የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚያወጣው አዲስ መመርያ

24 views
Skip to first unread message

Mohammedsadik Kelil

unread,
Sep 25, 2011, 3:08:51 AM9/25/11
to ethio Muslims In Europe, ethiomuslim google group, Ethiop...@yahoogroups.com, Jematel Mahbub, Muslim Ethiopian Friends, Ummat Mohammed
 
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የሚያወጣው አዲስ መመርያ ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎትን በእስላማዊ የፋይንናስ መርህ መሠረት ለማካሔድ በሚንቀሳቀሱ ላይ መደናገጥን አስከትሏል፡፡ ሆኖም ከመደበኛው የባንክ አሠራር ጐን ለጐን ወለድ አልባ አገልግሎትን ፈቅዷል፡፡

ከመጪው መስከረም 20 ቀን 2004 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገው መመርያ እንደሚለው ከሆነ፣ መደበኛ የባንክ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች በወለድ አልባ መርህ መሠረት ሙሉ ለሙሉ እንዲሠሩ አይፈቀድም፡፡

የእስላማዊ የባንክ አገልግሎትን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ትልመ ሐሳብ (Proposal) በቀረበበት ወቅት፣ ከሦስት ዓመት በፊት የወጣው አዋጅ እየተዘጋጀ የነበረ ሲሆን፣ ብሔራዊ ባንክ ያንን ተከብሎ በኢትዮጵያ ባንኮች ታሪክ የመጀመርያ የሆነውንና የወለድ አልባ ባንክ አሠራር እንደሚቻል የሚጠቅስ አንቀጽ በዚሁ አዋጅ አካቷል፡፡

ከሁለት ዓመት ያላነሰ ጊዜ የወሰደው የመመርያው ረቂቅ ለባንኮች ቢሰራጭም፣ እስላማዊ የባንክ አሠራርን ከመደበኛው የባንክ አሠራር ጐን ለጐን ማስኬድ የሚቻልበትን አግባብ ግን የሚገልጽ ምንም ነገር አልነበረም፡፡

የእስላማዊ የባንክ መርህን ለማንቀሳቀስ ረጅም ጊዜ ያስቆጠረውና የመጀመርያ ለመሆን በምሥረታ ሒደት ላይ የነበረው የዘምዘም ባንክ፣ እንዲህ ያለው መመርያ አይወጣም በሚል እምነት ለባንኩ ምሥረታ የሚያስፈልገውን ካፒታል አሟልቶና አደራጅ ኮሚቴ አዋቅሮ በኢትዮጵያ የመጀመርያውን እስላማዊ ባንክ ለመመሥረት ተቃርቦ ነበር፡፡

የባንኩ ባለአክሲዮኖች ተሰብስበው የቦርድ አባላትን የሰየሙ ቢሆንም፣ በሳምንቱ መጨረሻ መመርያው ይፋ ለመደረግ መቃረቡ ሒደቱን መና ያስቀረዋል ተብሎ ተሰግቷል፡፡ የብሔራዊ ባንክ ምንጮች እንደገለጹት፣ ባንኩ መመርያውን የሚያወጣው ባንኮች መደበኛውን የባንክ አሠራር መከተል አለባቸው ከሚል መነሻ ነው፡፡

ወለድ አልባ የባንክ አገልግሎት ለመስጠት ፍላጐት ያላቸው በመኖራቸው ከተለመደው የባንክ አሠራር ጐን ወለድ አልባ አገልግሎት መስጠት ተፈቅዷል፡፡ ወለድ አልባ ባንክ ለብቻ ማቋቋም ግን አዲስ በሚወጣው መመርያ የተከለከለ ይሆናል፡፡

ይህም ሆኖ እንደ አንድ የባንክ አገልግሎት የሚሰጠው ወለድ አልባ አሠራርም እንዲያሟላ የተጣለበት ግዴታዎች አሉ፡፡ አንደኛው የሪስክ ማኔጅመንት ሲሆን ይህም በተለይ ከእስላማዊ ባንክ አሠራር አኳያ ወሳኝ ነው ተብሏል፡፡

ሌላው ይህንን አሠራር ከመደበኛው የባንክ አሠራር በመለየት የሚያዝበት አሠራር ሲሆን፣ በዚህ ዘርፍ አገልግሎት የሚሰጡ ባንኮች ለብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ አቅማቸውን፣ የሒሳብ አያያዝ ፖሊሲያቸውንና የእስላማዊ ባንክ ከመደበኛው የባንክ አሠራር አኳያ የሚኖረውን ድርሻ የተመለከቱ መረጃዎችን ለብሔራዊ ባንክ የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ 

Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages