ታዲያስ ሁላችሁም!
ወርድፕሬስ ትርጎማው አሁን 90% ደርሷል። 90% ከደረሰ በኋላ በአረንጓደ ምልክት ይደርገበታል። ጥሩ እየሄደ ነው። 98% አካባቢ እስከሚደርስ አልተረጎምኩም ግን እቀጥላለሁ። እስካሁን ከሄድኩባቸው ቀደም ብየ ልጠይቃችሁ ብየ ነው። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሌላ ተጨማሪ ጥያቄ ይኖረኛል። በተረፈ ጊዜያችሁን ተጠቀሙ።
ትርጎማን በተመለከተ ስታንዳርድ የሚባል ነገር እስካሁን አላየሁም። ምናልባት እየተነጋገርን ስታንዳርዱን እንሰራው ይሆናል!!!
እንዲሁ ለመግለጽ ያህል እንደነገሩ ለመጨረስ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ጨርሼ ነበር። ትልቅ ዋጋ መሰጠት ያለበት ትርጉሙን ለመረዳት ቀላል፣ ግልጽና ለመጠቀም የሚገፋፋ መሆን አለበት ብየ አምናለሁ።
1ኛ) ተያያዡ ሰነድ ላይ አንዳንድ ቃላት ሌላ ቦታ የተተረጎሙት ሳያረኩኝ ሲቀሩና አደናጋሪ ስለሆኑ በተቻለ መጠን በርካታ ነገሮች አገላብጨና ፈልጌ ሰነዱ ላይ የምታዩት አይነት ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ። ብዙ አይደሉም። በዛውም ቀጥያለሁ። ሆኖም ግን የበለጠ ትክክል እንዲሆን አስተያየታችሁን እፈልጋለሁ።
ሌላ ትርጉም የምትሰጡ ከሆነ ከማብራሪያ ጋር ምክንያታችሁን እንደምትገልጹ ተስፋ አለኝ። 2ኛ) ከዚህ በታች ደግሞ ምሳሌ ነው።
አቀማመጣቸው ተቀይሮ የተተረጎሙ ምሳሌወች፤
Your account is now activated. Log in or go back to the homepage. አሁን መለያወ ተቀስቅሷል። ይግቡ ወይም ወደ መነሻ ገጽ ይመለሱ።

Please upgrade WordPress to a current version, or downgrade to version 2.4 of the Akismet plugin.
ወደ ወቅታዊው ስሪት ወርድፕሬስን አሳድግ ወይም ወደ አህክስመት ውታፍ ስሪት 2.4 አሳንስ።.

Akismet has protected your site from %3$s spam comments.
አህክስመት ከ %3$s አይፈለጌ አስተያየቶች ድረገጽወን ተከላክሉወለታል።

msgid "Basics of Rich Editing"
msgstr "መሰረታዊ ምርጫ የበዛበት አጻጻፍ "

msgid "Advanced use of the Rich Editor"
msgstr "የረቀቀ ምርጫ የበዛበት ማደቻ አጠቃቀም "

msgid "Rich Editing Basics"
msgstr "መሰረታዊ ምርጫ ያለበት አጻጻፍ "

msgid "Sorry, that file cannot be edited."
msgstr "ይቅርታ፤ ያ ሰነድ መታደት አይችልም።"

msgid "%s exceeds the maximum upload size for the multi-file uploader when used in your browser."
msgstr "%s የኢንተርኔት ማሰሻወ ጥቅም ላይ በሚውል ጊዜ በርካተ ሰነዶች ጫኙ መጫን ከሚችለው ከፍተኛ መጠን ድንበር ያልፋል።"

3ኛ)
ከዚህ በታች ያሉትስ እንደት ይተርጎሙ? አስተያየት አላችሁ?
Jan_January_abbreviation
Feb_February_abbreviation
Mar_March_abbreviation
Apr_April_abbreviation
Your key has been cleared.
navigate