Fw: Ahbashism በ ኢትዮጵያ...

25 views
Skip to first unread message

Aman Ibrahim

unread,
Sep 20, 2011, 3:25:57 AM9/20/11
to : Abujunaid, Abdulmenan Abduselam Alhabeshiy sum aladamiy, Ahmed Dawed, Ali Abdushikur, Alrebwah Alrebwah, UMERELFARUK, abdurahman keno, abubeker muhammed, sadat A.A, saleh ahmed, university albasearch, patrirkh bridgepub.com, Ibnu Maso Center, EDRIS MUHAMMED, ETHIOEDU MUS, Yenus Wagaw, Hamid Umer, hamdihun semie, Aman Ibrahim

----- Forwarded Message -----
From: jemal mohammed <jem...@gmail.com>
To: amanib...@yahoo.com
Sent: Wednesday, September 14, 2011 4:44 AM
Subject: Ahbashism በ ኢትዮጵያ...




Original Post


3:06am Sep 13


በዲናችን እንፅና!!
ዲናችንን ለመከላከል እንነሳ!!
ሊከፋፍሉን ለተነሱት ሴረኞች ፈጽሞ እጅ አንስጥ!
አል-ሐምዱሊላሂ ረቢል ዓለሚን ሙስሊም ላደረገን ጌታችን ምስጋና ይድረሰው! ሰላምና እዝነቱ በአሸረፈልኸልቅ መሐመድ(ሰ.አ.ወ) ላይ ይሁን፡፡
ስንቶቻችን በዲናች ላይ ስለመጽናት ከራሳችን ጋር መሹራ አድርገን እናውቃለን? አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይላል፡
‹‹ጌታህን ሞት እስኪመጣ ድረስ አምልከው›› (አል-ሒጅር 15፡99)፡፡
እንዲሁም ‹‹አላህ አማኞችን በዚህችም በመጪውም ዓለም በፅኑ ቃል ያፀናቸዋል፡፡››(ኢብራሒም 14፡27) ሲል ይናገራል፡፡
ያረቢ ከምታፀናቸው አማኞች አድርገን! እንደ ሙስሊምነታችን በዲናችን ቁርኣንና ሱንናን አጥብቀን ይዘን ቀጥ የምንል አድርገን! የማንም አስተሳሰብና ሴራ ከዲናችን ሊያወጣን አይገባም፡፡ እንደታዘዝነውም በኢስላም ቀጥ ማለት መቻል አለብን!
በቁርኣን ላይ አላህ(ጀለጀላሉሁ) እንዲህ ይመክረናል፡-
‹‹እንደ ታዘዝኸው ቀጥ በል›(ሁድ 11፡112)፡፡
ሙስሊም የማንንም መንገድ ሳይሆን የሰይዳችንን ሱንና አጥብቆ ይይዛል፡፡ ወዲዚያ ጥሪ ያደርጋል፡፡ ያስተምራል፡፡
የየሁዳንና ነሳራን ፍላጎት መቼም አይከተልም! አላህ በቁርኣኑ እንዲህ ይመክራል፡-
‹‹በመሆኑም (የሰውን ልጅ ወደ እውነት) ጥራ፡፡ እንደታዘዝከውም በቅኑ ፍኖት ላይ ፅና፡፡ የነርሱን ስሜትና ፍላጎት አትከተል፡፡›› (ቁርኣን 42፡15)
የኢስላም ጠላቶች ሁሌም በሙስሊሙ ላይ ይዶልታሉ፡፡ ያሴራሉ! ስለሆነም ንቃት ያስፈልገናል፡፡ ያላወቁ አለቁ እንደሚባለው ሴራቸውን ባለማወቃችን ስንቶቻችን አለቅን?! በጥሞና ይከተሉኝ፡፡ የኛ የሙስሊሞች ነገር አባት አልባ ሆኗል! ስለዚህ ተነሱና ለዲናችሁ ቁሙ፡፡
እስቲ ስንቶቻችን የሰሞኑን በእስራኤል የተላከልንን የአህባሽ አደጋ ሰምተናል? መጅሊስስ ከየሁዳ ጋር ሆኖ ሙስሊሙን ሊበክል ቆርጦ መነሳቱን ሰምተናል? በሐረር ከተማ የተካሄደውን ጉባኤስ ሰምተናል? ነገሩ እንዲህ ነው፡፡ የሙስሊሙን አንድነትና ህልውና አደጋ ላይ መጣል የዘውትር ህልማቸው የሆነው የሁዶች ለሙስሊሙ ብዙ መሰናክሎችን አዘጋጁ፡፡
አንዱ በኛ አገር እንዲስፋፋ ዘመቻ የተጀመረው ‹‹አሕባሽ›› ነው፡፡ ሙስሊሙን እርስ በርስ በማባላት እነርሱ በሰላም ጥቅማቸውን ማስጠበቅ ፈለጉ፡፡ በኢትዮጵያ እንዴት “አህባሽን” ማስፋፋት አለብን ብለው ከቴላቪቭ ዩኒቨርሲቲ ሀጋይ ኤርሊች የተባለ ሰላይ ወደ ኢትዮጵያ ላኩ፡፡ ሰውየው የእስራኤል ሰላይና የጦር ሠራዊት አባል ሲሆን በ1967 የ6ቱ ቀን ጦርነት ተጠባባቂ ወታደር ሆኖ ተሳትፎም ነበር፡፡ ጥናት አደረገና ሙስሊሙን ለመከፋፈል በአብደላ አል-ሐረሪ የተመራውን የአህባሽ ቡድን ለማስፋፋት ቆርጦ ተነሳ፡፡ እቅዱን የዛሬ ሦስት ዓመት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አቀረበ፡፡
በኢትዮጵያ ቴሌቨዥን በእንግሊዘኛ ፕሮግራም (ሚቲ ኢቲቪ) ላይም አቀረበ፡፡ መጽሐፍም ጽፎ አሰራጨ።ለመንግስት ባለስልጣናት ጭምር አዳረሰ፡፡ በግል ጎተጎታቸው፡፡ ሴራውን ተቀብለውም ደገፉት፡፡ ከዚያም ዓላማውን ከዳር ላድረስ ማገዝ ጀመሩ፡፡ በቶታል(ሦስት ቁጥር ማዞሪያ፣አዲስ አበባ) የተከፈተላቸውን ትምህርት ቤትንም መደገፍ ጀመሩ፡፡ በዲን ተመሳስለው እያስተማሩ ዓላማቸውን ደብቀው ቆዩ፡፡ ሰው ሳያውቅ እነርሱ ጋር የሚማርም ነበር፡፡ በየጊዜው እያስተማሩ በኺላፋ አስበው ሙስሊሙን ለማናቆር ሲሰሩ ነበር።
በቅርቡ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ሙሉ ድጋፍ ማድረግ የጀመረላቸው ሲሆን መንግስትም መጅሊስ ይህን የየሁዳ እገዛ ያልተለየውን የአህባሽን መንገድ ተከትሎ ህዝቡ በዚህ መንገድ እንዲጠመቅ ሥራ ጀመረ፡፡ ቁጥራቸው 1300 ያህል የመጅሊስ አባላትና ደጋፊዎቻቸው ከመላው ኢትዮጵያ ወደ ሐረር ተጠሩ፡፡ የኢፌዲሪ የፌዴራ ጉዳዮች ነበር መድረኩን ያቀናበረው። ሚኒስተሩም ዶ/ር ሽፈራው ተክለማሪያምም ዋና አቀናባሪ ሆነው ሙስሊሙም ጭምር ከሚከፍለው
ግብር ላይ ስድስት ሚሊዮን ብር ለእኩይ አላማቸው መደቡ፡፡ ዶ/ሩ ጴንጤ ሲሆኑ በደቡብ በተለይም በሆሳዕና ባለውና ሙስሊሙን ለማክፈር በሚሰራው የጴንጤ ‹‹ሲኖዶስ›› የቦርድ አባል ናቸው፡፡ እኒህ ሰው ናቸው እንግዲህ በሐረሩ ስብሰባ ከአሕባሽ መንገድ ሌላ አትከተሉ፡፡ መጅሊስን የማይታዘዝ ፀረ-ልማት፣ ፀረ-ህገ መንግስት ብለው ሲደሰኩሩ የተሰሙት።ይባስ ብለው የሱንና ተከታዮችን አክራሪ ብለው ፈረጁ፡፡ በየት/ቤቱ ኢስላማዊ ህግጋትን የሚገፋ መመሪያ ከመስከረም 2004 ጀምሮ እንደሚተገበርም መግለጻቸውን ከሜደያዎች አነበብን። ሙስሊም ተማሪዎችም አክራሪ ሆነዋል አሉ፡፡ በዚህ መድረክ የኢትዮጵያ መንግስት ሕገ መንግስቱን ጥሶ በሃይማኖታችን (በዲናችን) ጣልቃ
ገብቶ ሊያፋጀን 15 የአህባሽ ተከታዮችን ከሊባኖስ አስመጣ፡፡ የፔትራም ካምፓኒ ባለቤትም አቶ አብዱልከሪም በድሪም ከመንግስት ጋር ሆኖ እንቅዳቸው ደገፋ። በየወሩ አንድ ሚሊዮን ብር እያወጣላቸው ነው፡፡ መንግስት ሙስሊሙን ለማበጣበጥና ለማጋጨት ምን ያሀል እንደቆረጠና ከየሁዳ ጋር እንደ ተባበረ የሚያሳየው መንግስት ከሊዝ ነፃ 100 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት በየሁዳ ለሚታገዘው አህባሽ ኮሌጅ መክፈቻ ብሎ ከሁለት ወራት በፊት በነፃ ሰጣቸው፡፡ መስጊድ ለመስራት በስንት ግድያ የሚወሰደውን መሬት ለመስጠት ፈቃደኛ ያልሆኑት ለሙስሊሞች አስበው ሳይሆን ሊያፋጁን አስተሳሰቡን ማስፋፊያ ኮሌጅ ሊከፍቱላቸው ሰጧች። ወይስ አጅር ፍለጋ?
በሐረሩ የማጥመቂያ ፕሮግራም በኃላ በጊዮን ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ በፌደራል ጉዳዮች ተሰጠ፡፡ እነርሱ ያመጡት ዶ/ር ሰሚር ቃዲ አ-ሪፋኢ ሱኒውን ሙስሊም በአክራሪነት ፈርጀው፣ እነርሱ አሸባሪ ካልሆኑ ማነው አሸባሪ? አሉ። በኢትዮጵያ አህባሽን ለማሽፋፋት አብደላ አል-ሀረሪ በ2008 መንግስት ሊያስመጣ ዝግጅቱን ጨርሶ ነበር። ሆኖም በረመዳን አሸረር አዋኪር ሊመጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ በልዩ ጀት ሊያመጡት እያሰቡ አላህ ቀደማቸው። በረመዳን ሁለት ማታ አላህ አብደላህ አል-ሐረሪን በቃህ ብሎት ወደ አኪራ ወሰደው። ሞተ። እቅዳቸውም ከሸፈ። አሁን ደግሞ ዳግም
ተጠናክረው መጡ። ከሀረሩ በኋላ ለሁለተኛ ዙር ከረመዳን በኋላ በሸዋል ወር ደግሞ በዚህ በአዲሱ የአህባሽ መንገድ ስድስት ሺህ ሙስሊሞችን ለማስገባት መጅሊስና መንግስት በጋራ እየተሯሯጡ ነው፡፡ ሁለተኛውን ዙር አወሊያ ውስጥ እና በክፍለ አገር ለማካሄድ ፈልገዋል፡፡
እስከ ዛሬ በምርጫ ስንመርጠው የከረምነው መንግስት መጀመሪያውኑ እንዲመቸው ብሎ የራሱን ካድሬዎች እየመለመለ የሙስሊሙ መሪ ናቸው እያለ ወደመጅሊስ አስገባቸው፡፡ ህዝቡ ይመርጣቸው ነበር መንግስት በጓሮ በር የሚልካቸው፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ ቸል(ዝም) ስለሚል ያሻቸውን ሲሰሩ ነበር። ይኸውም አሁንም እንደ ከዚህ ቀደሙ
ዓላማውን ለማሳካት መሳሪያ አድርጓቸው አብዛኞዎቹ ሃይማኖትን ሽፋን አድርገው ወደ መጅሊስ የመጡ የፖለቲካ
ካድሬዎች ናቸው፡፡ ሀጂና ሼህ ተብለው ሰልጠነው መጡ። አቤት ማስመሰል ሲችሉበት! አሁን ለሚያያቸው ሼኽ
አይመሽሉም? የቅርብ ጊዜ እቅዳቸውን በሐረር በአቋም መግለጫ አውጥተዋል፡፡ በጋዜጣ (ሰለፊያ) አላነበቡምን? ግልፅ
ዳዕዋ ማስቆም! አህባሽ ማስፋፋት? መስጊድና መድረሳ እንዳይሰራ ነው ዓላማቸው። ለየሁዳ ሴራ መንገድ መጥረግ ነው
ተልኮአቸው!! ሰው እንዴት ሙስሊም ነኝ እያለ ከየሁዳ ጋር ተባብሮ በአላህ ዲን ላይ ያሴራል? ኢናሊላሂ ወኢና
ኢለይሂ ራጂዑን! የመጅሊስ ሰዎች በዲኑ ላይ እያሴሩ ነው፡፡ አንድም የሰሩት ከይር ሥራ የላቸው! ሰዉ አማራጭ
ሲያጣ አንዲት የትብብር ደብዳቤ ይጽፉና ዝግቱ “ከመጅሊስ ጋር በመተባበር” እየተባለ ይነገራል(ለምሳሌ ኤግዚብሽኑና
የሚሊኒየሙ የቁርአን ዉድድሩ)።ይህ ከመጋረጃ ጀርባ ለሚሰሩት የጥፋት ስራ ሽፋንና ከለላ ሆናቸው። ለመሆኑ
የሁዳዎች በሀበሻ ሙስሊሞች ዉስጥ ሊያስፋፉልን የሚፈልጉት የአህባሽ መንገድ ምንድነው? ቀጥለን የምንመለከተው
ደግሞ በጥቂቱም ቢሆን የአደጋጋቸውን ክፋት ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፡፡
የሀበሺ (አህባሽ) መንገድ የጀመረው አብደላ አል-ሐረሪ የተባለ ግለሰብ ነበር፡፡ ግለሰቡ ሐረር የተወለደ ሲሆን የሀይለ
ስላሴ መንግስት ቀኝ እጅ ነበር፡፡ ከሃይለስላሴ አማች አንደርጌ ጋር ሆኖ ዓሊሞችን ሲያሳስር፣ መብትና እኩልነትን
የሚሉትን ሙስሊሞችን ሲያጠቃ እና ሲሰልል ቆየ፡፡እ.ኤ.አ በ1940 (1367 ሂጅራ) ላይ በሐረር የቁርኣን ሂፍዝ ማዕከል
መምህራንን አሳስሮ መርከዙን አስዘጋ፡፡ የመርከዙን ዳይሬክተር ሼህ ኢብራሁም ሀሰንን አሳስሮ 23 ዓመታት
አስረፈደባቸው፡፡ አብደላ አል-ሐረሪ የፈጠረው ፊትና ‹‹ፊትነተልኩሉብ›› ተብሎ ይታወቃል፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ
በመምጣት በሀደሬ ሰፈር ሙስሊሙን ሲያጋጭ ቆይቶ በ1948 ወደ እስራኤል ተጓዘ፡፡ ለዓመት በዚያ ቆይቶ በ1949
ወደ ሶሪያ ገባ፡፡ ከዚያም በ1950 ወደ ሊባኖስ ተጓዘ፡፡ በሊባኖስ ቁርአን በማቅራት ህፃናትን ማሳደን ቀጠለ፡፡ ቀስ እያለ
በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪች አፈራ፡፡ ከአገር ከወጣ በኋላ ከየሁዳዎች ጋር በሚስጢር ይገናኝ ጀመር። ከፍተኛ ገንዘብ
ተመድቦለት እ.አ.አ በ1982 የሊባኖስ የርስ በርሱ ጦርነት ጊዜ ድምፁን አጥፍቶ ሀይሉን አጠናከረ፡፡ ከዚያ በ1980ዎች
እስራኤል ሊባኖስ ስትወርና ስታጠቃ የሙስሊሞች ጀመዓ ስትወጋ አህባሾችን ግን ተወቻቸው፡፡ ምክንያቱም የርሷ
ወዳጅ ናቸውና ነው፡፡ በ1990 አህባሾች በእስራኤል ተረድተው ወደ ፖለቲካ ገቡ፡፡ በ1992 የሊባኖስ ምርጫ ጥቂት
ወንበር አሸንፈው ፓርላማ ገቡ፡፡ ቀስ በቀስ የራሳቸውን ሚሊሻ ጦር መለመሉ፡፡ ሙስሊሙን ማበጣበጡን ገፍተው
ቀጠሉ፡፡ ከነርሱ ውጭ ያለውን ሁሉ ‹‹ካፊር›› እያሉ መፈረጁ ተያያዙት፡፡ ለመንግስትና ለእስራኤል መረጃ እየሰጡ
ሙስሊሙን ማስመታት ጀመሩ፡፡ ራሳቸውን በውሸት ‹‹የሻፊዒ መዝሀብ እንከተላለን›› እያሉ ያስወራሉ፡፡ አህለል ሱንና
ነው። አሻዓሪና ማቶረዲ ነን ይላሉ፡፡ ሱፊያም ነን ይላሉ። ሆኖም የሶፊያ ዓሊሞች በሊባኖስ በሌሎች ሀገራትም
መጀመሪያ እውነት ሱፊያ ናቸው ብለው ተሸደውደው ነበር። ሆኖም በሗላ በዝርዝር ሲያውቋቸው አጋልጠው ምላሽ
ጻፉባቸው። ሰዉም እንዲያውቃቸውን እና እናዳይከተሏቸው አስጠነቀቁ።እውነታው ግን እነርሱ የእስራኤል ቀኝ እጅ
ናቸው፡፡ ቀሰ በቀስ አል-ሀበሺ የሱንና መንገድ እየበከለ ሺዓ፣ ሪፋኢ፣ ሙርጂአ፣ተክፊር፣ሱፊ፣አል-ጀበሪ፣ ቃዲሪያና
ጃህሚያ ወዘተ መንገዶችን ቀይጦ(ስፕሪስሪስ) አድርጎ የራሱን አዲስ መንገድ ፈጠረ፡፡ የዓለም ሙስሊሞችን ማክፈር
ያዘ፡፡ አብደላ አል-ሐረሪ ‹‹ሳዑዲ እንዴት ከፈረች?›› ብሎ ሁሉ መጽሀፍ ጽፏል፡፡ የነብዩ (ሶ.አ.ወ) አገር መካና መዲና
የካፊር አገር ብሎ ጽፏል፡፡ ይህ ብቻ የየሁዳ መሳሪያ መሆኑን ቁልጭ አድርጎ ያሳያል፡፡ ለመሆኑ አቋማቸው ምንድነው?
ቀጥሎ ጥቂቶችን ብቻ እናያለን፡-
1. ከካፊር ጋር ቁማር መጫወት፣ የካፊርን (ክርስቲያን) ጎረቤት መስረቅና ማጭበርበር ይቻላል ብሎ
ያስተምራል።ዋናው እንዳይነቃ በድብቅ ማድረግና ዋናው መጠንቀቅ ነው ብሎ ያስተምራል፡፡ (መጽሐፉ ሰሪህ
አል-በያን፣ገጽ 133)
2. ሰሀቦችን ይሳደባል፡፡ አንዳንዶቹን ሰሀቦች ካፊር ናቸው የጀሀነም ናቸው ብሎ ጽፏል፡፡ ለምሳሌ ታላቁን የነብዩ
(ሶ.ዐ.ወ) ሆሃባ ሙአዊያ ኢብኑ አቢሱፍያን ካፊር የጀሀነም ሲል ገልጿል፡፡ የነብያችን (ሶ.ዐ.ወ) ባለቤት አዒሻን
ተሳድቧል፡፡
3. በነጃሳ መስገድ ይፈቀዳል ይላል፡፡(መጽሐፉ ቡግየቱ ጧሊብ፣ገጽ 99-100)
4. ዘካ የለም ይላል፡፡ ዘካ ከእስልምና ማዕዘናት አንዱ ነው፡፡ አህባሾች ግን ሰው ዘካ እንዳያወጣ ከወረቀቱ
ብር(ኖት) ላይ ዘካ የለበትም ይላሉ፡፡ ይህ ማለት በባንክም ይሁን በቤትዎ ቢሊዮን ብር እንኳ ካለዎ ዘካ
አይስጡ ብሎ ይቀሰቅሳሉ፡፡
5. ሪባ (ወለድ) መውሰድን ያበረታታሉ፡፡ ባንክ ገንዝ አስቀምጠው ባንኩ የካፊሮች(ወይም ስራ አስኪያጁ
ካፊር(ክርስቲያን) ከሆነ ጠላታችን ስለሆኑ ወለዱን መውሰድ ይቻላል ብለው ያስተምራሉ።
6. ሴቶቻቸው ሻሽ ብቻ አድርገው ሱሪ ማድረግ ይችላሉ ይላሉ። ጂንስና ፋሽንንም ያበረታታሉ፡፡
7. በሊባኖስ አገር የሙዚቃ ባንድ አላቸው ይህ ባንዳቸው ‹‹James last›› ይባላል፡፡ ዓመታዊ የሙዚቃ ድግስ
ያደርጋሉ:: በዛ ላይ ሴቶችና ወንዶች በጋራ ይጨፍራሉ፡፡
8. የአጅነቢ ሴትን ፎቶ፣ ቪዲዮ አልያም በመስታወት ውስጥ ራቁቷን እንኳ ብትሆን በስሜትም ቢሆን ማየት
ይቻላል:: ከቁርአንና ሱና ተቃራኒ ሆነው የተከለከለው በዓይን በቀጥታ ማየት ብቻ ነው ብለው ያስተምራሉ፡፡
9. ‹‹ሪፋዒ›› የተሰኘ ጦሪቃን ያስፋፋሉ:: በኢትዮጵያ ጀምረዋል ይህ ጦሪቃ ከሺዓ ጋር የሚያመሳስለው ብዙ
እምነት አለው፡፡ የኢትዮጵያ ሙስሊም ግን ሱኒ ነው፡፡
10. እምነት በልብ ነው ባይሰግዱም ኢባዳ ባይሰራም አንዴ አመንኩ ማለት በቂ ነው ብለው ያስተምራሉ::
(መጽሀፍ አ-ደሊል አልቀዊም፣ ገጽ 7)
11. ተከታዮቻቸው በአሜሪካና ካናዳ የቂብላ አቅጣጫ ካልተቀየረ ብለው ረብሻ ፈጥረዋል፡፡ በመጨረሻም
ከመስጊድ ሲባረሩ የራሳቸው መስጊድ በተለየ ቂብላ ላይ ሰሩ። አሁን ከሙስሊሙ በተለየ ቂብላ ነው
መስጊዳቸው፡፡
12. ድግምትን አይቃወሙም። ራሳቸውም ይፈፅማሉ፡፡ ለሲህር የሚጠቀሙበት ‹‹ሁቡብ አል-አሀብ›› ብለው
የሚጠሩት ነገር አላቸው፡፡
13. ቁርኣን የጂብሪል ቃል እንጂ የአላህ ቃል አይደለም ብለዋል። የአላህ ቃል አይፃፍም ይላሉ፡፡
14. የሚገርመው ይህን ሁሉ የጥመት መንገድ እየተከተሉ ሱፊያ ነን፣ ሻፊዒ መዝሀብ ተከታይ ነን ይላሉ፡፡
15. ከነርሱ እምነት ዉጭ ያሉ ዓሊሞችን እንደያስተምሩ ሆን ብለው ያስተጓጉላሉ፣ ይደበድባሉ፣ ያሳስራሉ፣
ያውካሉ፣ በአንድ ወቅት በሊባኖስ ይህ ችግር በስፋት ፈጥረው ‹‹ሸሪዓ መጽሔት›› በቁጥር 574 እትሙ
‹‹ሊባኖስ ጦርነት በመስጂዱ ውስጥ›› በሚል ርዕስ ጽሑፍ አስነበቦ ነበር፡፡
16. ዓመታዊ የሴቶቻቸው የሂጃብ ፋሺን ሾው አላቸው፡፡ በዚያ ላይ ሂጃብ ከሚለብሱት ሴቶች ጋር በጋራ
ይጨፍራሉ፡፡
ይህ እንግዲህ በጣም በጥቂት አቋማቸው ነው፡፡ ብዙ ወዲያውኑ አቋማቸውን ግልጽ አያደርጉም፡፡ መጀመሪያ
በደካማ ጎን ይገባሉ፡፡ ጭፍን ተከታይ ካደረጉ በኋላ ቀስ በቀስ ያፈነገጠውን ጎዳናቸውን ማስተማር ይጀምራሉ፡፡
በመጀመሪያ ሆን ብለው ኸላፍ ያለበትን ነጥብ ብቻ እያነሱ ተከታይ ለመፍጠር ይጥራሉ፡፡ በዚያውም ሙስሊሙን
ማወክ ይጀምራሉ፡፡ በአጠቃላይ ዘዴያቸው አደገኛ ነው፡፡
በዓለም ላይ ያሉ ዑለሞች በርካታ ፍትዋ ሰጥተውባቸዋል፡፡ አል-አዝሀር ዩኒቨርሲቲ፣ መዲና ዩኒቨርሲቲ እና የዓለም
የዑለማ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዩሱፍ አል-ቀርዷዊና ሌሎች በርካታ ዓሊሞች አህባሽ የጥመት መንገድ ላይ እንዳሉ ፈትዋ
ሰጥተዋል፡፡ በመጽሐፍም ጽፈዋል። እነኚህን ነው እንግዲህ ኢትዮጵያ ውስጥ ለማስፋፋት የሁዶች እየሰሩ ያሉት፡፡
መጅሊስና መንግስትም ሙስሊሙን ወደዚህ መንገድ ለማስገባት ቆርጠው የተነሱት፡፡ ታዲያ መፍትሄው ምን
ይሆን?
አህባሾችን በኢትዮጵያ ለማስፋፋት ጥረቱ ከተጀመረ ጥቂት የቆየ ሲሆን በአንዳንድ አካባቢዎች ሳይታወቅ ስር
እየሰደዱ ነው፡፡ ለምሳሌ በጎንደር፣ትግራይ፣ ነቀምት፣ አዲስ አበባ 3 ቁጥር ማዞሪያ ቶታል፣ መካኒሳ እና ላፍቶ
ሰፈር፣ ኦሮሚያ ውስጥ መሠረት ለመጣል እየታገሉ ነው፡፡ በነዚህ አካባቢዎች ሙስሊሙን አክራሪ፣አሸባሪ፣
ወሀቢያ፣ ጽንፈኛ ወዘተ በማለት ማጥላላት ጀምረዋል፡፡ እቅቁ ዳዒ ዶክተር ዛኪር ናይክንም ካፊር ብለው
ፈርጀዋል። የዻዕዋ ሰዎችንም(ተብሊግ) ዻዕዋ ሰዎች ጋርም በዓለም ላይ ከረር ባለ ግጭት ዉስጥ በቅርቡ
ገብተዋል። መጅሊስ የሙስሊሙ ተቋም ቢሆንም አመራሩ በፀረ-ኢስላም ሥራ ላይ ተሰማርቷል፡፡ በሌላ አካል
የሚመራ የጠላት መሳሪያ ሆኗል፡፡ ምርጫ ተደርጎ ትክክለኛ የሙስሊሙ ወኪል ሊመረጥ አልቻለም፡፡ በሙስናና
በፀረ- ኢስላም ተግባር የተሰማራ ሆኗል፡፡ መንግስትም ሙስሊሙን ፈጽሞ መስማት አልፈለገም፡፡ ምን ያመጣሉ?
በሚል ንቀት ታውሯል፡፡ ታዲያ በየሁዳና ነሷራ ሴራ ዲናችንን ሲቦረቦር እጃችን አጣጥፈን መመልከት አለብን?
በየአካባቢያችን መሹራ አድርገን ለመከላከል እንነሳ! ሊከፋፍሉን ለተነሱት ሴረኞች ፈጽሞ እጅ አንስጥ! ይህ ሁሉ
ድፍረት የተሰማቸው በዲናችን የሚፈጸመውን ሴራ ስለማንከታተል ነው፡፡ ተነሱ መጅሊስ ሙስሊሙን
እንዳማይወክል እንግለፅ! ላልሰማው እናሰማ! ህዝባችንን እናንቃ! ሴራቸው መች ይህ ብቻ ይሆንና? ኢስላማዊ
ድርጅቶችን ለማዘጋት ቆርጠው ተነስተዋል፡፡ ተማሪዎችን ለመግፋትና ሰላትና ጂልባብ እንዳይለብሱ ለማድረግ
ተነስተዋል። ዲናችንን ለመከላከል ይህን ወረቀት ያባዙና በከተማም ሆነ ገጠር ላለው ሙስሊም ያሰራጩ፡፡
ዲንዎን ከጥፋትና ከጥቃት ያድኑ!
የነብያችንን (ሶ.ዐ.ወ) ሱንና ትክክለኛውን የቁርኣን መንገድ ትተን የየሁዳ መሳሪያ እንድንሆን ታቀደ! እንዴት ቢንቁን
ነው ጃል?! መተኛት አይበቃንምን ያ ሙስሊሙን! (ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በኢንተርኔት
( http://www.facebook.com/l/EAQDq3GCqAQBl7nVYgM58urj4UGXmvl-UGgYHb4g4vBWlmQ/www.antihabashis.com) ወይንም በጎግል ላይ አልያም በአዝሀር ዩኒቨርሲቲ ዑለሞች ፈትዋ ላይ ይፈልጉ፡፡)
ይህን ወረቀት አባዝተን በረመዷን ከፍተኛ አጅር እናግኝ! ለአላህ ዲን ቁሙ! ዳዕዋ እስኪቆም፣ መስጊዶቻችን
እስኪነጠቁ፣ ዲናችንነ እስኪ ቦረቦር ዝም ማለት አለብን? በአንድነት ተነስተን የየሁዳን ሴራ እናክሽፋ! ኢስላምን
የሁዳና ተባባሪዎች ሲቦረብሩ ምን አድርገክ ብሎ አላህ ነገ በቂያማ ቢጠይቀን ምን ይሆን መልሳችን?
ወሰላሙ ዓላይኩም!

View Post on Facebook ¡ Edit Email Settings ¡ Reply to this email to add a comment.



Aman Ibrahim

unread,
Sep 20, 2011, 2:50:26 PM9/20/11
to Hamid Umer, hamdihun semie, Ahmed Kerem, abdurahman keno, kedir suleiman, ETHIOEDU MUS, Nuraddis Muhammed, mohammed sherif, saleh ahmed, Ridwan, Umer Tesfaaye, طيبة محمد‎
Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages