የህብር ሬዲዮ ጥር 4 ቀን 2006 ፕሮግራም
ለእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለመውሊድ በዓል አደረሳችሁ
<...መንግስት ማስተዳደር ኢኮኖሚውን መምራት ስላቃተው ነው በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ውንጀላ የሚያደርገው...እታሰራለሁ ብዬ አልፈራም። እስር ስላለ ነው ፖለቲካ ውስጥ የገባሁት...> ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰሞኑን የመንግስት ፓርቲያቸው ላይ የከፈተውን ክስ አስመልክቶ ለህብር ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ
ህብር ለሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በርከት ያሉ አቄዎችን አቅርበናል።
ከተቃዋሚዎች ጋር ለምን እንደማይተባበሩ፣ ብቻቸውን ሰልፍ በማድረግ ብቻ ለውጥ ያመጡ እንደሆን? ኢህአዴግ ከጀርባቸው አለ ስለመባሉ ተጠይቀው ምላሽ ሰጥዋል ተከታተሉት።
ዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ወቅታዊ ስለሆነው አደገኛ ጉንፋን ወቅታዊ ምላሽ ሰጥተዋል።
የቀድሞ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስቴር ኤርያል ሻሮን ምንታ ማንነትና ሰሞኑን ሞታቸውን ተከትሎ ስለተሰጡ አስተያየቶች ዘገባ
በ2013 የኢትዮጵያ የአገር ውስጥ ፖለቲካ ከየት ወዴት ? የሕወሃት የቡድን ፍጥጫ በአነ ማን አሸናፊነት ይጠናቀቃል? ልዩ ቅኝት
ሌሎችም ዝግጅቶች
ዜናዎቻችን
በቬጋስ በከባድ ጉንፋን ሶስት ሰዎች መሞታቸው ይፋ ሆነ
ባለስልጣናት ህብረተሰቡ ክትባት እንዲወስድ ጠይቀዋል
የኢትዮጵያዊው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት መሪ ከህውሃት ሰዎች የግድያ ማስፈራሪያ ደረሳቸው
የካናዳ ፖሊስ ጉዳዩን እየመረመረ ነው
የጃፓን ጠቅላይ ሚነ ስትር የአበበ ቢቂላን ቤተሰቦችን በአዲስ አበባ ጉብኝታቸው ወቅት ያነጋግራሉ
ቀዳማዊ ሀይለስላሴ ለዋሽንግተን ከተማ የሰጡት የዝሆን ጥርስ መሰረቅ ይፋ ሆነ
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አገር ቤት ሲገቡ እታሰራለሁ ብለው እንደማይፈሩ ገለጹ
የቀድሞው የቤንሻንጉል ክልል ፕሬዝዳንት በእስራት ተቀጡ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን
(ህብርን ከዘሐበሻ፣አፍሮ አዲስ ድህረ ገጾችእና በሌሎችም ያዳምጡ። በተጨማሪ በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)
Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።