> https://soundcloud.com/hiber-radio-las-vegas-1/hiber-radio-030214-030914
> የህብር ሬዲዮ የካቲት 23 ቀን 2006 ፕሮግራም
>
> እንኳን ለአድዋ ድል 118ኛው በዓል አደረሳችሁ!!
>
> <...በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ዕድገት የሚባለው ጥቂቶች የተንደላቀቀ ኑሮ የሚኖሩበት ብዙዎች በሚያስፈራ ድህነት ውስጥ የወደቁበት... ውጭ ውጩን በህንጻዎች ግንባታ የተጋረደ ውስጡን ግን የከፋ ሙስና የተንሰራፋበት ሁኔታ ነው ያለው ይሄ አደገኛ ነው ...>>
>
> ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የቀድሞው የዓለም ባንክ የኢኮኖሚ አማካሪ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ቃለ ምልልስ(ሙሉውን ያዳምጡ)
>
> <...የአድዋ ድል የመላው ጥቁር ሕዝቦች ድል ነው ይሄን ማንም አይነጥቀንም ። ዛሬ ለሚረገጠው መብታችን ግን አባቶቻችን አንድ ላይ እንደቆሙት በጋራ መቆም አለብን ...>
>
> አቶ ስዩም መንገሻ የአንድነት ዋና ጸሐፊ የአድዋን 118ኛ በዓልን በአዲስ አበባ ስላከበሩበት ሁኔታ ተጠይቀው ከሰጡት ምላሽ(ሙሉውን ያዳምጡት)
>
> <<...ለረዳት አብራሪው ሀይለመድህን አበራ ፊርማ ማሰባሰብ ጀምረናል ።ፊርማው ለስዊዝ ባለስልጣናት የሚቀርብ ነው...>>
>
> አቶ ጴጥሮስ አሸናፊ ረዳት አብራሪው እንዲፈታ ጥረት የሚያደርገው ግብረ ሀይል አባል ለህብር ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ
>
> የህብር ሬዲዮ አራተኛ ዓመት በዓል ልዩ ሪፖርት
>
> ሌሎችም ዝግጅቶች
>
> ዜናዎቻችን
>
> ሙስና ኢትዮጵያን እያጠፋት መሆኑን የቀድሞው የዓለም ባንክ የኢኮኖሚ አማካሪ ገለጹ
>
> ሱዳን በአገሯ የኢትዮጵያ አማጺያንን እያሰለጠነች መሆኑ ተገለጸ
>
> ኢትዮጵያውያን ግፍ በዛብን ብለው የሳውዲን እስር ቤት ሰብረው ወጡ
>
> ጩኸትና የጥይት ተኩስ ተሰምቷል
>
> የአድዋ ድልን መዘከር ብቻ ሳይሆን በአንድ ላይ ቆመው ለመብታቸው እንዲታገሉ ጥሪ ቀረበ
>
> ተቃዋሚዎችም እንዲተባበሩ ተጠይቋል
>
> ኩዌት ኢትዮጵአውያን የጉልበት ሰራተኞችን አልቀበልም አለች
>
> ረ/አብራሪ ሀይለመድህንን የስዊዝ መንግስት ጥገኝነት እንዲሰጠው የሚጠይቅ ፊርማ መሰብሰብ ተጀመረ
>
> የመጀመሪያው ድሪም ላይነር አብራሪና የአየር መንገዱ ም/የስራ ሀላፊ በፈቃዳቸው ለቀቁ ተባለ
>
> አንድነት በባህር ዳር ያደረኩትን ተቃውሞ አዲስ አበባን ጨምሮ በ12 የአገሪቱ ከተሞች ይቀጥላል አለ
>
> ሌሎችም ዜናዎች አሉ
>
> (ህብርን ከዘሐበሻ፣አፍሮ አዲስ ድህረ ገጾችእና በሌሎችም ያዳምጡ። በተጨማሪ በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)
>
> Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።
>
>
>
> --
> Habtamu Assefa
> Producer of Hiber radio Las Vegas
> 702-589-6347
> (www.zehabesha.com,www.afroaddis.WordPress.com & www.
> KRLV1340AM.com )
>