That is fine Belay!
Thanks for the suggestion and attachment. I think we also, in a way have similar way of saying as the English attachment says. In my experience we do not always say ጥሩ፣ በጣም ጥሩ ና እጅግ በጣም ጥሩ as the three examples below:
1) For ex. we say ቆንጆ፣ በጣም ቆንጆ ና ውብ/እጅግ በጣም ቆንጆ። ጥሩ ንግግር፣ በጣም ጥሩ ንግግር ና እጅግ በጣም ጥሩ ንግግር። ጎበዝ > በጣም ጎበዝ > እጅግ በጣም ጎበዝ። ወዘተ።
እዚህ ላይ እጅግ በጣም ከማለት እጅግ ብቻ ማለት ይበቃል?
2) ምሳሌ፤ ጨለማ > ጨለም ያለ > በጣም ጨለማ። ይህ ጥሩ ይመስለኛል። ጥቁር፣ ጠቆር ያለ፣ በጣም ጥቁር እንልስ የለም ወይ?
እዚህ ላይም ይበልጥ ጨለማ፣ ከሁሉም ጨለማ /ወይም/ በጣም ጨለማ፣ እጅግ በጣም ጨለማ ማለት ትክክል አይመስለኝም?
3) On the other hand, I think, we say ትንሽ > አነስ ያለ > በጣም ያነሰ። ትልቅ > ተለቅ ያለ > ከሁሉም ትልቅ። ግዙፍም ይባላል።
ሰፊ > ሰፋ ያለ > ከሁሉም ሰፊ። ጠባብ > ጠበብ ያለ > ከሁሉም ጠባብ።
እነዚህ የመሳሰሉት ላይ ለምሳሌ እጅግ ማለት የቱን ያህል እንደሚስማማና ለማለትም የተለመደ መሆኑ እርግጠኛ አይደለሁም። ምክንያቱም ለምሳሌ በትንሽና በበጣም ትንሽ መካከል የሆነ መጠን መኖር አለበት። ለምሳሌ ልብስ ለመግዛት ስንለካ የመጀመሪያው ከጠበበን "ሰፋ ያለ" ልሞክር እንላለን እንጂ "በጣም ሰፊ" ትክክል አይሆንም። በኔ አስተያየት " xxxx ያለ" የምንለው የተለመደ ይመስለኛል። ብዙ ነገሮችላይ ይገባል።
ለምሳሌ ስለ ሶስት ገመዶች እርዝመት ብናወራ እንኳን አጭሩን ለመተው "ረዘም ያለውን" ምረጥ እንላለን። ረዢሙን ለመተው ደግሞ "አጠር ያለውን" ምረጥ እንላለን። ከሶስቱ በእርዝመት የሚበልጠውን ለመውሰድ ደግሞ "ከሁሉም ረጅሙን" ምረጥ እንላለን። "ከሁሉም" የሚለው የእዮብ ሃሳብ ሲሆን ትክክል ይመስለኛል። "ይበልጥ ረጅም" በሚለው ፋንታ ግን "ረዘም ያለ" ቢሆን የተለመደና የተሻለ ይመስለኛል። የገመዱ ምሳሌ ላይም ይበልጥ ረጅም ወይም ይበልጥ አጭር ካልን እንግዳ ነገር ነው የሚል አስተያየት አለኝ። "ረዘም ያለ" ካልን ግን ቀላልና የተለመደ ይመስለኛል።
እንደምታዩት፤
ሀ) ሶስታችንም የተለያዩ አስተያየቶች አሉን።
ለ) እንግሊዘኛው ማወዳደሪያ ውል እንደሌለው ሁሉ (የበላይ ተያያዥ) አማርኛውም ውል የለውም።
ሐ) ይህንን ጉዳይ ላነሳ የቻልኩት "Wider" ን ለመተርጎም WP ላይ ስላጋጠመኝ ነው። ለጊዜው "ሰፋ ያለ" ብዬ ተርጎሜዋለሁ። ከላይ በምሳሌም እንደጠቀስኩት "ሰፊ፣ ሰፋ ያለ፣ በጣም ሰፊ" ከሚለው ሃሳብ በመነሳት ነው። ከ "በጣም ሰፊ" የሚበልጥ መጠን አለ የሚል ጥያቄ ሊያስነሳ ይችላል። ለማንኛውም በሰፊና በበጣም ሰፊ መካከል የሆነ መጠን መኖር አለበትና ፤ "ሰፊ" ካልን በኋላ "በጣም ሰፊ" ካልን ትክክል መሆኑን እጠራጠራለሁ።
አስተያየት? ምን ይመስላችኋል?