እምነታችንን ኢስላምን
ለመበረዝ የሁዳዎች ካሰማሩዋቸው የአህባሽ ጉሩፕ ተጠንቀቁ
በአላህ ስም እጅግ ሩህሩህ ና አዛኝ በሆነዉ
አህባሾች እነማን ናቸው ፡- የአህባሽን መንገድ የመሰረተው አብደላህ አል-ሐረሪ የተባለ ግለሰብ ነው ፡፡ ይህ ግለሰብ ሐረር ተወልዶ ያደገ ሲሆን ባንድ ወቅት የዲን ትምህርት ለመማር ወደ ወሎ በሄደበት ጊዜ ከታዋቂዉ ሙፈቲህ ሙሀመድ ሲራጅ አል ኣኒ አልጀበርቲ ጋር ተጋጭቶ
ከሳቸው ተከትሎ መስገድ አይበቃም በማለቱ በደረሶች መሀል ፊትና ቀስቅሶ በተባረረበት ወቅት ሙፍቲው እሱን በተመለከተ እንዲህ ማለታቸው ይታወሳል (ይህ ሰዉ ለወደፊቱ የፊትና ሰው ይሆናል) እንዳሉትም አልቀረም አይደለም ለኢትዮጵያ ሙሰሊሞች ለመላዉ አለም ሙሰሊም ፊትና ሆኖዋል፡፡ ፊትናዉን አንድ ብሎ የጀመረዉ የሀይለ ስላሴ መንግስት ቀኝ
እጅ በመሆን ነበር፡፡ አብደላህ አል-ሐረሪ ሀይለ ስላሴ ሀረረን እንዲያስተዳድር ከሾመው
የሃይለስላሴ አማች አንደርጌ ጋር ሆኖ ከሱ የፊትና አመለካከት ያልተስማሙትን ሙሰሊሞች ወሃቢያ ናቸው የሚል ታርጋ ለጥፎላቸው ዓሊሞችን ሲያሳስር፣ መብትና እኩልነትን የሚጠይቁ ሙስሊሞችን ሲያስጠቃ እና ሲሰልል ቆየ ፡፡ እ.ኤ.አ በ1940 ላይ በሐረር የቁርኣን ሂፍዝ ማዕከል መምህራንን አሳስሮ መርከዙንና እስላማዊ ድርጅታቸውን አዘግቶ የመርከዙን ዳይሬክተር ሼህ ኢብራሂም ሀሰን ሻሽን ለ23 ዓመታት እስር አስረፈደባቸው፡፡ አብደላህ አል-ሐረሪ በወቅቱ የፈጠረው ፊትና ‹‹ፊትነተል ኩሉብ›› ተብሎ ይታወቃል፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት በሀደሬ ሰፈር ሙስሊሙን ሲያጋጭ ቆይቶ በ1948 ወደ እስራኤል ተጓዘ፡፡ ለ1ዓመት በዚያ ቆይቶ በ1949 ወደ ሶሪያ ገባ፡፡ ከዚያም በ1950 ወደ ሊባኖስ ተጓዘ፡፡ ከአገር ከወጣ በኋላ ከየሁዳዎች ጋር በሚስጢር ይገናኝ ጀመር። ከየሁዳዎች ከፍተኛ ገንዘብ ተመድቦለት እ.አ.አ በ1982 የሊባኖስ የርስ በርሱ ጦርነት ጊዜ ድምፁን አጥፍቶ ሀይሉን አጠናከረ፡፡ ከዚያ በ1980ዎች እስራኤል ሊባኖስን ስትወርና ስታጠቃ የሙስሊሞችን ጀመዓ በሙሉ ስትወጋ አህባሾች ግን በእንግሊዝ
ኤምባሲ ከለላ እንዲደረግላቸው ስለተደረገ ምንም አልተነኩም፡፡ ምክንያቱም አህባሾች የኢስራኤል ወዳጆች ናቸውና ነው፡፡ በ1990 አህባሾች በእስራኤል ተረድተው ወደ ፖለቲካ ፓርቲነት ተቀይረዉ በ1992 በሊባኖስ ምርጫ ጥቂት ወንበር አሸንፈው ፓርላማ ገቡ ፡፡ ቀስ በቀስ የራሳቸውን ሚሊሻ ጦር መልምለዉ የሊባኖስን ሙስሊሞች ማበጣበጡን ቀጠሉ ፡፡በሊባኖስ ያሉ እስላማዊ ጀማዓዎችን በሙሉ ለማጥፋት ከእስራኤልና ከሶሪያ መንግስት ጋር የቅርብ ግንኙነት በመፍጠር ከነርሱ ውጭ ያለውን ሁሉ ካፊር ከሃዲ እያሉ መፈረጁን ተያየዙት፡፡ ለሊባኖስ የደህንናት አካልና ለእስራኤል መረጃ እየሰጡ ሙስሊሙን ማስመታት ጀመሩ፡፡አህባሾች ራሳቸውን በውሸት ‹‹ የሻፊዒይ መዝሀብ እንከተላለን አህለል ሱንና ነን አሻዓሪ ነን ›› እያሉ ያስወራሉ፤ ሱፊያም ነን ይላሉ። በዚህ የውሸት ወሬያቸው የተነሳ አንደንድ የሱፊያ ዓሊሞች
በሊባኖስ፤ በሶሪያ፤ በግብጽ እና በሌሎች ሀገራትም መጀመሪያ እውነት ሱፊያ ናቸው
ብለው ተሸውደው ነበር። ሆኖም ግን ዉሎ ሲያድር ማንነታቸውን በዝርዝር ሲያውቋቸው
በግልጽ ምላሽ ጻፉባቸው ። ሰዉም ተንኮላቸውን እንዲያውቅና እንዳይከተሏቸው አስጠነቀቁ ።
እውነታው ግን እነርሱ የሁዳዎች እስላምን ለመበረዝ ና ሙሰሊሙን ለመከፋፈል የመሰረቱዋቸዉ የእስራኤል ቀኝ እጅ ናቸው ፡፡
አል-ሀበሺ ቀስ እያለ የአህለሱናን መንገድ እየበከለ፡ ከሺዓ፣ ከሪፋኢ፣ከሙርጂአ፣ከተክፊር፣ከሱፊ፣ከአል-ጀበሪያ፣ሙዕተዚላ፡ከዋሪጅ፤ ከቃዲሪያና ከጃህሚያ…ወዘተ ዉስብስብ አመለካከቶችን ቀይጦ(ድብልቅልቅ) አድርጎ የራሱን የሆነ አዲስ መንገድ (መዝሀብ) ፈጠረ፡፡ የሱን መንገድ ያልተከተሉትን የዓለም ሙስሊሞችን ማክፈር ስራዬ ብሎ ተያያያዘ፡፡ አብደላህ አል-ሐረሪ የነብዩ (ሶ.አ.ወ) አገር ና ቁርዓን የወረደባቸውን መካና መዲናን የካፊር አገር ናቸዉ ብሎ ጽፏል፡፡ ይህ ብቻ የየሁዳ መሳሪያ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ በተለይ አህባሾች ወደ ሀገራችን እንዲዘምቱ መንገዱን የጠረገላቸውና የገፋፋቸው እስራኤላዊዉ ሀጋይ አርሊች መሆኑ ለመላው ሚድያ ለሚከታተለው የሀገራችን ህዝብ ግልጽ ነው ፡፡ እነዚህ አህባሾች እስላምን ከበረዙባቸው አመለካከቶቻቸው ከቡዙው
ጥቂቱን እናንሳ ፡-
1. ስለ አላህ ያላቸዉ አመለካከት በቁርዓንና በሀዲስ ከተነገረው ጋር ይጋጫል፡፡ የነሱ አስተምህሮ ከግሪክ በመጣው ፍለስፍና ላይ የተመሰረተ በመሆኑ ይህን የፍልስፍና ሀሳባቸውን ላለመቀየር ብለው የአላህን ና የረሱልን(ሰአወ) ቃል መቀየር መርጠዋል ፡ ከዚህ በመነሳት አላህን የሚገልጹበት አገላለጽ ከአላህና ከረሱል(ሰአወ) አገላለጽ ይለያል እንኳን
ላልተማረ ለተማረዉም ግራ የሚያጋባ ነው ፡፡ የአላህን ስሞችና ባህሪያት ሲገልጹ አላህ በቁርዓን ነቢዩ (ሰአወ) በሀዲሳቸዉ ስለ አላህ ግልጽ በሆነ መልኩ ካስተማሩት ጋር በተቃራኒ ነው የሚያስተምሩት ፡፡
2. አንድ ሰው የነሱን አመለካከት መቀበሉን የሚያረጋግጡት የአላህ መልዕክተኛ ባስተማሩን በላኢላሀ እለ ላህ ሙሀመዱን ረሱሉላህ ሳይሆን እነሱ በፈለሰፉት ልዩ ቃላቶች ነው ፡፡
3. ለአመለካከታቸው ብዙውን ግዜ መረጃ የሚጠቅሱት የፍልስፍና አመለካከትንና ሺዓዎች የሚጠቀሙበትን ሰነድ ነው ፡፡
4. ቁርኣን የአላህ ቃል አይደለም የጂብሪል ንግግር ነዉ ይላሉ ፡፡(መጽሀፍ ኢዝሃር አል አቂደቱ አሱኒያ ፤ገጽ 59) ፡፡ አላህ ግን ቁርዓን የሱ ቃል መሆኑን በሱረቱ አተዉባህ አንድ ሙሽሪክ ነቢዩ ጋር ሲመጣ እንዲህ ነዉ ያላቸው ( የአላህን ቃል እስኪሰማ ድረስ ጥበቃ አድርግለት) ።
5. አላህ በቁርዓን ጀነትን ግቡ በሰራችሁት ስራ መሰረት እያለ እነሱ ግን እምነት በልብ ነው ባይሰግዱም ኢባዳ ባይሰራም አንዴ አመንኩ ማለት በቂ ነው ብለው ያስተምራሉ:: (መጽሀፍ አ-ደሊል አልቀዊም፣ ገጽ
7)
6. በእስላም ማንኛውንም ሰው መበደልም ሆነ ንብረቱን ያለፍቃዱ መንካት በጣም የተከለከለ ሆኖ ሳለ አህባሾች ግን ከክርስቲያን ጋር ቁማር መጫወት፣ የክርስቲያን ጎረቤትን መስረቅና ማጭበርበር ይቻላል ዋናው እንዳይነቃብህ በድብቅ ማድረግ ነዉ ብሎ ያስተምራሉ ።(መጽሐፉ ሰሪህ አል-በያን፣ገጽ 133) ከእንዲህ አይነቱ አህባሽ አላህ እኛንም አገራችንም ይጠብቅልን ፡፡ አሚን
7. ሰሀቦችን ይሳደባሉ አንዳንዶቹን ሰሀቦች ካፊር ናቸው የጀሀነም ናቸው ብለዉም ጽፈዋል ፡፡ ለምሳሌ
ታላቁን የነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ሰሃባ ሙአዊያ ኢብኑ አቢሱፍያን(ረ.አ) ካፊር የጀሀነም ብለዉ ገልጿዋል፡፡ የነብያችን (ሶ.ዐ.ወ) ዉድ ባለቤት የመላዉ ሙዕሚን እናት የሆኑትን አዒሻን (ረ.አ) ተሳድቧል፡፡
8. በነጃሳ ሰላት መስገድ ይፈቀዳል ይላሉ፡፡(መጽሐፉ ቡግየቱ ጧሊብ፣ገጽ 99-100)
9. ዘካ ከእስልምና ማዕዘናት አንዱ ሆኖ ሳለ ፡፡ አህባሾች ግን ሰው ዘካ እንዳያወጣ ከወረቀቱ ብር
ላይ ዘካ የለበትም ይላሉ፡፡
10. ሪባ (ወለድ) መውሰድን ያበረታታሉ፡፡ ባንክ ገንዝ አስቀምጠው ባንኩ የካፊሮች(ወይም ስራ አስኪያጁ ካፊር(ክርስቲያን) ከሆነ ጠላታችን ስለሆኑ ወለዱን መውሰድ ይቻላል ብለው ያስተምራሉ።
11. ሴቶች ሻሽ ብቻ አድርገው ሱሪና ታይት ማድረግ ይችላሉ ይላሉ። ጂንስና ፋሽንንም ያበረታታሉ፡፡
12. በእስላም ሙዚቃ ሀራም ሆኖ እያለ አህባሾች ግን በሊባኖስ አገር ‹‹James last›› የሚባል የሙዚቃ ባንድ አላቸው በዚህ ባንዳቸው ዓመታዊ የሙዚቃ ድግስ ያደርጋሉ:: በዛ ላይ ሴቶችና ወንዶች በጋራ ይጨፍራሉ፡፡
13. የአጅነቢይ ሴትን ፎቶ፣ ቪዲዮ አልያም በመስታወት ውስጥ ራቁቷን እንኳ ብትሆን በስሜትም ቢሆን ማየት ይቻላል ይላሉ: አላህ ግን በቁርዓን አጅነብይ ሴቶችን በተመለከተ እንዲህ ይላል (ሴቶችን እቃ ስትጠይቁዋቸው ከግርዶሽ በስተጀርባ ሁናችሁ ጠይቁዋቸው):
14. ‹‹ሪፋዒ›› የተሰኘ ጦሪቃን ያስፋፋሉ ይህ ጠሪቃ አላህንና ወልዮችን
እኩል መብት አላቸው ብሎ የሚያስተምር ሲሆን በኢትዮጵያም ማስተማር ጀምረዋል ይህ ጦሪቃ ከሺዓ ጋር የሚያመሳስለው ብዙ መንገድ አለው፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊም ግን ሱኒይ
ነው፡፡
15. ተከታዮቻቸው በአሜሪካና ካናዳ የቂብላ አቅጣጫ ካልተቀየረ ብለው ረብሻ ፈጥረው፡በመጨረሻም ከመስጂድ ሲባረሩ የራሳቸው መስጂድ በተለየ የቂብላ አቅጣጫ ሰሩ። አሁን እየሰገዱ ያሉት ከሙስሊሙ በተለየ
ቂብላ ነው ፡፡
16. አንድ ሰው ሰላት ሲሰግድ ራቁቱን በፓንት ብቻ ቢሰግድ መቃወም አይቻልም እሱ ይበቃል የሚል ሀሳብ እስካለው ድረስ ብለዉ ያስተምራሉ (ቡግየቱ አጣሊብ ፡138)
17. ድግምትን (ጥንቆላን) አይቃወሙም። ራሳቸውም ይፈፅማሉ፡፡ ለሲህር የሚጠቀሙበት ‹‹ሁቡብ አል-አሀብ›› ብለው የሚጠሩት የድግምት አይነት አላቸው፡፡
18. በደረሱበት ሀገር ሁሉ የነበረውን እስላማዊ እንቅስቃሴ የሀገሩን መንግስት በማሳሳትእና እነሱ የተሸሉ ዘመናዊ ነን ሌሎች ግን የድሮውን ኢስላም ነው የሚከተሉት በማለት ሌሎችን ማጥፈት እርምጃ ማስወሰድ የተለመደ በህሪያቸው ነው ለምሳሌ በሊባኖስ ፤ በሶሪያ፤በአሜሪካ፤በኡስትራሊያ፤በካናዳ …ወዘተ አሁን ደግሞ ይሀው በሀገራችን ኢትዮጵያ
የለመዱትን ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ አሁን እንኳን ግልጽ ካደረጉዋቸው ነጥቦች ብንነሳ በሀገሪትዋ ያሉ መስጅዶችን መድረሳዎችን በሙሉ በውድም ሆነ በግድ እንረከባለን የሙሰሊም ሚዲያዎችን እንቆጣጠራለን ካልሆነ እናሳግዳለን በማለት በየስብሰባቸው እየስወሩ ይገኛሉ፡፡
19. የሚገርመው ይህን ሁሉ የጥመት መንገድ እየተከተሉ ሱፊያ ነን፣ ሻፊዒይ መዝሀብ ተከታይ ነን እያሉ በሙሉ አፋቸው ማዉራታቸዉ ነዉ እነሱና ሻፊእይ የሰማይና የምድር ያህል መራራቅ ብቻ ሰይሆነ የብርሃንና የጨለማ ያህል ይፋለሳሉ ይጋጫሉ ፡፡
20. ከነርሱ እምነት ዉጭ ያሉ ዓሊሞችን እንዳያስተምሩ ሆን ብለው ያስተጓጉላሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያሳስራሉ፣ ያውካሉ፣ በአንድ ወቅት በሊባኖስ ይህን ችግር በስፋት ፈጥረው ህዝበ ሙስሊሙ መረበሹን ‹‹ሸሪዓ መጽሔት›› በቁጥር 574 እትሙ አስነብቦዋል ፡፡
21. በሸሪኣችን ያላግጣሉ ፡- ለምሳሌ አንድ ሰው መስጂድ መሄድ ካልፈለገ ነጭ ሽንኩረት ይብላ ይላሉ ፡እንዲሁም አስካሪ መጠጥ ያለበትን እቃ በዕቃው ሽፋን መጠጡንም አብሮ መሸጥ ይቻላል ላሉ ፡፡
22. ሌላዉ በባህሪያቸው ብዙ ግዜ ወዲያውኑ አቋማቸውን ግልጽ አያደርጉም፡፡ መጀመሪያ በደካማ ጎን ይገባሉ ለምሳሌ እኛ ሻፊዕይ ነን እኛ ሱፊይ ነን እኛ ሱኒይ ነን እኛ ዘመናዊ ነን . . . ወዘተ እያሉ ተከታይ ለመፍራት ይጥራሉ፡፡ ሰውን ጭፍን ተከታይ ካደረጉ በኋላ ቀስ
በቀስ ያፈነገጠውን ጎዳናቸውን ማስተማር ይጀምራሉ፡፡ ከዚያም ሙስሊሙን እርስ በርሰ የተለያዩ ስሞችን በመስጠት ማጋጨት ይጀምራሉ፡፡ በአጠቃላይ ዘዴያቸው አደገኛ ነው፡፡
23. አህባሾች የድሮ ኡለማዎችንና የዘመናችን ኡለማዎች ከነርሱ አመለካከት ጋር የማይስማሙ በመሆናቸው ብቻ ካፊሮች ናቸው ይላሉ ለምሳሌ የዘመናችን ታዋቂ ዳዒ ዶክተር ዛኪር ናይክንም ካፊር ብለው ፈርጀዋል (አኡዙ ቢላህ) ።
24. አህባሽ ተወልዶ ባደገበት ሊባኖስ አገር ውስጥ የፖለቲካ ፓርቲ መስርቶ ከሀገሪቷ መንግስት የሚጻረሩ ፖሊሲዎችን ሲያራምድ የነበረ እና የሀገሪቷ መሪ ረፊቅ አልሀሪሪ ግድያ እጁ እንዳለበት በunited nations(un) የግድያ አጣሪ ቡድን የተገለጸ አሸባሪ ቡድን ነው ፡፡
25. ከዻዕዋ ሰዎችም(ተብሊግ) ጋር የከረረ ግጭት ዉስጥ ናቸው ፡ ምክንያቱም የተብሊግ ጀማዓ በሙሰሊሞች አንድነት ያምናል በኺላፍ ዉስጥ አይገባም አህባሾች ግን አዲስ አስተሳሰባቸውን ያልተቀበለ በሙሉ ካፊር ነው ብለው ስለሚያምኑ ።
26. በዓለም ላይ ያሉ ዑለሞች የተቃዉሞ ፈትዋ ሰጥተውባቸዋል፡፡ለምሳሌ፡- የሱፊያ መዕከል እና የሻፊኢይን መዝሀብ መሰረት ያሚያደርገው የአል-አዝሀር ዩኒቨርሲቲ፣ የመዲና
ዩኒቨርሲቲ ፣ የሊባኖስ የፈትዋ መዕከል የሶሪያ ኡለማዎች እና የዓለም አቀፍ ዑለማዎች ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዩሱፍ አል-ቀርዷዊና ሌሎች በርካታ ዓሊሞች አህባሽ የጥመት መንገድ ላይ እንዳሉ ፈትዋ ሰጥተዋል፡፡ መጽሐፍም ጽፈዋል።
ይህ እንግዲህ በጣም ጥቂት ጸረ ኢስላም አቋማቸው ነው፡፡ እነኚህን ነው እንግዲህ በሀገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ መጅሊስን ሽፋን በማድረግ ለማስፋፋት የሁዶች እየሴሩ ያሉት፡፡በአሁኑ ሰዓት ያሉ የመጅሊስ አባላትም ሁሉም ባይሆኑም እየተደረገላቸው ያለውን ደጎስ ያለ ጥቅም ላለማስመለጥ ሙስሊሙን ወደዚህ መንገድ ለማስገባት ኢማናቸውን በጥቅም ለመሸጥ ቆርጠው ተነስተዋል ፡፡
ስለዚህ የዲን ፍቅር ያላችሁ በሙሉ ዲናችንን ለመበረዝ የመጡብንን አህባሾች ለመከላከል ይህን ወረቀት ያባዙና በከተማም ሆነ ገጠር ላለው ሙስሊም ያዳርሱ፡፡ ለበለጠ መረጃ በኢንተርኔት
ወይንም በጎግልላይ በአማርኛ(አህባሽ) ብለዉ ፡፡
ለዲናችንና ለኢማናችን ዘበኛ እንሁን!
ሊከፋፍሉን ለተነሱት ሴረኞች ፈጽሞ እጅ አንስጥ!
ሀስቡና አላሁ ወንዕመል ወኪል
ላልደረሰዉ ያድርሱ