Groups
Groups
Sign in
Groups
Groups
EthioMuslims - ኢትዮሙስሊሞች
Conversations
About
Send feedback
Help
… ደሞ ሐሰን ታጁን ተኮሱብን! …
33 views
Skip to first unread message
abumo...@gmail.com
unread,
Apr 6, 2013, 3:56:54 AM
4/6/13
Reply to author
Sign in to reply to author
Forward
Sign in to forward
Delete
You do not have permission to delete messages in this group
Copy link
Report message
Show original message
Either email addresses are anonymous for this group or you need the view member email addresses permission to view the original message
to ethiopia...@googlegroups.com
~~~ * * * … ደሞ ሐሰን ታጁን ተኮሱብን! … *** ~~~
በወንድም ሐሰን ታጁ እንደተጻፈ እና ከህዝበ ሙስሊሙ የሃይማኖት ነፃነትን የማስከበር ሰላማዊ ትግል ጋር በተያያዘ “ተቃውሞው ይቀጥል ወይስ አይቀጥል?” በሚል ጥያቄ ላይ የተንጠለጠለ አንድ ጽሑፍ ለውይይት በሚል ተሰራጭቷል፡፡ ጽሑፉ በሁለት ወገኖች የሚንፀባረቁ የተለያዩ አቋሞችን ከፈተሸ በኋላ ወንድም ሐሰን ታጁ “የያዘውን አቋም” ለማሳየት የሚሞክር ሲኾን፣ እነሆ የህዝበ ሙስሊሙ መነጋገሪያ አጀንዳ እየሆነ ነው፡፡
ምንም እንኳ ጽሑፉ የምንወደውና እጅግ የምናከብረው ወንድማችንን ስም ይዞ አደባባይ ላይ ቢወጣም፣ በግሌ በጽሑፉ የተንፀባረቀው ሐሳብ/አቋም በትክክል የወንድም ሐሰን ታጁ ነው ለማለት አዳግቶኛል፡፡ ወንድም ሐሰን በሐምሌ ወር 2004 ለአዲስ ጉዳይ መጽሔት የሰጠውን ቃለ ምልልስ ያነበበ ሰው፣ ይኸው ወንድማችን ነገሮችን የሚያይበት መነጽር ደርሶ እንዲህ ሊንሻፈፍ እንደማይችል መገንዘብ አይሳነውም፡፡ ያም ሆኖ፣ ይህ ጽሑፍ የእርሱን ስም ይዞ እንዲወጣ ተፈልጓል፡፡ ይህቺ ጨዋታ፣ አያ ኢህአዴግ በአንድ አቋም ዙርያ የተሰባሰበን ጠንካራ ቡድን ወይም የሰዎች ስብስብን ለመሰንጠቅ (ለመከፋፈል) የሚጠቀምባት በጣም ነባርና ታዋቂ ስልቱ ነች፡፡ የህዝበ ሙስሊሙ እንቅስቃሴ ከተጀመረ ወዲህ ኢህአዴግ ሰላማዊ ትግሉን በዚህ ስልት ለማሰናከል ብዙ ጥሯል፡፡ ከዚህ ቀደም ወንድማችንን ዶ/ር ኢድሪስ ሙሐመድን ለዚህ ዓላማ ማስፈፀሚያነት ተኩሶብን … በአላህ ፈቃድ ፈተናውን በድል ተወጥተናል፡፡ በዚያ ሳቢያ ብዙ ወንድሞች ዛሬም በዶ/ር ኢድሪስ ላይ ከቅሬታቸው ጋር ይኖራሉ፡፡ … በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደሰማነውም፣ በእሥር ላይ የሚገኙ የህዝበ ሙስሊሙ ኮሚቴ አባላትንም በተናጠል በማነጋገር ለመከፋፈል ከማዕከላዊ እስከ ቃሊቲ ያልተሞከረ ሙከራ የለም፡፡ በሐቅ እና በመርኅ ላይ የቆሙት ጀግኖቹ የህዝብ ልጆች ግን ቅንጣት ታህል ሸብረክ አላሉም፡፡ … አሁን ደግሞ ወንድም ሐሰን ታጁ ተተኩሶብናል፡፡ …
… እነሆ አሁንም የከሸፈ ጨዋታቸውን ዳግም በህዝቡ ላይ ለመሞከር የምንወደውና የምናከብረውን የወንድም ሐሰን ታጁን ስም (ለምድ) ለብሰው መጥተዋል፡፡ የእርሱን ስም ይዞ በመካከላችን የተሰራጨው ጽሑፍ ይዘቱም ሆነ አቀራረቡ ፍፁም ዘመምተኛ (biased) ከመሆኑም በላይ፣ የማንን ሐሳብ፣ ፍላጎትና አቋም በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ለመርጨት እንዳለመ በጣም ግልጽ ነው፡፡ ጽሑፉ ተጀምሮ እስኪጨረስ መንግሥት መንግሥት፣ ኢህአዴግ ኢህአዴግ፣ “ዶክተር ዶክተር”፣ ደግሞም ሼም የለሽ … ሼም የለሽ ይሸታል፡፡ “ሼም የለሽ”ን ታውቋት የለ?! …
እኔ በግሌ ይህ ጽሑፍ ከወንድም ሐሰን ታጁ ብሩኅ አዕምሮ የመነጨ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ነገር ግን ወንድም ሐሰን ታጁ “እውን ይህ ጽሑፍ ያንተ ነውን?” ተብሎ ቢጠየቅ፣ “አዎን የእኔ ነው” እንደሚል አልጠራጠርም፡፡ ወንድም ሐሰን ይህ ጽሑፍ በእርሱ ስም መውጣቱን እንዳይቃወም ብቻ ሳይሆን፣ በምንም መልኩ እንዳያስተባብል ከፍተኛ ጫና ሳይደረግበት እንዳልቀረ በብርቱ እጠረጥራለሁ፡፡ አንድ ወንድሜ ወንድም ሐሰን ሜክሲኮ አደባባይ እሚገኘው ፌደራል ፖሊስ ጽ/ቤት ሲገባ ከአንድ ሁለቴ ታይቷል ብሎኛል፡፡ እናም እንኳን በጽሑፉ ላይ የሰፈረውን ሐሳብ ማስተባበል፣ “ትንፍሽ ያልክ እንደሆን …” ተብሎ ሳይስፈራራ የቀረ አይመስለኝም፡፡ … ይህ ግን ግምት ነው፤ … ‹ብሩኅ አዕምሮና የጠራ ምልከታ ያለው ወንድማችን ሐሰን እንዲህ የወረደ፣ የተፋለሰና እርስ በእርስ የሚጣረስ ጽሔፍ ለውይይት ሊያቀርብ አይችልም› ከሚል እምነት የመነጨ ግምት፡፡ …
የተወደዳችሁ ወንድም እና እህቶቼ ሆይ፣
የወንድም ሐሰን ታጁን ስም ይዞ “ለውይይት” በሚል የተሰራጨው ጽሑፍ በማንም ተጻፈ በማን፣ ትኩረታችንን በጽሑፉ ይዘት ላይ ብቻ እንድናደርግ፣ በምንም ዓይነት የጽሑፉ አቅራቢ ተደርጎ በቀረበው ሰው ላይ ጣታችንን እንዳንቀስር፣ ከምላሳችን ክፉ ኃይለ ቃል እንዳይወጣ በአላህ ስም አደራ እላችኋለሁ፡፡ ለመተቸትም ሆነ ለማሞገስ (የሚሞገስ ነገር ካለው) በጽሑፉ ውስጥ የቀረቡት “ሐሳቦች” በራሳቸው ከበቂ በላይ ናቸው፡፡ በእኔ እምነት ጽሑፉ የሃይማኖት ነፃነቱን ለማስከበር ዓለምን ባስደመመ የትግል ስልት እየታገለ ለሚገኘው ህዝበ ሙስሊም የሚያሳየው ንቀት በጣም የሚያሳዝንና የሚያበሳጭ ነው እንደ አዲስ ዘመን፣ እንደ ኢቲቪ፣ እንደ ዛሚ ኤፍ. ኤም ወዘተ.፡፡ [ይህ በአላህ ፈቃድ ሰፋ ባለ ተከታታይ ወይ አንድ ወጥ ጽሑፍ በዝርዝር የምዳስሰው ጉዳይ ነው፡፡] ጽሑፉ በኢ ፍትኃዊው እና በመርኅ አልባው የመንግሥት ፕሮፖጋንዳ ክፉኛ የታጠነ በመሆኑ ተጀምሮ እስኪጨረስ በተቃርኖ፣ በአሳፋሪ አመክንዮ እና በአስቂኝ ትንተና የታጨቀ ነው፡፡ …
በዚህ እንቶ ፈንቶ ጽሑፍ መነሾነት በምንወደውና በምናከብረው ወንድማችን በዑስታዝ ሐሰን ታጁ ላይ ጣታችንን የምንቀስርበት አንዳችም ምክንያት የለም፡፡ ምናልባት በዚህ የወረደና የዘቀጠ ጽሑፍ አናት ላይ የምርጡ ወንድማችን ስም የሠፈረው ጽሑፉ በሚያሳድርብን ቁጣ ገንፍለን ወንድማችንን በኃይለ-ቃል እንድንወርፈውና በዚህም መነሾ እርስ በእርሳችን በቃላት ጦርነት ውስጥ እንድንገባ፣ የቃላት ጦርነቱም የመከፋፈላችን መንስዔ እንዲሆን ታስቦ ሊሆን ይችላል፡፡ ስለዚህም የተወደዳችሁ ወንድሞችና እህቶቼ ከዚህ ቀደም እንዳለፍናቸው በርካታ ፊትናዎች ሁሉ ይህንንም ፊተና ከኢስላማዊ አደብ ሳንወጣ በብስለት፣ በእርጋታ እና በጥበብ እናልፈው ዘንድ በድጋሚ አደራ እላችኋለሁ፡፡
መልዕክቴን የምደመድመው ለውድ ወንድሜ ለዑስታዝ ሐሰን ታጁ ያለኝን ልባዊ ወንድማዊ ፍቅርና አክብሮት በድጋሚ በመግለጽ ነው፡፡ ለወንድም ሐሰን ያለኝ ወንድማዊ ፍቅርና አክብሮት “በመንታ መንገድ ላይ ነን፡ የቱን አቅጣጫ እንከተል?” በሚል ርዕስ በእርሱ ስም በቀረበው ጽሑፍ ምክንያት አንዲት ጋት እንደማይቀንስ እነሆ በፌስቡክ አደባባይ አረጋግጥለታለሁ፡፡ አኺ፣ ከልቤ እወድሃለሁ፡፡ ለኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የዲን እውቀት መጎልበት ላበረከትከውና እያበረከትህ ላለኸው ወደር የለሽ አስተዋጽኦም አላህ (ሱ.ወ.) ኸይር ጀዛዕህን እንዲከፍልህ እለምነዋለሁ፡፡…
ውዴታና አክብሮቴ እንደተጠበቀ ሆኖ ግን፣ ይህችን የአንተን ስም ይዛ የወጣች፣ ይህቺን “ሰላማዊ ተቃውሞው ይቀጥል” ብለን የምናስበው እኛ ህጻናቶቹ፣ አፍላ ጎረምሶቹና ጃሂሎቹ መሆናችንን ልትነግረን የምትቃጣ ጽሑፍ፣ ይህቺን “ኧረ መንግሥት በጅምላ ይጨፈጭፋችኋል፤ ይህን ተቃውሞ አቁሙ!” በማለት እንደ ህጻን ልጅ በ“ጅቡ መጣብህ” ልታስፈራራን ዓልማ በስምህ የተበተነች ጽሑፍ ግን … በአላህ እገዛ፣ ጭምብሏን ገላልጠን ሌጣዋን እስክናስቀራት ድረስ እኔም ሆንኩ ወንድሞቼና እህቶቼ በዓይናችን እንቅልፍ እንደማይዞር ላረጋግጥልህ እወዳለሁ፡፡ … አንድም ህግ ሳይተላለፉ፣ አንድም ጥፋት ሳይፈጽሙ በጡንቸኛ መንግስት ወህኒ ተከርችሞባቸው የሚገኙት እኒያ አንደበተ ርቱዕ፣ እኒያ አንደበተ ጣፋጭ ወንድሞቻችን አንደበታቸው በግፍ በተለጎመበት በዚህ ቅፅበት እኛ አንደበት እንሆናቸው ዘንድ ኅሊናችን ያስገድደናል፡፡ በአላህ ፈቃድ እና በእርሱም እገዛ ይህን የኅሊና ዕዳ እንከፍላለን፡፡ ኢንሻአላህ!
https://www.facebook.com/groups/ethiopianmuslims/permalink/10151329943547687/
Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages