2. ነብዩ صلى الله عليه وسلم ሰኞን ይፆሙ ነበር:: ሲጠየቁም “ይህ የተወለድኩበት ቁርአንም በእኔ ላይ የተወረደበት ቀን ነው” ብለዋል ይህ ደግሞ ነብዩ صلى الله عليه وسلم የተወለዱበትን ቀን እያከበሩ መሆኑን ይገልፃል ይላሉ፡፡
3 ነብዩ صلى الله عليه وسلم ለራሳቸው አቂቃ አወጡ ተብሎ የተገለፀው ሐዲስ በእርግጥ ሐዲሱ ውዝግብ አለበት፡፡ በርካታ ዑለማዎች ሰነዱ ደካማ እንደሆነ ይገልፃሉ/ ለመረጃነት አይበቃም እንደምትሉትም የሁለተኛው አቂቃ ”መውሊድ ” ቢሆን ኖሮ ለምን ረሱል صلى الله عليه وسلم በየአመቱ አልደጋገሙትም፡፡