Fwd: ሰላምታና....

2 views
Skip to first unread message

zbe...@comcast.net

unread,
Oct 9, 2014, 5:45:50 PM10/9/14
to Abraham Azene, Addisu Habte, Tilahun Degefu, Seleshi Sendekie, girmatam, Solomon Mola, Pietro Toggia, Afework Wogayehu, Fikru Bekele, Abate Mammo, abek...@yahoo.com, ec...@googlegroups.com

Hello all,
Below is a letter from Netherlands. sent to me via LinkedIn. If any of you can help our brother on his request please do so.
Thank you so much
Z


 
 
LinkedIn
 
 
 
 
 
 
Amanuel Mekonen
 
Amanuel Mekonen
Sportleider bij RSVV Arnhem Zuid en buurtcoach en scholarshiper bij Richard Krajicek Foundation
 
 
ውድ አቶ ዘሪሁን,

ስምዎትንና ኣድራሻዎትን ያገኘሁት በሥራዉ የምወደዉን ሀይሌ ገሪማን በክብር እንግድነት በጋበዛችሁበት ፴ኞው የማህበራችሁ በዓል ላይ ዝግጅታችሁን በፌስ ቡክ አይቼ እጅግ ደስ ስላለኝ እነማን እንደሆናችሁ ጎግልን ስጠይቅ እርስዎን አገኝሁ። ስሜንና ዝርዝር ማንነቴን ከሊንከዲን እንዳዩት ዓማኑዔል እባላለሁ ከሁለት ልጆቼና ባለቤቴ ጋር ኔዘርላንድ ዉስጥ ነዉ እምኖረዉ። በደስታ እየሠራሁ እምኖርበት ዓለም ስፓርት ነዉ ( Proffessional Sport & activity leader)
ከእስፓርቱ ዓለምም ቴኒስን ልቤ ዓርፎበት ( ለጊዜዉ 95 ፐርሰንት በነጮች የተያዘዉን) ላለፋት 4 ዓመታት የቴኒስ ስፖርትን ለማሳደግ ከሚጥሩ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባለሁበት ዓገር በኔዘርላንድ ለልጆች በሚዘጋጁ ፕሮጀክቶች ላይ በመሥራት ላይ ነኝ. ይህንንም ጥረቴንና ፍላጎቴን ያየ ዓንድ የቴኒስ ደጋፊ ድርጅት የአሠልጣኝነት ትምህርት( International Licence) እንድከታተል እድል ሠጥቶኝ ከ 2013 አጋማሽ ጀምሮ ያን ት/ት ለመካፈል የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን ለማሟላት በጥረት ላይ ነኝ.

እንደሚያዉቁት ይህ ስፖርት ( ቴኒስ) ለሀገራችን ሕፃናት ዕድሉ በብዛት የደረሠ ዓይደለምና በዚህ ሙያ ላይ ከተሠማሩ ወይም ይህን ስፖርት ከሚወዱ ኢትዮጵያዉያን ወንድሞቼና እህቶች ጋር በመምከር ይህን በአብዛኞዉ በነጮች የተያዘዉን ስፖርት ለሀገራችን ህፃናቶች ማድረስ የሚል ህልም አለኝ. እንዲህ ዓይነት አበሾችን በሶሻል ሚዲያና በስማ በለዉ ለማግኝት ሞክሬ ቢከብደኝ ልቤ ከመረጥዎት ከርስዎ ጋር መምከርን መረጥኩ. ቢቻል እዛዉ ዓሜሪካ (እዚህ አዉሮፓ ማግኝት አልቻልኩምና) ዉስጥ በዚህ ( የቴኒስ ስፖርት) ዙሪያ የተሰማሩ ወይም ይህን ስፖርት የሚወዱ ያገር ልጆችን ሊያገናኙኘ ቢችሉ ወይም እንዴት ላገኝ እደምችል ሀሣብ ቢሠጡኘ ብዬ ነዉ. ካስፈለገም ሐሣቤን በይበልጥ መረዳትም ከፈለጉ ልደዉልሎትም እችላለሁ. ምላሽ መሥጠት ካስፈለግዎ ሳይቸገሩብኝ በመረጡት ቋንቋ ቢጠቀሙ ችግር የለዉም.

ከዉድ ጊዜዎ ላይ ቀንሰዉ ሀሣቤን ስለተጋሩኝ በቅድሚያ ዓመሠግናለሁ።


ይህ ድንበር የማያሻግረዉ የደቾቹ ቓንቓ እንግሊዘኞ ፅሁፌን እያበላሸብኝ በመቸገሬ ነዉ በዓማርኛ መፃፌ

ከአክብሮት ጋር
ዓማኑዔል ከሆላንድ
 
 
 
Reply to Amanuel
 
 
 
 
 
info
 
Replying via your email application will message everyone in the conversation.
 
 
 
You are receiving member message notifications emails. Unsubscribe
This email was intended for Zerihun Belay (Service Industry Executive). Learn why we included this.
 
© 2014, LinkedIn Corporation. 2029 Stierlin Ct. Mountain View, CA 94043, USA
 

Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages