቡልኝ፡-
🚩 ምክንያት አንድ- እስልምናችን የተሟላ በመሆኑ! ከሁሉም በላይ እስልምናችን ሙሉዕ (perfect) ነው፡፡ የሚጎድለው ነገር የለምና አይጨመርበትም፤ የማይፈለግ ነገር የለውምና አይቀነስለትም፡፡ አላህ -ሱብሃነሁ ወተዓላ- ነብዩ ሙሀመድን -አለይሂ ሶላቱ ወሰላም- የላከልን እስልምናን ለማሟላትና ለመደምደም ነው፡፡ ስለሆነም ማንም ሰው ረሱላችን ባመጡት በዚህ ዲን ላይ ቅንጣት የመጨመርም ሆነ፣ የመቀነስ መብት የለውም፡፡
አላህ -ሱብሃነሁ ወተዓላ- በቁርአኑ እንዲህ በማለት ለእስልምናችን ሙሉዕነት ማረጋገጫ ሰጥቷል፤ “ዛሬ ቀን ሀይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ፤ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ደመደምኩ፡፡” (ሱረቱል ማኢዳ፡3)
የታላቆች ሁሉ ታላቅ የሆነው አሏህ ይህን የመሰለ ማረጋገጫ በመስጠት፣ ‘ዲናችሁን አሟልቸላችኋለሁ’ እያለ፣ እንዴት ተደርጎ ነው በቁርአንም ሆነ በሀዲስ ያልታዘዘ መውሊድ የእስልምና አካል ተደርጎ የሚከበረው? ከየት በመጣ አጉል ድፍረት ነው፣«‘አሏህ ሀይማኖታችሁን ሞልቸላችኋለሁ’ ቢልም፣ መውሊድን ማክበር አለብን» ብዬ ሽርጉድ የምለው? «መውሊድ የእስልምና አካል ነው» ማለት «ረሱል- አለይሂ ሶላቱ ወሰላም- ማድረስ የሚገባቸውን
መልዕክት በትክክል አላደረሱልንም» ወይም «ማድረስ ከሚገባቸው ውስጥ ያስቀሩት አለ» ከማለት ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡
ውድ ሙስሊም ወንድሜ! ውድ ሙስሊም እህቴ! ይሄውላችሁ ይህን ከመሰለው አደጋ ራሴን ለመጠበቅ ስል ነው መውሊድን የማላከብረው፡፡
🚩 ምክንያት ሁለት - መውሊድን እንድናከብር ባለመታዘዛችን!
መውሊድ፣ ግለሰቦች በኢስላም ላይ የጨመሩት ፈጠራ (ቢድአ) ነውና በቁርአንም ሆነ በሀዲስ ቅንጣት ማስረጃ የለውም፡፡ አሏህን በብቸኝነት ለማምለክ፣ ሶላት ለመስገድ፣ ረመዷንን ለመፆም፣ ዘካን ለመስጠት፣ ሀጅ ለመሄድ፣ ወዘተ. ይቅርና ትርፍ/ተጨማሪ የአምልኮ ስራዎችን ለመስራት ደረትን የሚያስነፋ ማስረጃ ሞልቷል፡፡ ሌላው ይቅርና መፀዳጃ ቤት ስንገባ ወይም ከመፀዳጃ ቤት ስንወጣ ማድረግ ስለሚገባን ዱአ በቂና አስተማማኝ የሀዲስ ማስረጃ አለን፡፡ ታዲያ መውሊድን ያህል አመታዊ በአል ለዚያውም እንደሚባለው ለረሱላችን ያለንን ፍቅር የምንገልፅበት የኢባዳ ተግባር ሆኖ ሳለ መረጃ የለሽ የሆነው ለምንድነው? መልሱ አጭር ነው፤ መውሊድ በኢስላም ላይ የተደረተ ፈጠራ (ቢድአ) ነው፡፡ በኢስላም ውስጥ ያለ በቂ ማስረጃ የሚስሰራ ኢባዳ (አምልኮት) ከንቱ ልፋት ነው፤ ለዚያውም በመጨረሻው ቀን ተጠያቂ የሚያደርግ፡፡ ሀያሉ አሏህ ያዘዘን ‘ሰዎች የሚጨምሩላችሁንም ተከተሉ’ ብሎ አይደለም፤ ኧረ በፍፁም! ይህን ከመሰለው ጉድለት ፍፁም የጠራው አምላካችን እንዲህ ሲል ነው ያዘዘን፤ «አሏህንም ተገዙ፤ መልዕክተኛውንም ታዘዙ፡፡» (አል-ተጋቡን፣ 12)
ውዱ ሙስሊም መንድሜ፣ ውዷ ሙስሊም እህቴ ሆይ! ይሄውላችሁ ይህን የጌታዬን ትእዛዝ ሰጥ-ለጥ ብዬ ማክበር ስላለብኝ፣ ሰዎች ባለማውቅ የጨመሩትን መውሊድ አላከብርም፡፡
🚩ምክንያትሶስት - መውሊድን ማክበር መልእክተኛውን መቃረን በመሆኑ!
አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ የራሱ ቃል በሆነው በተከበረው ቁርአኑ እንዲህ በማለት አዞናል፤ «መልዕክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት፡፡ ከርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ፡፡» (አል-ሐሽር፣ 7) የነብያት ሁሉ ፈርጥ የሆኑት ረሱላችን -አለይሂ ሶላቱ ወሰላም- ከከለከሉን ነገሮች ሁሉ አንዱና ዋናው ቢድአ ነው፤ “በዲን ላይ የሚፈጠሩን ነገሮች ሁሉ አደራ ተጠንቀቋቸው፡፡ ማንኛውም በዲን ላይ የሚደረግ ፈጠራ (ቢድአ) ጥሜት ነው፤ የማንኛውም ጥሜት መዳረሻ ደግሞ የጀሀነም እሳት ነው» በማለት የቢድአን አደገኛነት በወርቃማ ንግግራቸው አሳስበውናል፤ ማንኛውንም የቢድአን ተግባር እንዳንፈፅም ከልክለውናል፡፡ ረሱላችን ያላስተማሩትና እንዲሰራ ያላዘዙት የአምልኮ ተግባር ነውና መውሊድ የለየለት ቢድአ ነው፤ በፈለገው የቃለት ጋጋታ ቢሞካሽ፣ በፈለገው የህዝብ ብዛት ቢታጀብ ጥሜት ነው፡፡ መውሊድን ማክበር ረሱላችንን በግሀድ መቃረን ነው፡፡
ሙስሊም ወገኖቼ ሆይ! ለዚህ ነው መውሊድን የማላከብረው፣ ረሱላችንን መቃረን በአሏህ ላይ ማመፅ በመሆኑና የዚህ አይነቱ አመፅ ፍፃሜ ደግሞ ከጀሀነም እሳት ስለሚያስገባ፣ አሏህ በሱረቱል አኒሳዕ አንቀፅ 14 ላይ አስምሮ እንደነገረን፡፡
🚩ምክንያት አራት - በኢስላም ውስጥ የተፈቀዱት ሁለት አመታዊ ኢዶች ብቻ በመሆናቸው!
አቡዳውድና ነሳኢይ በዘገቡት ሀዲስ መሰረት ረሱል -አለይሂ ሶላቱ ወሰላም- አሏህ፣ ለሙስሊሞች ሁለት የበአል ቀናትን፣ ማለትም የውመል አድሃ (በተለምዶ አረፋ በአል የምንለውን) እና የውመል ፊጥርን ሰጥቷል፡፡ ከዚህ ውጭ አሏህ የሰጠንም፣ የፈቀደልንም አመታዊ በአል የለም፡፡ በበአል ቀን ብቻ ሳይሆን፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ ባለ በማንኛውም የአምልኮ ዘርፍ ፍፁም ጥበበኛ የሆነው አሏህ የሰጠንና የፈቀደልን በቂያችን ነው፡፡ እስልምና ማለት እሱ ነው፤ መላ መንፈሳችንን፣ ስሜታችንናና አካላችንን ሙሉ በሙሉ ለአላህ ትዕዛዝና ፈቃድ ብቻ ተገዢ ማድረግ፡፡ አላህ በቁርዓን እንዲህ ይላል፤ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ሁላችሁም በመታዘዝ ውስጥ ግቡ፤ የሰይጣንንም እርምጃዎች አትከተሉ…” (በቀራህ፣ 208) እናም መውሊድን ማክበር ከአሏህ ፈቃድ፣ ከአሏህ መታዘዝ መውጣት ነው፡፡
ሙስሊም ወንድሜ፣ ሙስሊም እህቴ ሆይ! ይሄውላችሁ ለዚህ ነው መውሊድን የማላከብረው፡፡
🚩 ምክንያት አምስት - ከእነዚያ እንቁ ሶሀቦች የበለጠ ረሱላችንን የሚወድ ማንም ባለመኖሩ!
አንዳንድ ሰዎች መውሊድን የሚያከብሩት ነብዩን -አለይሂ ሶላቱ ወሰላም- በጣም ስለሚወዱ መሆኑን ይናገራሉ፡፡ እሳቸውን መውደዳቸው እሰዬ የሚያስብል ነው፡፡ ሆኖም ግን ከነዚያ እንቁዬ ሶሀቦች «አብልጠን እንወዳቸዋለን» ሊሉ አይችሉም፤ ካሉም ሽምጥጥ ያለ ቅጥፈት ይሆንባቸዋል፡፡ እነዚያ የኢስላም የቁርጥ ቀን ልጆች፣ እነዚያ አሏህ ለኢስላም የመረጣቸው ሶሀቦች፣ እነዚያ ረሱልን ከነፍሳቸው የበለጠ የሚወዱና በተግባርም ያስመሰከሩ ሶሀቦች ያልሰሩት ዲናዊ የውዴታ መገለጫ፣ እሳቸውን የመውደድ ዲናዊ መገለጫ ፍፁም ሊሆን አይችልም፡፡
የእነዚያ በጀነት የተመሰከረላቸው የእነአቡቦክር፣ የእነኡመር፣ የእነኡስማን፣ የእነአልይ፣ ወዘተ. የኢማን ደረጃና የተቅዋ ምጥቀት ከሰማየ ሰማያት እርቆ እንደሚገኘው አብሪ ኮከብ ቢሆን፣ የእኔ የኢማን ደረጃና ተቅዋዬ ከምድር የመጨረሻው ወለል ላይ እንኳን ለመገኘቱ ምንም ማረጋገጫ የለኝም፡፡ በእርግጥ መውሊድ ትክክለኛ የነብዩ ውዴታ መገለጫና የዲናችን አካል ቢሆን ኖሮ፣ ረሱላችን ባዘዙን፣ እኒያ የኢስላም ፈርጦችም በተገበሩት ነበር፡፡ ስለሆነም እነአቡቦክር፣ እነኡመር፣ እነኡስማን፣ እነአልይ... ለውዴታ ብለው ያልሰሩት ኢባዳ፣ ነብዩን የመውደድ መገለጫ ሊሆን አይችልም፡፡ ረሱላችንን እጅግ በጣም የሚወድ ሰው ምን ማድረግ አለበት? አሏህን በብቸኝነት ማምለክ፣ ረሱላችን ያዘዙትን መስራትና የከለከሉትን መተው፣ ብርቅዬ ሰሀቦች በተጓዙበት የዲን ጎዳና ቀጥ ብሎ መጓዝ! አራት ነጥብ!
ሙስሊም ወንድሜ፣ ሙስሊም እህቴ ሆይ! መውሊድን ማክበር «ረሱላችንን ከነዚህ የኢስላም አብሪ ኮከብ ከሆኑ ሶሀቦች የበለጠ እወዳለሁ» ማለት ስለሆነ ጭምር ነው መውሊድን የማላከብረው፡፡
🚩ምክንያት ስድስት - መውሊድ የሽርክ ተግባራት መናኻሪያ በመሆኑ!
ሙስሊም ወንድሜ፣ ሙስሊም እህቴ ሆይ! እስቲ የሚከተለውን የመውሊድ ግጥም ልብ ብለን እናንብብ፤
ያወጣማ ሰው መውሊድ
ቀልቡን ሳይከብደው በውድ
ይደርሱለታል (ረሱል) ከለህዱ
ትቶት ሲመለስ ዘመድ-አዝማዱ፡፡
ይህ ግጥም ሁለት እጅግ መሰረታዊ የሆኑ ግድፈቶችን የያዘ ነው፡፡
አንደኛ - አንድ ሙስሊም ሲቀበር ረሱል ወደ ቀብሩ ወይም ለህዱ እንደሚመጡ የሚገልፅ አንድም የቁርአን የሆነ የሀዲስ ማስረጃ (evidence) የለም፡፡ ስለዚህም የግጥሙ ሀሳብ ውሸት ነው፣ በረሱላችን ላይ የተፈበረከ ቅጥፈት፡፡
ሁለተኛ - ለአንድ ሟች በለህድ ውስጥ ከስራውና ኢማኑ ውጭ ሌላ አካል “ይደርስለታል” ብሎ ማመን በአሏህ ላይ የማጋራት (የማሻረክ) ተግባር ነው፡፡
🔎 እስቲ ከቡሰይሪ የመውሊድ ኪታብ አንድ-አራት ስንኞችን ለአብነት ያህል ቀንጨብ እናድርግ፡-
አንቱ ከፍጥረቱ ሁሉ የተከበሩና የተላቁ (ነብይ) ሆይ!
ዱንያና አኼራ ናቸው ያንቱ ስጦታ
በለህወል መህፉዝ በየትኛውም ቦታ
ካንቱ እውቀት ውጭ የለውም ጠብታ፡፡
🔎 ይህ የቡሰይሪ ግጥም የሚነግረን ረሱል በለህወል መህፉዝ ያለውን ሁሉ እንደሚያውቁ ነው፡፡ ይህ የለየለት ቅጥፈት ብቻ ሳይሆን ክህደት ነው፡፡ በለህወል መህፉዝ ያለውን ሁሉ የሚያውቅ አሏህ ብቻ ነው፡፡ ረሱል የሚያውቁት ሚስጥር አሏህ ያሳወቃቸውን ብቻ ነው፤ ለዚያውም በጣም ጥቂቱን፡፡ የዚህ የመውሊድ ግጥም አደገኛነቱ መቀጣጠፉ ብቻ አይደለም፣ ረሱልን ከአሏህ እወቀትና ስልጣን ጋር አቻ በማድረግ ወይም በማቀራረብ እሳቸውን በአሏህ ላይ ደርበን እንድንማፀን፣ ከዚያም ቀስ-በቀስ እንድናመልክ የሚያደርግ መሆኑ ነው፡፡
ሙስሊም ወንድሜ፣ ሙስሊም እህቴ ሆይ! መውሊድን ማክበር እንዲህ አይነትም የሽርክ አደጋ ስላለበት ነው እኔ የዲን ወንድማችሁ ፍፁም የማላከብረው፡፡
🚩 ምክንያት ሰባት - መውሊድን ማክበር ለነብዩ ሱና ተቃራኒ መስራት በመሆኑ!
ነብዩ -አለይሂ ሶላቱ ወሰላም- በህይወት ዘመናቸው በነበሩበት ወቅት በአመቱ ውስጥ ያሉትን አብዛኛዎቹን ሰኞ ቀኖች ይፆሙ ነበር፣ “ሰኞ የተወለድኩበት እለት ነው” በማለት፡፡ ስለሆነም ረሱላችን የተወለዱበትን ቀን በተመለከተ ሱናው ሰኞ ቀንን መፆም ብቻ ነው፡፡ በአመት አንዴ መውሊድን ማክበር የዚህን ተቃራኒ መስራት ነው፡፡ ስለሆነም ነብዩ -አለይሂ ሶላቱ ወሰላም- የተወለዱበት ቀን ትዝ የሚለኝ በአመት አንድ ቀን ብቻ ከሆነና ለዚያውም ከሰንጋው ፍሪዳ፣ ከሙክቱ ቅልጥም እየተቋደስኩ ስበላና ስጠጣ፣ በጫት የምርቃና ሀሴት ስዋኝ ብውል ያለምንም ጥያቄ ኢባዳዬ የረሱላችን ሱና ተቃራኒ ከመሆን አያመልጥም፤ ታዲያ ይሄ በምን ስሌት ትርፍ ሊሆን ይችላል፣ ኪሳራ እንጂ፡፡
ሙስሊም ወንድሜ፣ ሙስሊም እህቴ ሆይ! ቢድአ ምን ያህል ተቃራኒውን እንደሚያስሰራ ብቻ ሳይሆን፣ የያዝነውን የጥሜት መንገድ እንዴት አሳምሮ እነደሚያቀርብልን ልብ በሉልኝ፡፡
🚩ምክንያት ስምንት- ከታዘዝናቸው የአምልኮ ተግባራት ያልሰራናቸው እጅግ በርካታ በመሆናቸው!
አንድ ሙስሊም አሏህን መገዛት ያለበት በቁርአንና በሀዲስ በታዘዘው ብቻ ነው፡፡ ከታዘዘው ውጭ ፍፁም መስራት የለበትም፡፡ መስራት የሚችልበት እድል የለም’ ንጂ ቢኖር እንኳን፣ ያልታዘዘውን ከመስራቱ በፊት፣ መጀመሪያ የታዘዛቸውን ተግባራት መከወን አለበት፡፡ ከፈርድ ስራዎች ባሻገር ኢልምን መፈለግ/መማር፤ ጎረቤትን፣ ዘመድንና የታመመን መጠየቅ፤ የተቸገረን መርዳት፤ ትርፍ ፆሞችን (በየሳምንቱ ሰኞና ሀሙስን፣ ከየወሩ ደግሞ 3 ቀኖችን) መፆም፣ ትርፍ ሶላቶችን (ከፈርድ ሶላቶች በፊትና/ወይም በኋላ፣ የሌሊት ሶላቶች) መስገድ፣ በየቀኑ ቁርአን መቅራት… ይህ ሁሉ የኸይር ስራ የሰሪ ያለህ እያለ ነው፤ ይህ ሁሉ የኸይር በር ቧ ብሎ ተከፍቶ የሚገባበትን እየጠበቀ ነው… እኛ ግን የት ነው ያለነው? አጅር ሊያሰጥ ይቅርና ለጀሀነም እሳት የሚዳርግ የቢድአና የሽርክ ተግባር በማደን ላይ አይደለንምን?
ሙስሊም ወንድሜና ሙስሊም እህቴ ሆይ! ከእነዚህ ሁሉ ለዝርዝር ከሚያታክቱ የታዘዝናቸው የኸይር ተግባራት ውስጥ አቅሜ የቻለውን ለመስራት መንደፋደፍን፣ ካልሆነልኝም መተውን እመርጣለሁ፣ ያልታዘዝኩትን ሰርቼ ከአሏህ የማገኘው ደመወዜ ክስረትና ቅጣት ከሚሆን፡፡
ውድ ሙስሊም ወንድሜና ውድ ሙስሊም እህቴ ሆይ!
መውሊድም ሆነ ሌላ ማንኛው ነገር በተለምዶ ሲሰራ ስለቆየ ብቻ የኢስላም አካል ሊሆን አይችልም፡፡ መውሊድም ሆነ ሌላ ማንኛውም ኢባዳ ፣አሏህ ወይም ታማኝ በሆኑት መልእተኛው እስካልታዘዘ ድረስ፣ ውድቅ መሆኑና ሰሪዎቹን በአኼራ ለኪሳ መዳረጉ አይቀሬ ነው፡፡
«የአሏህን ትዕዛዝ አከብራለሁ» የሚል ሙስሊም፣ አሏህ ፍፁም ያላዘዘውን መውሊድን ማክበር የለበትም፡፡ መልዕክተኛውን -አለይሂ ሶላቱ ወሰላም- «እወዳለሁ፣ እከተላለሁ» የሚል ሙስሊም፣ መውሊድን ማክበር የለበትም፣ ይህን እንዲያደርግ አላስተማሩትምና፡፡
ውድ ሙስሊም ወንድሜና ውድ ሙስሊም እህቴ ሆይ! ሳይመሽብን በጊዜ በኢስላም ላይ የተደረቱ መውሊድና መሰሎቹን የቢድአ ተግባራት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመተው፣ ቁርአንና ሀዲስ ወደሚያዙን ተግባራት እንመለስ፡፡
አሏህ ሁላችንንም ቅኑን ጎዳና
ከተመሩት ያድርገን - አሜን!
http://www.nesihaa.com/selamawlidbida01.htm
http://www.biiftuuislaamaa.com/ihtifalmawlid.htm
Ruling regarding celebrating the birthday of the Prophet (sal-Allaahu `alayhe wa sallam)
Question: Is gathering (the people) on the 12th day of Rabee' al-Awwal in remembrance of the birth of the Prophet (sal-Allaahu `alayhe wa sallam) permissible?
Response: Celebrating the birthday of the Messenger (sal-Allaahu `alayhe wa sallam) is an innovation; this is because he (sal-Allaahu `alayhe wa sallam) did not do this himself and nor did he order this to be done, and nor did any of his companions (radhi-yallaahu 'anhum) do this, and they were the most adherent of people in honouring the Messenger (sal-Allaahu `alayhe wa sallam) and following his Sunnah. And all good is in following his guidance, and he (sal-Allaahu `alayhe wa sallam) said:
((Whoever introduces anything into this matter of ours (i.e. Islaam) that which is not from it, will have it rejected)), [Saheeh al-Bukhaaree/2697 and Saheeh Muslim/1718].
And with Allaah lies all success and may Allaah send prayers and salutations upon our Prophet (sal-Allaahu `alayhe wa sallam) and his family and his companions.
The Permanent Committee for Islaamic Research and Fataawa
Head: Shaykh 'Abdul 'Azeez ibn Abdullaah ibn Baaz;
Deputy Head: Shaykh 'Abdur-Razzaaq 'Afeefee;
Member: Shaykh 'Abdullaah ibn Ghudayyaan;
Member: Shaykh 'Abdullaah Ibn Qu'ood
Fataawa al-Lajnah ad-Daa.imah lil-Buhooth al-'Ilmiyyah wal-Iftaa. - Volume 3, Page 30, Question 13, Fatwa No. 5005
...
How can one actualise one's love for the Messenger (sal-Allaahu `alayhe wa sallam)
Question: How can one actualise (their) love for the Messenger (sal-Allaahu `alayhe wa sallam)?
Response: Love of the Messenger (sal-Allaahu `alayhe wa sallam) and love of Allaah (Subhaanahu wa Ta'aala) is actualised by following the Messenger (sal-Allaahu `alayhe wa sallam), and everyone who follows the Messenger (sal-Allaahu `alayhe wa sallam) is more eligible for the love of Allaah and the love of His Messenger. Allaah (Subhaanahu wa Ta'aala) says:
{Say: "If you (really) love Allaah then follow me (Muhammad), Allaah will love you}, [Soorah Aal-'Imraan, Aayah 31].
And the sign of the love of the Messenger (sal-Allaahu `alayhe wa sallam) is that a person inquires about his sunnah and then follows it and does not add nor take anything away from that. Based upon this, then those who innovate in anything related to the Prophet (sal-Allaahu `alayhe wa sallam) and state that this is from their love and honouring of him (the Prophet) then in reality they do not love him and nor honour him. And that is because true love and honouring of him is to follow his sayings and not to add to his Sharee'ah and nor to take away from it.
And indeed whoever desires to innovate in the Sharee'ah of Allaah that which is not from it, then his love of Allaah and His Messenger is limited without doubt, because completeness of manners and honouring is not to extend oneself before Allaah and His Messenger. Allaah (Subhaanahu wa Ta'aala) said:
{O you who believe! Do not put (yourselves) forward before Allaah and His Messenger, and fear Allaah. Verily! Allaah is All-Hearing, All-Knowing. O you who believe! Raise not your voices above the voice of the Prophet, nor speak aloud to him in talk as you speak aloud to one another, lest your deeds may be rendered fruitless while you perceive not}, [Soorah al-Hujuraat, Aayahs 1 and 2].
Shaykh Ibn 'Uthaymeen
Fataawa Noorun 'alad-Darb - Volume 2, Page 522, Question 414
...
Dealing with someone (an innovator) who insists on celebrating the birthday of the Prophet (sal-Allaahu `alayhe wa sallam)
Question: We have a man with us at work who approves of the celebration of the birthday (i.e. the Prophet’s (sal-Allaahu `alayhe wa sallam) birthday), and advocates and insists upon this. Should I abandon him for the Sake of Allaah or not? What should I do? ...and may Allaah reward you with good.
Response: Celebrating the Prophet’s birthday is an innovation, and whoever pursues this (path) is an innovator (mubtadi’) if he insists on doing so and does not accept the (sincere) advice, (rather, choosing to) continue in calling to (celebrating) the birthday and arousing interest in it. (In this case), then, it is obligatory to abandon him since he is an innovator, and it is not permissible to maintain companionship with an innovator.
Shaykh Ibn Fowzaan
Fataawa tata’allaaq bil-Mawlid an-Nabawee - Page 49, Question 11
Al-Muntaqaa min Fataawa al-Fowzaan - Volume 1, Page 184