ዉድ ኢትዮጵያዊያንና ትዉልደ-ኢትዮያዊያን!!!
አገራችን ኢትዮጲያ በዘመናት ከገጠማት ተግዳሮቶች ሁሉ የከፋ ጊዜ ቢኖር አሁን ነዉ። መራራ የሆነ ጦርነት እየተካሄደ ብቻ ሳይሆን ጠላት አገራችንን እስከወዲያኛዉ የምናጣበት ሁኔታ ሊፈጠር የሚችልበትን አቅጣጫ እንዲይዝ እየጣረ መሆኑን መጠራጠር የለብንም። በአገራችን እየተካሄደ ባለዉ ጦርነትና ወረራ እየታየ ያለዉ ጭካኔ ፤ ክፋትና ጥፋት በጣሊያን ወረራ ዘመን ከነበረዉ የክፋ ሆኗል። ይኸንን ግፍ የሚፈጽመዉን ጠላት በማስቆምና በመደምሰስ አገራችንን ማዳን የሚቻለዉ ከፍተኛ መስዋትነት በመክፈል ላይ ባለዉ የኢትዮጲያ መከላከያ ሰራዊትና ከጎኑ በተሰለፉት የየክልሉ ህዝባዊ ሃይሎች ብቻ ነዉ።
እነዚህ ኃይሎች በጦርነቱ የመጀመሪያ መስመር ላይ ተሰልፈዉ ያለማወላወል ጠላትን እየተፋለሙ ይገኛሉ ። መላዉ የኢትዮጲያ ህዝብም ለህልዉናዉ ከሚፋለምለት ሰራዊት ጎን መቆሙን በተግባር እያሳየ ይገኛል።
በተለያዩ የዉጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትዉልደ ኢትዮጲያዊያንም አገራችንን ለማዳን ከሚፋለመዉ ሰራዊት ጎን መቆማቸዉን ለማሳየት በልዩ ልዩ መንገዶች እርዳታ እያደረጉ ይገኛሉ።
እኛም በላንካስተርና አካባቢዉ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ይኸንኑ ሃላፊነታችንን ለመወጣት እንዴትና በምን መልክ የሚለዉን ለመነጋገርና የዜግነት ግዴታችንን ለመወጣት እንድንገናኝ ይኸንን ጥሪ አቅርበናል። ስለዚህ ቅዳሜ September 25, 2021 ከጠዋቱ 10:00 AM እንዲገኙ በታላቅ አክብሮት ተጋብዘዋል።
ኑ ! መስዋትነት እየከፈለ ያለዉን መከላከያ ሰራዊታችንና መላዉን ህዝባዊ ሃይል ለመርዳት እንመካከር ! ኢትዮጵያ በነጻነቷ ኮርታ ለዘለዓለም ትኑር !
Landisville, PA 17538
Via Zoom
Meeting ID : 859 1903 9923
Passcode : 958152አስቸካይ የስብሰባ ጥሪ
ዉድ ኢትዮጵያዊያንና ትዉልደ-ኢትዮያዊያን!!
አገራችን ኢትዮጲያ በዘመናት ከገጠማት ተግዳሮቶች ሁሉ የከፋ ጊዜ ቢኖር አሁን ነዉ። መራራ የሆነ ጦርነት እየተካሄደ ብቻ ሳይሆን ጦርነቱ አገራችንን እስከወዲያኛዉ የምናጣበት ሁኔታ ሊፈጠር የሚችልበትን አቅጣጫ እየያዘ መሆኑን መጠራጠር የለብንም። በአገራችን እየተካሄደ ባለዉ ጦርነት እየታየ ያለዉ ጭካኔ ፤ ክፋትና ጥፋት በጣሊያን ወረራ ዘመን ከነበረዉ የክፋ ሆኗል። በዚሁ ምክንያት በሽህዎች የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ለሞት ለስደትና ለእርዛት ተዳርገዋል። ብዙ ሽህዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል።
መላዉ የኢትዮጲያ ህዝብም በጦርነቱ ምክንያት እየደረሰ ያለዉን ግፍና መፈናቀል ለመርዳት በተግባር ድጋፍ እያሳየ ይገኛል።
በተለያዩ የዉጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያዊያንና ትዉልደ ኢትዮጲያዊያንም አገራችንን ለማዳን ከሚፋለሙ ወገኖች ጎን መቆማቸዉን ለማሳየትና የተፈናቀሉትንም ለማቋቋም በልዩ ልዩ መንገዶች እርዳታ እያደረጉ ይገኛሉ።
እኛም በላንካስተርና አካባቢዉ የምንገኝ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን እንዴትና በምን መልክ እንርዳ የሚለዉን ተነጋግረን የዜግነት ግዴታችንን ለመወጣት እንድንገናኝ ይኸንን ጥሪ አቅርበናል። ስለዚህ September 25, 2021 ከጠዋቱ በ10:00am ላይ እንዲገኙ በታላቅ አክብሮት ጋብዘንዎታል።
ኑ ! በጦርነቱ ምክንያት የተፈናቀሉና የተጎዱ ዜጎቻቸንን ለመርዳት እንምከር !!!
ኢትዮጵያ በነጻነቷ ኮርታ ለዘለዓለም ትኑር!
የስብሰባ አድራሻ
175 Church St.
Landisville, PA 17538
Via Zoom
Meeting ID : 859 1903 9923
Passcode : 958152
በበጎ ፈቃድ የተቋቋመ አስተባባሪ ግብረኃይል