መቅዳት ወንጀል ሊሆን ይችላል። መቅዳት እንደሚቻል ማወቅ ወይም ማሳወቅ ወንጀል አይመስለኝም።
ሁሉም የአማርኛ ፊደል ያለው የፊደል ቅርጽ እንግሊዘኛም ስላለው መቀያየር አስፈላጊ አይምስለኝም። abysinica sil ነፃ ነው። ባይሆን ኖሮ ዑቡንቱ ውስጥ መግባት አይችልም ነበር። በአቶ አባስ አላምረው የተሰሩት የዋሸራ የፊደል ቅርጽ ዘሮችም እንደዚሁ ነጻ ናቸው። የዑቡንቱ ሰዎች እንዲጨምሩዋቸው ጠይቄያለሁና ወደፊት ያስገቧቸዋል። እስከዚያ ድረስ ግን ራስህ እያስገባህ መስራት ትችላለህ። ነጻ የሆኑት የፊደል ቅርጾች ከ
http://am.wikipedia.org/wiki/Can%27t_see_the_font%3F ላይ ማምጣት ይቻላል።
በነገራችን ላይ ዑቡንቱ ውስጥ ያሉት የፊደል ቅርጾች ግኖም (ወይም በትክክለኛው አጠራር ኖም) ውስጥ አይደለም ያሉት። ያ ማለት ሸቡንቱ (xbuntu) ከቡንቱ(kbuntu) ም ላይ አሉ ማለት ነው። ዑቡንቱን ለአማርኛ ለምትጠቀሙ ሸቡንቱን ብትጠቀሙ ጥሩ ይመስለኛል። ምክንያቱም ሸፍሲ (xfce) ወደ አማርኛ ተተርጉሞ ስላለቀ (እስካሁን ያለቀው ወደ ዑቡንቱ መጥቶ ላይሆን ይችላል) ሙሉበሙሉ የአማርኛ ሸቡንቱን ማግኝት ስለሚቻል ነው። በእግዚአብሔር ፈቃድ ምናልባት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ በቀጥታ ከሲዲው ላይ ጀምሮ በአማርኛ የምንሰራበት ሁኔታ ሊኖር ይችል ይሆናል። ደራሲዎቹ ያለቁትን ትርጉሞች ሁሉ ለሚቀጥለው የዑቡንቱ ዝርያዎች ለማስገባት ቃል ገብተዋል። ከአሁን ጀምሮ እስከ 6 ወር ማለት ነው። እኛም እስከዚያ ድረስ ያሉትን ፕሮግራሞች በተቻለ መጠን ተርጉመን መጨረስ ብንችል ጥሩ ነው።