One English word which can not be translated with one Amharic word

19 views
Skip to first unread message

Fantaw Tesema

unread,
Oct 30, 2015, 4:13:12 AM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com
ሰላም!
የእንግሊዘኛ አንድ ቃል በአማርኛ አንድ ቃል ሳይተረጎም ሲቀር እንዴት እናድርግ?

Argument የጋራ-እሴት ወይስ የጋራእሴት ወይስ የጋራ እሴት
Database: ውሂብ-ጎታ  ወይስ ውሂብጎታ ወይስ ውሂብ ጎታ
Username: መጠቀሚያ-ስም  ወይስ መጠቀሚያስም  ወይስ መጠቀሚያ ስም
Password: ይለፍ-ቃል  ወይስ ይለፍቃል ወይስ ይለፍ ቃል
ይህን የመሳሰሉ ሌሎች ብዙ ቃላት አሉ።

ከላይ እንደምታዩት አማርኛው አንድ ቃል በሚሆን ጊዜ ዐ/ነገር ውስጥ አደናገሪ ሊያደርግ ይችላል። እነዚህ ቃላት ለብቻቸው ብቻ ሳይሆን ዐ/ነገር ውስጥም አሉ። ሰረዝ ከገባ ግን ስለሚያያይዘው ለመረዳትም ሆነ ምን እንደሆነ የሚቀል ይመስለኛል። ሰረዝ ካልገባ ደግሞ አንዳንድ ጊዜ ዐ/ነገሩ ውስጥ ካሉት ሌሎች ቃላት ጋር ሊያምታታ ይችላል ብዬ እሰጋለሁ። ምን ይመስላችኋል? //ፋተ 

Eyob Fitwi

unread,
Oct 30, 2015, 4:23:30 AM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com
ሠላም ፋንታሁን፣

በግልጽ የተለያዩ የሆኑ ቃላት አንድ ላይ ማድረጉ የሚያስፈልግ አይደለም። ለንባብም አይመችም። የሰረዙ ነገር፣ እንደኔ እንደኔ በቃላቱ መካከል የተለየ የሚያቆራኛቸው ባህሪ ወይም ተፈጥሮ ከሌላቸው በስተቀር ባንጠቀም ይመረጣል እላለሁ። ሰረዝ ማስገባትም የምዕራባውያን ልማድና እኛ ከእሱ የወረስነው ይመስለኛል። ፍጹም አንጠቀም አይደለም የምለው፣ ግን አሳማኝ ምክንያት እየፈለግን እየቆጠብን እንጠቀም ባይ ነኝ። ይህን ካልኩ ዘንዳ ግብረመልሴን እነሆ፦

Argument

በይፋዊ የቃላት መዘገቡ ላይ «ነጋሪ እሴት» ተብሎ ተተርጉሟል። የሚሻለውም ይሄው ነው። Argument ለአንድ ሞዱል ወይም ተመሳሳይ የሆነ ነገር የሚተላለፍ ይዘት ነው፤ ማለትም እሴቱ/እሴቶቹ ምን ምን እንደሆኑ «ይነግረዋል»

Database
የውሂብ ጎታ።

Username
የተጠቃሚ ስም። ቀጥተኛ የሆነ ትርጉም ስላለው እሱን እንጠቀም።

Password
የይለፍ ቃል።

ከሠላምታ ጋር፣
እዮብ
--
You received this message because you are subscribed to the Google Groups "Gnu/Linux Ethiopia" group.
To unsubscribe from this group and stop receiving emails from it, send an email to linux-ethiopi...@googlegroups.com.
For more options, visit https://groups.google.com/d/optout.

Fantaw Tesema

unread,
Oct 30, 2015, 4:57:50 AM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com

አመሰግናለሁ እዮብ!
Argument = ነጋሪ እሴት እርማትና ማብራሪያም ጭምር አመሰግናለሁ።
በተረፈ የእንግሊዘኛው አንዱ ቃል ብቻ አንድ ቦታ ላይ ከሆነ ያለ ሰረዝ ቢተረጎም ምንም አይደለም። ስጋቴ የነበረው ዐ/ነገር በሚሆን ጊዜ አንባቢው/ተጠቃሚው እነዚህን ሁለት ቃላት እንዴት እንደሚያዛምዳቸው ግር ሊለው ይችላል ብዬ ስለሰጋሁ ነው። ከኔ ጀምሮ!

ተነጋግረን አንድ አይነት ወጥ እንዲኖረው መወሰኑ ቆንጆ ነው። እኔም አሁን ሰረዝ ላስገባ አላስገባ እያልኩ የማያስፈልግ ትኩረት ሳልሰጥ ጊዜ እቆጥባለሁ። ቃሉ አንድ እስከሆነ ድረስ የትኛው ቃል ውስጥ ሰረዝ ማስገባት አሳማኝ ምክንያት እንደሚኖር አሁን አላውቅም። አንድ ቃል እስከሆነ ድረስ። እንደሚመስለኝ እናስገባ ወይስ አናስገባ የሚለውን ብንወስን ቆንጆ ነበር!! ለኔ አሳማኝ ምክንያት ነው ብዬ ሰረዝ ባስገባ ለሌላ ሰው ላይጥመው ይችላል። 
መልካም ቀን። //ፋተ

Fantaw Tesema

unread,
Oct 31, 2015, 4:18:34 AM10/31/15
to linux-e...@googlegroups.com
ሰላም!

ከላይ እንደጠቀስኩት፤

" የእንግሊዘኛው አንዱ ቃል ብቻ አንድ ቦታ ላይ ከሆነ ያለ ሰረዝ ቢተረጎም ምንም አይደለም። ስጋቴ የነበረው ዐ/ነገር በሚሆን ጊዜ አንባቢው/ተጠቃሚው እነዚህን ሁለት ቃላት እንዴት እንደሚያዛምዳቸው ግር ሊለው ይችላል ብዬ ስለሰጋሁ ነው። ከኔ ጀምሮ!"
ሌላ ምሳሌ ለመጥቀስ Multimedia የሚለውን ሕብረ ሚዲያ፣ ሕብረሚዲያ እና ሕብረ-ሚድያ የሚሉት አማራጮች አሉን።
1) ሕብረ ሚዲያ፤ ይህ ትርጉም አረፍተ ነገር ውስጥ በሚገባ ጊዜ ተጠቃሚው ከኋላ ወይስ ከፊት ካሉት ቃላት ጋር እንድሚያዛምድ አንዳንድ ጊዜ ሊያስቸግረው ይችላል። 
2) ሕብረሚዲያ፤ በአንድ ላይ መሆኑ ባይከፋም አንባቢውን ሊያሰለቸው ይችላል። ወይም ለመረዳት ሊከብድ ይችላል።
3) ሕብረ-ሚድያ፤ ተጠቃሚው ይህንን ለማወቅና ለማዛመድ ሊቀለው ይችላል። ሰረዝ ስለገባ አማረኛውን ምንም አያደርገውም ብዬ አስባለሁ።

ለአሁን Multimedia ን እንደ ምሳሌ ጠቀስኩ እንጂ ተመሳሳይ ቃላት ብዙ አሉ።
አስባችሁ ምን እንደሚመስላችሁ ብታስረዱ ደስ ይለኛል!
በተረፈ መልካም ሰንበት!! //ፋተ 
Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages