How to enable reading Amharic on Android

648 views
Skip to first unread message

Belay

unread,
Jan 11, 2012, 4:51:58 PM1/11/12
to Gnu/Linux Ethiopia
Purpose: to place a single font file in in /system/fonts.
To Do: Change permission of /system/fonts, get a Ge'ez font and place
it on sdcard.

My Phone: Motorolla Droid Bionic + rooted + Gingerbread (2.3.4)

Apps: Root Explorer, Root Check Basic

Instruction:
1- Verify you are rooted with Root Check Basic. If you are a shell
person open either adb shell or terminal and issue su -
2- Download any popular Ge'ez font to your sdcard. I create a folder
called fonts in /mnt/sdcard and place my font there. I like Nyala.ttf.
Rename using any file manager you have this font to
"DroidSansFallback.ttf" Some Ge'ez font download sites are:
http://www.filecrop.com/nyala-ttf.html
http://www.punchdown.org/rvb/email/UniGeez.html
3- Open Root Explorer and walk to /system/fonts. On the top right you
see a small white square in it written Mount R/W". Click it. This
changes the permission on the folder to enable writing and the small
white square now toggles to "Mount R/O", that is read only. This is
similar to chmod command. Copy the DroidSansFallback.ttf file in /
system/fonts to /home. I created a folder called fonts in /home and
placed the font under /home/fonts but it is up to you how you organize
your /home folder.

4- Walk to /sdcard/fonts or where you placed your downloaded Ge'ez
font and copy it to /system/fonts. Note that the font
DroidSansFallback.ttf will be overwritten. Allow it. To restore use
the font you placed in your /home/fonts folder. The change is instant.
See if you can read Warka or some amharic intensive site.
5- Reset the permission on /system/fonts folder to read only by
pressing the small white square on the top. After pressing it should
read "Mount R/W".

Basically it is a copy and paste process.

More at:
http://androidforums.com/samsung-galaxy-mini-s5570/439800-how-install-amharic-fonts.html

Next Posting - Typing in Amharic and Tigrigna with Honso MultiLing
Keyboard

Question: Is posting in this forum in English medium preferred over
any Ethiopic languages ? I can see the difficulty with technical terms
if I have to write in Amharic. On the other hand, if written in
Amharic it could reach a wider audience. What is your thought?

tegegne tefera

unread,
Jan 11, 2012, 5:14:16 PM1/11/12
to linux-e...@googlegroups.com
ውድ በላይ
በበኩሌ በኣማርኛ የተጻፈን ነገር ውሃ ሳልፈልግ እውጠዋለሁ። ምናልባት መጻፉ ለመጀመሪያ ጊዜ ትንሽ ሊያስቸግር ይችላል። ነገርግን እያደር እየቀለለ እንደሚሄድ ምንም ጥርጥር የለኝም። ልክ እንደትርጉም ስራ ማለት ነው። እንዳልከው ኣንባቢውም ይበዛል።  የትርጉም ስራ ዋና ዓላማውም ይሄ ነው። እንግሊዘኛን ገረፍ ገረፍ ኣድርገን ያለፍነ የስነመላ ጨለማ ውስጥ እንዳንቀር።

Dawit Habtamu

unread,
Jan 14, 2012, 1:13:21 AM1/14/12
to linux-e...@googlegroups.com
ወድ ፡ በላይና ፡ አቶ ፡ አለቃ!
ይህንን ፡ ድንቅ ፡ ሃሳብ ፡ አጅግ ፡ አደግፈዋለው! እርስዎም ፡ አለቃ ፡ አንዳሉት ፡ ያንባቢዉን ፡ ቁጥር ፡ ይጨምረዋል።
አማርኛ ፡ ለነገሩ ፡ እንደው ፡ ካልፈራነው ፡ በስተቀር፣ ደግ፡ ቋንቋ፡ ነው። ... እኔስ ፡ የኡቡንቱ ፡ አማርኛ ፡ ድጋፍ ፡ አለኝ። ለሌላቸው ፡ ወገኖች ፡ ግን ፡ መላ ፡ ብንፈጥርና ፡ ባገርኛው ፡ ብናወጋ ፡  ልብን ፡ ድየስ ፡ የሚያሰኝ ፡ ሳይሆን ፡ አይቀርም። 

ለጊዜው ፡ ትንሽ ፡ ትንሽ ፡ ብንቀላቅልም ፡ የሊነክሱን ፡ ወሬ ፡ ወዝ ፡ ይሰጠዋል ፡ ባይ ፡ ነኝ።

እስቲ ፡ እናውጋ ፡ .... 

ዳዊት ፡ ነኝ ... ተሃገር ቤት
--
"And we know that all things work together for good to them that love God, to them who are the called according to His purpose." Romans 8:28 KJV

Dawit
dawit....@gmail.com
dawith...@yahoo.com

Twitter: @dawithabtamu
Skype: dawit.habtamu

Dawit Habtamu
P. O. Box 13474
Addis Ababa
Ethiopia


Eyob Fitwi

unread,
Jan 14, 2012, 11:34:37 AM1/14/12
to linux-e...@googlegroups.com
@Belay

Looks like you've took a more 'complicated' way to root your phone.
Mine was much simpler. I simply downloaded SuperOneClick.exe (yes,
that's the catch; you'll have to use Windows. There's an Ubuntu
version but let's face it, we don't want to torture ourselves while a
shortcut is available.) Then you connect you're phone with USB
Debugging enabled. Then launch SOC, select your Android version, and
click root. Mine was that simple. Here's are some links. You might
follow any instructions they may have; mine is a bit rough based on
memory, but trust me - IT'S THAT SIMPLE!!!!

http://forum.xda-developers.com/showthread.php?t=803682
http://shortfuse.org/

To enable Amharic, download Font Installer (or ROM Toolbox; it
includes Font Installer along with some other interesting apps) from
the Android Market. Then tap the funnel symbol at the top and
select/tap 'Fonts found on SD card' (you must copy a Geez font on your
memory card. I advise PowerGeez since it's characters' alignement
doesn't go off). Tap the font you want to enable, and on the menu that
appears, tap install. It will ask you to reboot, say yes.

After the reboot, Voila! እንኳን በአንድሮይድ ላይ ውዱ የግዕዝ ፊደሎቻችን ለማንበብ አበቃዎ!!!

Of course, I might want to try out changing the file systems
permissions. Do you know if you can leave the stock font as the main
font while allowing Amharic characters to be read by any other
available font in the fonts folder, like in computers? Or is only one
font functional at a time?

@Dawit

Thanks Dave. I also have a number of ebooks. The problem is that their
content is so numerous or bulky that you don't where to start. I have
a (hardcover) book that seems the best for beginners. I'll holler at
you guys whenever I need something. And damn I like the recent
activity hike we're having!!

@ Tegegne

I like the idea of networked education. In fact I had some serious
ideas about why not us guys start something big from this small linux
group. I mean something that could eventually catch national headlines
or something. Dave, www.linux-ethiopia.org would just be scratching
the surface.

የአበሻ ወረተኝነታችን አስሮ ካልያዘን በስተቀር እዚህ በትንሹ የጫርነው ነገር እኮ በጣም ትልቅ ቦታ ሊደርስ
እንደሚችል በጣም ይሰማኛል። እንዲያውም አንዳንዴ በአካል ተሰባስበንና ተገናኝተን የሆነ ሐሳቦች ብንለዋወጥና
የሆነች ነገር ማቀጣጠል ብንጀምር እላለሁ። እስቲ እግዚአብሔር ያውቃል...

ደግሞ ልብ ብላችኋል እንዴ? እኛ የኮምፒውተር ቅርቅሮች፣ ወይም በፈረንጅኛው Geek (ቅርቅር ራሴ ነኝ
የፈጠርኳት :-) ) ሆነን ሳለ አማርኛ በቴክኖሎጂ አገኘን ብለን እንዲሁ ለሙድ ወይም ዘና ለማለት በአገርኛ
የምንሞነጫጭረው እኮ የሆነ ስነ ጽሑፋዊ ውበት ያለው ነው እኮ። መውጣት የፈለገው ውስጣችን ሳናስበው ፊት ለፊት
ባለው የማያ ገጻችን ላይ ፊደለ-ዳንኪራው በአሪፉ እያስነካው ነው ያለው። ኧረ በርቱበት!! እንዲያውም እዚህ
የሊኑክስ ተጠቃሚዎች መሰባሰቢያ መድረክ ላይ በላቲን መጻፍ አይፈቀድ!! (ትግርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ጉራጊኛ፣ ወዘተ
ይፈቀዳሉ አይዟችሁ)

እንደገና ለበላይ

ስለቴክኒካዊ ቃላት አንጨነቅ። እንዲያውም እዚሁ ልንፈጥር እንችላለን። እኔም የማውቃቸው አንዳንድ ቃላት አሉ።
ቅድም እንዳደረግሁት እየፈጠረን ወይም የምናውቀው ቴክኒካዊ ቃላት እየጻፈን ፍቺያቸው በቅንፍ ውስጥ ማስቀመጥ
እንችላለን እኮ፣ የምን ስነ ቃል ፈርቶ መሸሽ ነው?

በተረፈ ሌሎች ሐሳቦች ካሏችሁ አምጡት። ይሄ ግዕዝ እናድራው እንጂ።

ሌላ ነገር ደግሞ ተባበሩኝ፣ የሆንሶ ፊደል ሰሌዳ (keyboard) ምንም እንኳን ግዕዝ በአንድሮይድ ስልክ ላይ
ማስቻሉ አሪፍ ቢሆንም የፊደል አዘረጋጉ ግን ትንሽ ያስቸግራል። ገንቢው (the developer) Twitter
(ብዙ ጊዜ የምርት፣ ድርጅቶች፣ ወዘተ. ስም አይተረጎሙም፣ ለዛ ነው) ላይ ስላለ አስተያየት ብንጽፍለት አሪፍ
ነው። የSCIM ፊደል ዝርጋት - ኡቡንቱ ላይ የምንጠቀመው ማለት ነው - እንዲጠቀም ሐሳብ አቅርቤለት ነበር።
እናንተም ተጨመሩና ድምጻችን ጫን እናድርገው። አሪፍ ልጅ ይመስለኛል።

> *"And we know that all things work together for good to them that love God,
> to them who are the called according to His purpose.*" *Romans 8:28* *KJV*

tegegne tefera

unread,
Jan 14, 2012, 2:15:38 PM1/14/12
to linux-e...@googlegroups.com
ለመረጃ ያህል http://www.geez.org/IM/

Dawit Habtamu

unread,
Jan 15, 2012, 12:18:21 AM1/15/12
to linux-e...@googlegroups.com
እሺ! ዕቅድ እናውጣ፤ ማለትም፣ በዚሀ ቀን ይህን እናድርግ ብለን ነገሩን "ኮስታራ" እናድርገው ... እንደ አባቶቻችን! ወይኔ አድዋ! ...  ለምሳሌ፡

1) የተከለሰ (remastered) የኡቡንቱ ወይም ሌላ ሊነክስ ዝርያዎችን ማዘጋጀት፦ ለኢትዮጵያ የሆነ (ቢያንስ አሁን ባለው ደረጃ አማርኛ እሽጎችን (packages)፣ የሙዚቃ/ፊልም ወዘተ ማጫወቻ ነጂዎችን (drivers/codecs)) ጨማምረንበት የተከለሰ (remastered) የኡቡንቱ ወይም ሌላ ሊነክስ ዝርያዎችን ማዘጋጀት ... እኔ ባለፈው አንድ የተሳካ ሙከራ አድርጌያለሁ። እስቲ እናንተም ሃሳብ ጨማምሩና (ማለትም በአዲሱ ክልስ ምስል [image] ላይ እንዲጠቃለሉ ምትፈልጉትን ብታወጉኝ ሞክረን እናሳምረው ባይ ነኝ)።

2) አንድሮይድ ምን ያህል ይሰራበት? ወይስ ይቅርብን? መተርጎም(translation)፣ ማዋጣት (contribution)፣ ወዘተ ... ግን እኛ ካልሰራን ማን ሊሰራ ነው?  በል ጀግና ተነስ/ሽ እንጂ (ጾታዊ እኩልነት እንዳይረሳ ... ሴቶቹ ጀግኖች እህቶቻችን እናዳይከፉብን!)

3) መጽሃፍቶችንና ጠቃሚ ድህረ-ገጾችን መጋራት፣ ብሎም የራሳችንን የተከሸነች፣ ጣት ምታስቆረጥም ድህረ-ገጽ መስራት

4) ኢትዮጵያችንን የሊነክስ ተጠቃሚ ማድረግ! ፡-) እውነት እውነት ዊንዶውስ አያዋጣም! ተራራ ቢመስልም፣ ግን ይቻላል! በበራሪ ወረቀቶች፣ ነጻ ለሃገራችን የተከለሱ የሊነክስ ምስሎችን በሲዲና በዲቪዲ በነጻ ማከፋፈል፣ ቅስቀሳ ማድረግ፣ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አቤቱታ ማቅረብ (የግሎቹ ሳይቀሉ አይቀሩም) ...

5) እስቲ ጨምሩበት ... 

ኢዮቤ፣ በአካል መገናኘቱ ጥሩ ሃሳብ ነው ... በወር አንዴ እንኳን ተገናኝተን ብናወጋ በጣም አሪፍ ይሆናል!!

በሉ እናውራ እስቲ ... 

የናንተው ዳዊት ነኝ። 
--
"And we know that all things work together for good to them that love God, to them who are the called according to His purpose." Romans 8:28 KJV

Eyob Fitwi

unread,
Jan 15, 2012, 3:52:49 PM1/15/12
to linux-e...@googlegroups.com

ዳዊት፣

1) ሰራሁት ያልከው የተከለሰ የኡቡንቱ ዘር አሪፍ ነገር ነው። ምናልባት ስለስኬትህ ትንሽ ተጨማሪ መረጃ ብትሰጠን ሳይሻል አይቀርም።

2) አንድሮይድ እንኳ ሶፍትዌሩ ላይ ብዙ መስራት የምንችል አልመሠለኝም። ለምን ብትል ጉግል ስለሆነ በዋነኝት የያዘው እሱ ከያዘው አቅጣጫ ውጭ ብዙ መሄድ አንችልም፤ ከሱ የፈለቀ ሌላ ዘር እንስራ ካላልን በስተቀር ለምሳሌ እንደነ CyanogenMod ያሉ። ባይሆን ስሪት 4.0 ላይ የአማርኛ ትርጉም ራሱ ጉግል ሊያስገባ ይችላል ሳይባል አልቀረም መሠለኝ። ግን ለኛ የሚስማሙ መተግበሪያዎች (apps) ሰርተን ለተጠቃሚዎች ብናቀርብ ነው ተሳትፏችን ልንጠቀምበት የምንችለው። እንደሚታወቀው በኛ ታሳቢነት ብዙ መተግበሪያዎች አይሰሩም (ጥቂቶች ግን አሉ፣ ለምሳሌ አንድ የአበሻ ቀን መቁጠሪያ የሚያሳይ አለ)። ግን የባሰ ችግር ነው የምለው በተወሰኑ አገራት ያሉ ገንቢዎች ናቸው መተግበሪያዎቻቸውን Android Market መስቀል የሚችሉት። እንደነ Amazon appstore ያለ የራሳችን የመተግበሪያ 'ገበያ' ፈጥረን ኢትዮጵያዊ መተግበሪያዎችን ማሟሟቅ እንችላለን።

3) በጣም ይደገፋል።

4) አላማችን አይደል

ለበላይ፣

የሚገርምህ ነገር AndroJOB ከ androidforums.com ማለት እኔ ነኝ። yagya አሪፍ ምክር ነገር ሰጥቶ ነበር፣ ሌላ ስፈልግ ትንሽ የቀለለ ነገር አግኝቼ ተውኩት እንጂ።

From my Android

tegegne tefera

unread,
Jan 16, 2012, 3:55:10 PM1/16/12
to linux-e...@googlegroups.com
የግኑ/ሊኑክስ ተጠቃሚዎች ግሩፕ/አዲስ አበባ (ግሊተግ/አአ) ወይም በእንግሊዝኛው ምህጻረቃል GLUG/AA ጊዜው የደረሰ ይመስለኛል።
ምን ምን ያስፈልጋል?

በወር ኣንድ ጊዜ(ዛፍ ስርም ቢሆን) መገናኘት የግድ ነው። የወሩ የመጀመሪያ እሁድ ከ8 ሰዓት እስከ 11 (2pm to 5pm) ምን ይመስላችኋል?

https://en.wikipedia.org/wiki/Linux_User_Group



2012/1/15 Eyob Fitwi <eyob....@gmail.com>

Belay

unread,
Jan 17, 2012, 5:25:20 AM1/17/12
to Gnu/Linux Ethiopia
እሺ ወገኖቼ።

ጫወታው ስለደራ ለየቱ መልስ ሰጥቼ የቱን እንደምተው አላወቅሁም ። ሰሚስተሩን ሙሉ ሳያጠና ለነገ ፈተና ዛሪ
ሌሊት በጥናት እንደተጋው ተማሪ ሆንኩ አይደል ። እንግዲህ ጀማው ከየት ልጀምር ?

፩ - ከፊሎቻችን እንደ እኔ አይነቱ ከአገር ውጭ ነው ያለነው ። ስካይፕ ማድረግ ስለማይቻል ፤ ከስብስባችሁ
ወይም ከሴምናር ስትመለሱ የሦስተኛውን ቡና ጀባ ብትሉንሳ? አቦሉንማ ለእናንተ ትተናል።

፪ - እውጭ ያለነው ማሕበራችሁን ለመርዳት የምንሞክርበት መንገድ ብታማክሩንስ ። ከሆነ ጥሩ ካልሆነም ማንን
ይጎዳል ።

፫ - የአንድሮይድ ዘይቤ እና የሊኒክስ ዘይቤ ተመሳሳይ ስለሆነ የአንዱ እውቀት ወደ ሌላው ተሸጋጋሪ ነው ።
በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የብልጥ ሞባይሎች /smart phones/ ብዛት መጠነኛ ይመስለኛል ። አብዛኛዎቹም
ሞባይሎች ከእስር ቤት ያመለጡ /jailbreak = rooted/ ስለሆነ to root or not to root
የሚለው ሼክስፒሪያዊ ጥያቄ ከፍተኛ ሥፍራ የለውም ። እኔ እንደማስበው ሊኑክስን በአገር ቤት ቋንቋዎች ማቅረብ
ቅድምያ ቢሰጠውሳ ። ማለት ትርጉማዊ እና ኪፖርድ የመሳሰሉ ሥራዎች። ከአለቃ ተገኔ ተፈራ እና ከአንዳንዶቻችሁ
ጋር ሆነን የጉግል አማርኛ ግሩብ ላይ ጥሩ ሥራ ጀምረን ነበር ። ያን የመሰለ ሥራ ማፋፋም ደግ ነው እላለሁ ።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ያቀናበረው መዝገበ ቃላትን (excel) ሊንክ በመጥፋቱ ፤ እዚህ ባለሁበት ከተማም
አማርኛ የሜያናግረኝ ስለሌለ ይህን አጋጣሚ ተጠቅሜ በዚህ ሰሌዳ ላይ መሞጫጨር ጀመርኩ ።
፬- አንድሮይድን በሚመለከት በእነ ኢዮብ ፍትዊ አበረታችነት የሞባይሌ አስተዳዳሪ /root/ በመሆን የአማርኛ
ፊደላትን ማንበብ ቻልኩ ። ይህ በጣም አስፈላጊ ነበር። ሆኖም የ Honso Multiling keyboard ሁለት
ነገር ስለጎደለው በጣም ካላስፈለገ በስተቀር ላልጠቀምበት ወስኛለሁ ። ይኽውም
ሀ- ያለሁበት ሥራ የታይፕ ፍጥነትን ይጠይቃል ። ጥቃቅን በመሆናቸው በሞባይሌ ኪቦርድ ፊደሎችን አንድ በአንድ
መምታት ያስቸግራል። ስለሆነም ብዙ የብልጥ ሞባይል ተጠቃሚዎች የሚጠቀሙት Swype የተባለ የታይፕ አጻጻፍ ዘዴ
ነው። በትንንሽ ልምምድ ከ100 ቃላት በላይ በደቂቃ መጻፍ ይቻላል ። Honso Multiling keyboard
ይህንን አይደግፍም ። ስለ Swype እዚህ ይመልከቱ ፤
http://www.youtube.com/watch?v=2xA64e3Txe8
http://www.youtube.com/watch?v=WAh-FqEizi4

ለ - ሆኖም Swype ን መጠቀም ላልፈለገ ሰው የሆንሶ ኪቦርድ ደስ የሜል ነው ። እንድያውም SERA Ge'ez
http://www.geez.org/IM/ ላይ እንዲለወጥ የምፈልገውን ይህ የቻይና ሰውየ (Honso)
አስተካክሎታል ። SERA ሳድስ ፊደላትን መሠረት ያደርጋል (እንደ ላቲኑ) ። ሆኖም ሳድስ ፊደላት በብዛት
አነስተኛ ከመሆናቸውም በላይ በግዕዝ ነክ ቋንቋዎች ላይ እንደ ግዕዙ የመጀመርያ ፊደል ሉዓላዊነት የላቸውም ።
አንድ ሙሉ የግዕዝ ግሥ ዝርዝርን የያዘ መጽሐፍ ካዕብን ፤ ሣልስን ፤ ራብዕን ፤ ... ወዘተ ሳይነካ በግዕዙ
ብቻ ሊጻፍ ይቻላል ።

ምሳሌ ፡ 1-ሀለወ ፤2-ሀከከ ፤ 3-ሀከየ ፤ 4-ሀወከ ፤ 5-ሀየየ ፤ 6-ሀደየ ፤ 7-ሀፐለ ፤ 8-ለሀበ
፤ 9-ለሐሐ ፤ 10-ለሐጸ ፤ 11-ለመደ ፤ 12-ለመጸ (1)፤ 13-ለመጸ(2) ፤ 14-ለቀወ ፤.15-
ለበበ ፤ 16-ለበወ ፤ 17-ለበየ ፤ 18-ለበጠ ፤ 19-ለተመ ፤ 20-ለተተ፤

ትርጉም በአማርኛ ። 1-ኖረ ፤ 2-አከከ ፤ 3-ሰነፈ ፤ 4-አወከ ፤ 5-ችላ አለ ፤ 6- አሳረረ ፤ 7-ልብስ
አጠበ 8- አጋየ ፤ 9-አለስለሰ (moisture) ፤ 10-ላጠ ፡ 11-ለመደ ፤ 12- ለስላሳ ሆነ 13-
ቆማጣ ሆነ ፤ 14-አፉን ከፈተ /yawn/ ; 15- ብልሕ ሆነ /አስተዋይነትን/ ፤ 16- ልቡናዊ ሆነ /
አዋቂነትን/ ፤ 17- ልበ ቢስ ሆነ /ጅልነትን/ ፤ 18- ለበጠ /overlay with coating/ 19-
ለተመ /አጋጨ/ ፤ 20-ተንተባተበ /stammer/ ::

በግዕዙም ሆነ በአማርኛው የግዕዝ (የመጀምርያው) ፊደላት በርከት ስለሚሉ ቅድምያ እነሱን ብናሰፍር የታይፕ
ፍጥነታችንን ይጨምረዋል እላላሁ ።

የHonso ን ፈደል ዝርጋታ በእዚህ አቀራረቡ ባመሰግነውም አምስተኛውን ፊደል ከስድስተኛው ፊደል ጋር በማቀያየሩ
ለመጠቀም ከብዶኛል ። ከሁሉም በላይ ያልወደድኩት Swype የመሰለ ጥበብ ከጣቶቼ መለየት ሰለማልፈልግ ነው ።

፭ - @ኢዮብ ስለ ሩት ማድረግ ያመጣኽው ዘዴ ጥሩ ነው ። አመሰግናለሁ ። ምን አይነት አንድሮይድ version
እንደምትጠቀም ብትገልጽ የአንተ አይነት ለሌላችው ሌላ አማራጭ መፈለግ ይቻላል ። እኔም ሆነ አንተ ሁለት ነገር
አስፈልጎናል ። Windows driver and Dan Rosenburg 's (ደራሲው) executible to
bypass the vendor lock and give us root access (jailbreak). I am
currently running in unroot mode. I thought, just in case Verizon
wants to dump a new version it would be good to unroot or refuse ROM
updates until you unroot. I am running Gingerbread 2.3.4 and you?

ዛሪ ሳነባቸው የነበሩትን ገጾች በመተው ልሰናበታችሁ።
ሀ-
የጥበብ መጀመርያ ሱን /su - /መፍራት ነው
http://www.linfo.org/su.html
ለ-
Some links on rooting
1- Things you should know about rooting and flashing ClockworkMod
recovery
http://forum.xda-developers.com/showthread.php?t=1297141

2-Droid Bionic root instructions
http://droidmodderx.com/one-click-root-for-any-motorola-device-running-gb/


3- JailBreak with GingerBreak
http://droidmodderx.com/gingerbreak-apk-root-your-gingerbread-device/

4- More on GingerBreak
http://www.sparticusthegrand.com/hacks-and-mods/root-unroot-motorola-droid-x2-how-to/

5- Complaints on Droid Bionic
https://forums.motorola.com/posts/787cd0a088

በላይ።

On Jan 16, 12:55 pm, tegegne tefera <tefera.tege...@gmail.com> wrote:
> የግኑ/ሊኑክስ ተጠቃሚዎች ግሩፕ/አዲስ አበባ (ግሊተግ/አአ) ወይም በእንግሊዝኛው ምህጻረቃል GLUG/AA ጊዜው የደረሰ
> ይመስለኛል።
> ምን ምን ያስፈልጋል?
>
> በወር ኣንድ ጊዜ(ዛፍ ስርም ቢሆን) መገናኘት የግድ ነው። የወሩ የመጀመሪያ እሁድ ከ8 ሰዓት እስከ 11 (2pm to
> 5pm) ምን ይመስላችኋል?
>
> https://en.wikipedia.org/wiki/Linux_User_Group
>

> 2012/1/15 Eyob Fitwi <eyob.fi...@gmail.com>


>
>
>
> > ዳዊት፣
>
> > 1) ሰራሁት ያልከው የተከለሰ የኡቡንቱ ዘር አሪፍ ነገር ነው። ምናልባት ስለስኬትህ ትንሽ ተጨማሪ መረጃ ብትሰጠን
> > ሳይሻል አይቀርም።
>
> > 2) አንድሮይድ እንኳ ሶፍትዌሩ ላይ ብዙ መስራት የምንችል አልመሠለኝም። ለምን ብትል ጉግል ስለሆነ በዋነኝት የያዘው
> > እሱ ከያዘው አቅጣጫ ውጭ ብዙ መሄድ አንችልም፤ ከሱ የፈለቀ ሌላ ዘር እንስራ ካላልን በስተቀር ለምሳሌ እንደነ
> > CyanogenMod ያሉ። ባይሆን ስሪት 4.0 ላይ የአማርኛ ትርጉም ራሱ ጉግል ሊያስገባ ይችላል ሳይባል አልቀረም
> > መሠለኝ። ግን ለኛ የሚስማሙ መተግበሪያዎች (apps) ሰርተን ለተጠቃሚዎች ብናቀርብ ነው ተሳትፏችን ልንጠቀምበት
> > የምንችለው። እንደሚታወቀው በኛ ታሳቢነት ብዙ መተግበሪያዎች አይሰሩም (ጥቂቶች ግን አሉ፣ ለምሳሌ አንድ የአበሻ ቀን
> > መቁጠሪያ የሚያሳይ አለ)። ግን የባሰ ችግር ነው የምለው በተወሰኑ አገራት ያሉ ገንቢዎች ናቸው መተግበሪያዎቻቸውን
> > Android Market መስቀል የሚችሉት። እንደነ Amazon appstore ያለ የራሳችን የመተግበሪያ 'ገበያ' ፈጥረን
> > ኢትዮጵያዊ መተግበሪያዎችን ማሟሟቅ እንችላለን።
>
> > 3) በጣም ይደገፋል።
>
> > 4) አላማችን አይደል
>
> > ለበላይ፣
>
> > የሚገርምህ ነገር AndroJOB ከ androidforums.com ማለት እኔ ነኝ። yagya አሪፍ ምክር ነገር ሰጥቶ
> > ነበር፣ ሌላ ስፈልግ ትንሽ የቀለለ ነገር አግኝቼ ተውኩት እንጂ።
>
> > From my Android

> > On 15 Jan 2012 08:18, "Dawit Habtamu" <dawit.habt...@gmail.com> wrote:
>
> >> እሺ! ዕቅድ እናውጣ፤ ማለትም፣ በዚሀ ቀን ይህን እናድርግ ብለን ነገሩን "ኮስታራ" እናድርገው ... እንደ
> >> አባቶቻችን! ወይኔ አድዋ! ...  ለምሳሌ፡
>
> >> 1) የተከለሰ (remastered) የኡቡንቱ ወይም ሌላ ሊነክስ ዝርያዎችን ማዘጋጀት፦ ለኢትዮጵያ የሆነ (ቢያንስ
> >> አሁን ባለው ደረጃ አማርኛ እሽጎችን (packages)፣ የሙዚቃ/ፊልም ወዘተ ማጫወቻ ነጂዎችን
> >> (drivers/codecs)) ጨማምረንበት የተከለሰ (remastered) የኡቡንቱ ወይም ሌላ ሊነክስ ዝርያዎችን ማዘጋጀት
> >> ... እኔ ባለፈው አንድ የተሳካ ሙከራ አድርጌያለሁ። እስቲ እናንተም ሃሳብ ጨማምሩና (ማለትም በአዲሱ ክልስ ምስል
> >> [image] ላይ እንዲጠቃለሉ ምትፈልጉትን ብታወጉኝ ሞክረን እናሳምረው ባይ ነኝ)።
>
> >> 2) አንድሮይድ ምን ያህል ይሰራበት? ወይስ ይቅርብን? መተርጎም(translation)፣ ማዋጣት
> >> (contribution)፣ ወዘተ ... ግን እኛ ካልሰራን ማን ሊሰራ ነው?  በል ጀግና ተነስ/ሽ እንጂ (ጾታዊ እኩልነት
> >> እንዳይረሳ ... ሴቶቹ ጀግኖች እህቶቻችን እናዳይከፉብን!)
>
> >> 3) መጽሃፍቶችንና ጠቃሚ ድህረ-ገጾችን መጋራት፣ ብሎም የራሳችንን የተከሸነች፣ ጣት ምታስቆረጥም ድህረ-ገጽ መስራት
>
> >> 4) ኢትዮጵያችንን የሊነክስ ተጠቃሚ ማድረግ! ፡-) እውነት እውነት ዊንዶውስ አያዋጣም! ተራራ ቢመስልም፣ ግን
> >> ይቻላል! በበራሪ ወረቀቶች፣ ነጻ ለሃገራችን የተከለሱ የሊነክስ ምስሎችን በሲዲና በዲቪዲ በነጻ ማከፋፈል፣ ቅስቀሳ
> >> ማድረግ፣ ለከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አቤቱታ ማቅረብ (የግሎቹ ሳይቀሉ አይቀሩም) ...
>
> >> 5) እስቲ ጨምሩበት ...
>
> >> ኢዮቤ፣ በአካል መገናኘቱ ጥሩ ሃሳብ ነው ... በወር አንዴ እንኳን ተገናኝተን ብናወጋ በጣም አሪፍ ይሆናል!!
>
> >> በሉ እናውራ እስቲ ...
>
> >> የናንተው ዳዊት ነኝ።
>
> >> On Sat, Jan 14, 2012 at 10:15 PM, tegegne tefera <

> >> tefera.tege...@gmail.com> wrote:
>
> >>> ለመረጃ ያህልhttp://www.geez.org/IM/

> >>>> or something. Dave,www.linux-ethiopia.orgwould just be scratching


> >>>> the surface.
>
> >>>> የአበሻ ወረተኝነታችን አስሮ ካልያዘን በስተቀር እዚህ በትንሹ የጫርነው ነገር እኮ በጣም ትልቅ ቦታ ሊደርስ
> >>>> እንደሚችል በጣም ይሰማኛል። እንዲያውም አንዳንዴ በአካል ተሰባስበንና ተገናኝተን የሆነ ሐሳቦች ብንለዋወጥና
> >>>> የሆነች ነገር ማቀጣጠል ብንጀምር እላለሁ። እስቲ እግዚአብሔር ያውቃል...
>
> >>>> ደግሞ ልብ ብላችኋል እንዴ? እኛ የኮምፒውተር ቅርቅሮች፣ ወይም በፈረንጅኛው Geek (ቅርቅር ራሴ ነኝ
> >>>> የፈጠርኳት :-) ) ሆነን ሳለ አማርኛ በቴክኖሎጂ አገኘን ብለን እንዲሁ ለሙድ ወይም ዘና ለማለት በአገርኛ
> >>>> የምንሞነጫጭረው እኮ የሆነ ስነ ጽሑፋዊ ውበት ያለው ነው እኮ። መውጣት የፈለገው ውስጣችን ሳናስበው ፊት ለፊት
> >>>> ባለው የማያ ገጻችን ላይ ፊደለ-ዳንኪራው በአሪፉ እያስነካው ነው ያለው። ኧረ በርቱበት!! እንዲያውም እዚህ
> >>>> የሊኑክስ ተጠቃሚዎች መሰባሰቢያ መድረክ ላይ በላቲን መጻፍ አይፈቀድ!! (ትግርኛ፣ ኦሮምኛ፣ ጉራጊኛ፣ ወዘተ
> >>>> ይፈቀዳሉ አይዟችሁ)
>
> >>>> እንደገና ለበላይ
>
> >>>> ስለቴክኒካዊ ቃላት አንጨነቅ። እንዲያውም እዚሁ ልንፈጥር እንችላለን። እኔም የማውቃቸው አንዳንድ ቃላት አሉ።
> >>>> ቅድም እንዳደረግሁት እየፈጠረን ወይም የምናውቀው ቴክኒካዊ ቃላት እየጻፈን ፍቺያቸው በቅንፍ ውስጥ ማስቀመጥ
> >>>> እንችላለን እኮ፣ የምን ስነ ቃል ፈርቶ መሸሽ ነው?
>
> >>>> በተረፈ ሌሎች ሐሳቦች ካሏችሁ አምጡት። ይሄ ግዕዝ እናድራው እንጂ።
>
> >>>> ሌላ ነገር ደግሞ ተባበሩኝ፣ የሆንሶ ፊደል ሰሌዳ (keyboard) ምንም እንኳን ግዕዝ በአንድሮይድ ስልክ ላይ
> >>>> ማስቻሉ አሪፍ ቢሆንም የፊደል አዘረጋጉ ግን ትንሽ ያስቸግራል። ገንቢው (the developer) Twitter
> >>>> (ብዙ ጊዜ የምርት፣ ድርጅቶች፣ ወዘተ. ስም
>

> ...
>
> read more »

tegegne tefera

unread,
Jan 17, 2012, 6:42:46 AM1/17/12
to linux-e...@googlegroups.com
ሰላም በላይ

ርግጠኛ ነህ የግዕዝ ፊደላት ከሳድሱ እንደሚበልጡ? እስቲ የኣማርኛ መጽሐፍ (መጽሐፍ ቅዱስ ለምሳሌ) ውሰድና ኣንድ ምዕራፍ ውስጥ ያሉትን ፊደሎች ቁጠራቸው። ወደ ግማሽ የሚጠጉት ሳድስ ሆነው ታገኛቸዋለህ። ከዚህ በላይ በጻፍኩት ኣረፍተነገር ውስጥ እንኳን ለምሳሌ ከ 104 ፊደሎች ውስጥ 43 ሳድስ ሲሆን ግዕዞቹት 25 ብቻ ናቸው። ይህ ውስጠ ታዋቂ የሆኑትን ሳይጨምር ማለት ነው። ውስጠ ታዋቂ ምንድነው ብለህ ጠቅኸኝ መሰል። ኣዎ። እንደምታውቀው በተለምዶ ኣማርኛ ሲጻፍ ኣንድ ቃል ሲጠብቅና ሲላላ ሁለት ኣይነት ኣጠራርና ትርጉም ሊኖረው ይችላል። ለምሳሌ "በላ" ምግብ ስለመብላትና "በላ" "ተናገር እንጂ" ለማለት እንደማለት ማለት ነው። የምግብ መብላቱን "በላ" በድምብ ብታዳምጠው በመሃከሉ የተደበቀ ሳድስ ሸጉጦ ይዟል። ይኸውም "በልላ" ያሰኘዋል። ማንኛውም የሚጠብቅ የኣማርኛ ቃል ሳድስ በውስጡ ደብቆ ይዟል። (የኣማርኛ ክፍል ኣደረግኸው እንዳትሉኝ)።

በተረፈ መገናኘቱ መቼም በተለይ ፕሮግራሞችን ለመለዋወጥና ለመረዳዳት ጥቅሙ ኣሌ የማይባል ነው። ሻይ ቤትም ውስጥ ቢሆን ማለት ነው። ዋናው ጊዜና ቦታውን ወስኖ (ቦታው እንደኣመቺነቱ ሊለዋወጥ ይችላል) ያንን የሚፈልግ ሁሉ ኣስሊ መኪናውን ይዞ (የሌለውም ባዶ እጁን) እንዲመጣ መጥራት ነው። እንደ ትልቅ ነገር ባይቆጠር ጠቃሚነት አለው። እንደ ትልቅ የተቆጠሩ ነገሮች አይሳኩም። ኣንድ ነገር ቀስመን እንደምንሄድ ግን ርግጠኛ መሆን እንችላለን። የትርጉሙም ስራ እዚያ ላይ ሊሰራ ይችላል። ኣንድ ሰው ብቻውን ሆኖ ቀን ሙሉ ከሚሰራ ሁለት ወይ ሶስት ሆነው ኣንድ ላይ ኣንድ ሰዓት ቢሰሩ የበለጥ ውጤትና ጥራት እንደሚኖረው ኣትጠራጠር።
የዚህ አይነቱ የትርጉም አሰራር በነጻ ሥነ-ሥስነገር (free software) ዓለም የትርጉም ማራቶን (translation marathon) ተብሎ ይጥራል። ለምሳሌ የእሳት ቀበሮን (firefox) መተርጎም ቢያስፈልግ 5 ሰዎች በሁለት ወር ሁለት ጊዜ ቢገናኙና ለ2 ስዓት ቢሰሩ ይጨርሱታል። አንድ ሰው ግን አመትም አይበቃውም።

12/1/17 Belay <belayt...@gmail.com>

Belay Tekalign

unread,
Jan 17, 2012, 1:25:19 PM1/17/12
to linux-e...@googlegroups.com
I stand corrected Aleqa Tegene
Order Percen
ግዕዝ 28%
ካዕብ 6%
ሳልስ 5%
ራብዕ 15%
ሐምስ 1%
ሳድስ 43%
ሳብዕ 3%
 በገዛ እጄ የፃፍኩት ገጽ ከዳኝ ። አንደኛ ሳድስ ሁለተኛ ግዕዝ ናቸው ።
 
በሌላ በኩል ዘመናዊው ኪቦርድ  በግራ የሚጽፉ ሰዎች በቀኝ እጃቸው ከሚጽፉት የበለጠ ፍጥነት ሊኖራቸው ይችላል ይላል ይህ ውኪፕድያ ። ምን ይመስልሀል? ብዙ የአማርኛ ፊደላት በቀኝ ወይስ በግራ ናቸው? http://en.wikipedia.org/wiki/QWERTY
 In the QWERTY layout (standard keyboard) many more words can be spelled using only the left hand than the right hand. In fact, thousands of English words can be spelled using only the left hand, while only a couple of hundred words can be typed using only the right hand. In addition, most typing strokes are done with the left hand in the QWERTY layout. This is helpful for left-handed people but to the disadvantage of right-handed people.[16]
 
ከአለም ቋንቋ ውስጥ በፍጥነት ለመጻፍ የሚቻለው በኮርያ ቋንቋ ነው ። ምክንያቱም the vowels live on the right while the consonants are on the left side of the keyboard. This is the most beautiful script in the world.
 
Aleqa Tegene:
Can you point me to  the excel file that Addis University published a while ago. We used to have a link at Google Amharic. I think that link is either dead or I could not find it. Any other Amharic resources would be helpful, including books.
 
Belay
2012/1/17 tegegne tefera <tefera....@gmail.com>
ሥነ ፍጥረት - Sine Fitret.jpg

tegegne tefera

unread,
Jan 17, 2012, 4:15:10 PM1/17/12
to linux-e...@googlegroups.com
የተክኖሎጂ ኮሚሽኑ መዝገበቃላት ከመነሳቱ በፊት ወደዚህ ተዛውሯል። የ exel ፋይሉ የሆነ ቦታ ነበረኝ። ግን ኣሁን ያለሁት እቤት ስላልሆነ ማግኘት ኣልችልም። እዚያ ያሉት ቃላት ሁሉ ከዚህ በታች ኣሉልህ።

https://am.wiktionary.org/wiki/Comp_Glossary_A

2012/1/17 Belay Tekalign <belayt...@gmail.com>

tegegne tefera

unread,
Jan 17, 2012, 4:19:57 PM1/17/12
to linux-e...@googlegroups.com
በነገራችን ላይ ኮሪያንኛ ማንበብ በ 1 ሰዓት ከ 43 ደቂቃ ውስጥ መማር እንደምትችል ታውቃለህ። 43ቷን ደቂቃ ነገር ላሳምር ብዬ ነው። እኔ ኣንብቤ ነበር ግን ምን እንዳልኩ ኣላወቅሁም እንጂ።


2012/1/17 tegegne tefera <tefera....@gmail.com>

Eyob Fitwi

unread,
Jan 20, 2012, 3:09:58 AM1/20/12
to linux-e...@googlegroups.com

አዲሱ የሆንሶ የፊደል ሠሌዳ ሞክራችሁታል? ቀደም ሲል ከነበረው ሙሉ የፊደል ዝርጋታው እጅግ በጣም የተሻለ ነው። እንዲያውም ቀጥሎ ለሚመጣው ስሪት አንድ የምስራች አለኝ (በላይን ወደሱ ሊያስመልሰው የሚችል ሁሉ) — የአማርኛ መዝገበ—ቃላት አካትቶ ይመጣል፣ ያው ስንተይብ ቃላቱን እየተነበየልን ሥራችንን ለማቃለል የሚሞክረው ማለቴ ነው።

From my Android

Eyob Fitwi

unread,
Jan 20, 2012, 3:11:16 AM1/20/12
to linux-e...@googlegroups.com
Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages