Hiber Radio full program with updated info

0 views
Skip to first unread message

Habtamu Assefa

unread,
Apr 9, 2014, 12:02:27 AM4/9/14
to ethiopian-worldw...@googlegroups.com, Dagnachew Teshome, boycot...@googlegroups.com

          የህብር ሬዲዮ መጋቢት 28  ቀን 2006 ፕሮግራም

 <...አቶ ኦኬሎ አኳይ ከጁባ ታፍኖ ማዕከላዊ ነው።...አኪልዳማ አይነት ድራማ ሊሰራበት ይችላል።የወያኔ እሱን መያዝ በጋምቤላ ተፈጽሞ ለዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ማስረጃው የቀረበውን የዘር ጭፍጨፋ ወደሁዋላ አያስቀርም። ማስረጃው ወጥቷል ...  >

አቶ ኦባንግ ሜቶ  በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተጠይቀው ለህብር ከሰጡት (ሙሉውን ያዳምጡ)

<... አሁን ያሉት ሰዎች የደገሱልን የእርስ በእርስ እልቂት ነበር። የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ሕዝብ  በመሆኑ ያንን የደገሱለትን እልቂት አክሽፎታል።...አሁንም እነዚህ ሰዎች ያዋረዱትን የአገራችንን ባንዲራ  በጋራ ሙስሊምም ሆነ ሙስሊም ያልሆነው በጋራ ለመብቱ መቆም ባንዲራዋን ነጻ ማውጣት  አለበት ...>  ሐጂ ነጂብ መሐመድ የፈርስ ሒጅራ ፕሬዝዳንት በቬጋስ በኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ካደረጉት ንግግር መሐከል ቀሪውን ያዳምጡት

የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ሃያኛ ዓመትን የተመለከተ ወቅታዊ ዘገባ 

የህወሃት መሪዎች ሱዳንን ከህልውናቸው ጋር በማያያዛቸው ስለ ሱዳን ህልውና ለአሜሪካ ዲፒሎማቶች የተናገሩበትን  የዊክሊክስ ያጋለጣቸውን የምስጢ ር መልዕክቶች (ልዩ ዘገባ )

 

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

የኖርዌይ አምባሳደር ማዕከላዊ በመሄድ ከደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱትን የቀድሞ የጋምቤላ ፕ/ት ለማየት ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ

አሜሪካ ለግብጽ የምትሰጠው ዕርዳታ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እየዋለነው ሲሉ ብቸኛው የተቃዋሚ የፓርላማ አባል ወቀሳ አቀረቡ

ታንዛኒያ 43 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳልፋ ሰጠች

የአረና አመራሮችና አባላት ዛሬም ትግራይ ውስጥ ተደበደቡ

የታሰሩም አሉ

አንድነት በጠራው የዛሬው የደሴ የተቃውሞ ሰልፍ ከ60 ሺህ በላይ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ቁጣውን ገለጸ

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ለሁለተኛ ጊዜ ታሰረ

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ለማስፈታት እንዳልተሳካለት ገልጾ ለሱ ደህንነት ሲባል ሁኔታው እንዳይጋጋል ጠየቀ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፓሪስ የማራቶንን ሪኮርድ ሰበረ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

(ህብርን ከዘሐበሻ፣አፍሮ አዲስ ድህረ ገጾችእና በሌሎችም ያዳምጡ።  በተጨማሪ  በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት 1340 .ኤም  የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።






--
Habtamu Assefa
Producer of Hiber radio Las Vegas
702-589-6347
(www.zehabesha.com,www.afroaddis.WordPress.com & www.
KRLV1340AM.com )

in...@ecadforum.com

unread,
Apr 9, 2014, 12:02:30 AM4/9/14
to boycot...@googlegroups.com
Thank you for contacting http://ecadforum.com

In the meantime you can follow us at

Facebook: https://www.facebook.com/ecadfethiopia -
Twitter: http://www.twitter.com/ecadf or
Goole+: https://plus.google.com/s/ecadf#108017171073154828690/posts



Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages