መጽሐፍ ቅዱስ እና ሰማኒያ አሃዱ

754 views
Skip to first unread message

Kabe

unread,
Apr 16, 2013, 2:57:55 AM4/16/13
to adama-university-a...@googlegroups.com

መጽሐፍ ቅዱስ እና ሰማኒያ አሃዱ



ለሥጋ ለባሽ ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን የማወቅ፣ የማመንና የመዳን መብት ተሰጥቶታል፡፡ ነገር ግን እንኳን ሰው መላእክትም ቢሆኑ በተጻፈው ላይ መጨመር ወይም መሸቀጥ፣ መቀየጥ፣ መቀነስ፣ መበረዝ፣ ማጉደል፣ ማጣመም አልተፈቀደላቸውም፡፡

የሕያውን አምላክ ቃል ይቅርና «የሰውም ቢሆን እንኳን…» ያለባለቤቱ ፈቃድ ማን እንደፈለገው ተነስቶ የመቀየር መብት እንደሌለው በገላ. 3፡15 ተጽፎአል፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ክቡር ቃሉን እንዳለ እንዲቀበል እንጂ ማንም እንደፈለገ እንዳያጣምመው ማስጠንቀቂያ­ች ተሰጥተዋል፡-

1ኛ) በሕግ (በሙሴ) መጽሐፍት፡- ዘዳ. 4፡2፤ 12፡32፤ 13፡1

2ኛ) በመዝሙራት፡- ምሳ. 30፡6

3ኛ) በነቢያት፡- ኤር. 26፡2

4ኛ) በወንጌል፡- ማቴ.5፡18-20

5ኛ) በሐዋርያት ሥራ፡- ሐዋ. 20፡29-31
6ኛ) በመልእክቶች፡- ገላ.1፡8፣9

7ኛ) በራእይ፡- ራእ. 22፡18-19

ክቡር የሆነውን ቃል፡-

ተመልከት (ኤር.2፡31)፤ አንብብ (ኢሳ.34፡16) እንጂ፡-

(1) ከተጻፈው አትለፍ 1ቆሮ. 4፡6

(2) አትጨምር ወይም አታጉድል ራእ.22፡18-19፤ ዘዳ. 4፡2፤

(3) አታጣምም 2ጴጥ. 3፡15-16  

(4) ለራስህ አትተርጉም 2ጴጥ. 1፡20

(5) አትግፋ ሐዋ. 7፡38-39

(6) አትናቅ ሐዋ. 13፡40፤ ዕባቆ. 1፡5

(7) አታወላውል ኢያ.1፡7-8    

(8) አትሻር ማቴ. 5፡19         

(9) አትስረቅ ኤር. 23፡30

(10)  ከራስህ ልብ አትናገር ኤር.23፡16

(11) በውሸት አትቀላቅል 2ቆሮ.4፡1-3

(12) አንዲትም ቃል አታስቀር ኢያሱ 8፡35

 

የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች (በአማርኛ)

በኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ በግዕዝ በአማርኛና በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋ­ች ተተርጉሞአል፡፡ በአማርኛ ከተተረጎሙት መካከል የ1879 ዓ.ም. (1886 እ.አ.አ) የታተመውና በተለምዶ የቁም ጽሑፍ ወይም የአሮጌው አማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ የሚባለው እና የ1954 ዓ.ም. (1962 እ.አ.አ)፡፡

አንዳንድ የእምነት ክፍሎች ባላቸው የእምነት አቋም ላይ በቂ መልስ መስጠት ያስችለናል በሚል እምነት ይሁን ወይም የተሻለ የትርጉም ሥራ ለመሥራት በማሰብ የየራሳቸውን የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች እያዘጋጁ ነው፡፡ ለምሳሌ በተለምዶ ሰማኒያ-አሃዱ እየተባለ የሚጠራው ከበፊቱ 66 መጽሐፍትን ከያዘውና ቀድሞ ሲሠራበት ከቆየው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ ተጨማሪ መጽሐፍትን በማከል በ1980 ዓ.ም. ሲታተም፣ በተመሳሳይ ዓመት «መጽሐፍ ቅዱስ ቀለል ባለ አማርኛ የተተረጎመ» የሚልም ሌላ ትርጉም ወጥቶ ነበር፡፡ የዚህ ትርጉም አላማ አማርኛ ሁለተኛ ቋንቋቸው ለሆኑ ሰ­ች ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑም ተገልጾአል፡፡ ሌላው ደግሞ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሚባል በ1993 ዓ.ም. ታትሞአል፡፡

 

ስለ ሰማኒያ አሃዱ አንዳንድ ነጥቦች፡-

መቼና ለማን ታተመ፡- በ1980 ዓ.ም. «…ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን» ይላል፡፡

ለምን ታተመ?፡- መቅድም ውስጥ እንዲህ የሚል ተጽፎአል፡- በ1947 ዓ.ም. 52 የብሉይና 27 የአዲስ ኪዳን በድምሩ 79 መጻሕፍት የያዘው ትልቁ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ የታተመው ተሰራጭቶ በማለቁ «ከቤተ ክርስቲያናችን ውጭ የሆኑትንና ከግዕዙ ጋር የማይስማሙትን ቃላትና ዐረፍተ ነገሮች ቅዱስ ሲኖዶሳችን ከተመለከታቸውና ከአስተካከላቸው በኋላ እንደገና እንዲታተም አደረግን» (መቅድም ተመልከቱ)፡፡

 

ሰማኒያ አሃዱ (81) ስሙ ነውን? በተለምዶ ሰማኒያ አሃዱ (81) ይባል እንጂ በውስጡ 40 የብሉይ ኪዳን 18 ተጨማሪ እና 27 የአዲስ ኪዳን በድምሩ 85 መጽሐፍት የያዘ ነው፡፡ (ማውጫውን ተመልከቱ)፡፡

በሥራው ጥራት ይታመንበታል? «ከግእዙና ከአማርኛው ምንባብ ጋር የማይገናዘቡና ከምርመራ ያመለጡ ባዕዳን ቃላት ቢገኙ የመጽሐፍ ኅትመት በአንድ ጊዜ ፍጹም ሊሆን ስለማይችል ከአንባቢያን የሚቀርቡልንን ሰብስበን እንደገና በሚታተምበት ጊዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ታርሞና ተስተካክሎ ሊታተም ይችላል፡፡» (መቅድም ተመልከቱ)

 

ቤተክርስቲያን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ትስማማ ወይስ መጽሐፍ ቅዱስ ከቤተ ክርስቲያ አባባል ጋር᐀ «ከቤተ ክርስቲያናችን የሃይማኖት አነጋገርና ከግዕዙ ጋር እንዲስማሙ የተደረጉት ቃላትና ዐረፍተ ነገሮች» አሉ ይላል፡፡ (መቅድም ተመልከቱ)፡፡

የሰማኒያ አሃዱ ተጨማሪ መጽሐፍት- ከ1954 እትም ጋር ሲነጻጸሩ፡-

1954 እትም፡- «ሄኖክ ሞትን እንዳያይ በእምነት ተወሰደ…»ዕብ.11፡5

ሰማኒያ አሃዱ፡- «…ይሙት ይድንም የሚያውቅ የለም» መ. ሄኖክ 4፡2

♦♦

1954 እትም፡- «አካሄዳችሁ ገንዘብን ያለ መውደድ ይሁን፣ ያላችሁም ይብቃችሁ…» ዕብ. 13፡5

ሰማኒያ አሃዱ፡- «…ገንዘብ በቃኝ አትበል» መጽሐፈ ሲራክ 5፡1

«ቀምተህ ላመጣኸው ገንዘብ አትሳሳ» መ.ሲራክ 5፡8

«እንግዲህስ ገንዘብ በቃኝ አልቸገርም አትበል»  ሲራክ 11፡24

♦♦

1954 እትም፡- «የዓለምን  ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ» ዮሐ.1፡29

ሰማኒያ አሃዱ፡- «የፍየል ጠቦት ሠውቶ በደሙ የዓለሙን ኃጢአት ሁሉ አስተሰረየ፡፡» መ.ኩፋሌ 7፡2

♦♦

1954 እትም፡- «..በትንሣኤስ እንደ እግዚአብሔር መላእክት በሰማይ ይሆናሉ እንጂ አያገቡም አይጋቡምም፡፡» ማቴ.22፡29-30

ሰማኒያ አሃዱ፡- «የእግዚአብሔር መልአክት ከሰው ተጋብተው ወለዱ» መጽሐፈ ኩፋሌ 6፡9

♦♦

1954 (66ቱ)፡- «ለሰ­ችም አንድ ጊዜ መሞት ከእርሱ በኋላም ፍርድ እንደ ተመደበባቸው» ዕብ. 9፡27፡፡

ሰማኒያ አሃዱ፡- «ለሞተ ሰው ተዝካር ማውጣት አትተው» ሲራክ 7፡33

♦♦

1954 እትም፡- «…ጌታ ሆይ፣ አጋንንት ስንኳ በስምህ ተገዝተውልናል አሉት» ሉቃ. 10፡17፡፡ «…በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤» ማር.16፡17፡፡ «እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል» ያዕቆብ 4፡7፡፡

ሰማኒያ አሃዱ፡- «… የደቀቀ ዕጣን አምጥቶ የዚህን ዓሣ ጉበቱንና ልቡን ጨምሮ አጤሰው፡፡ ያም ጋኔን መዓዛው በሸተተው ጊዜ እስከ ላይኛው ግብጽ አውራጃ ድረስ ሸሸ ይኸም መልአክ ጋኔኑን አሥሮ አጋዘው» መጽሐፈ ጦቢት 8፡2-3   «ክፉ ጋኔን ያደረበት ቢኖር ወይም የረከሰ ረቂቅ ጋኔን ያደረበት ቢኖር ጉበቱና ልቡን ለዚያ ሰው በፊቱ ያጤሱለታል ሴትም ብትሆን ያጤሱላታል ከዚያ በኋላ አይታመምም» (6፡7)፡፡

♦♦

1954 እትም፡- «በዚያም ቀን እግዚአብሔር ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን ጠማማውንም እባብ ሌዋታንን በጠንካራ በታላቅም በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፣ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል፡፡» ኢሳ.27፡1 በማለት ሌዋታን እባብ እንደሆነ ይናገራል፡፡ «ሌዋታንን ለማንቀሳቀስ የተዘጋጁ ቀኑን የሚረግሙ ይርገሙት» ኢዮብ 3፡8 ይላል፡፡

ሰማኒያ አሃዱ፡- «…ለምትወዳቸው ለጻድቃን ምግብ ይሆኑ ዘንድ ሌዋታንና ብሔሞት ጠበቅሃቸው» መ. ዕዝራ ሱቱኤል 4፡52  ይላል፡፡

በሰማነያ አሃዱ (1980 ዓ.ም.) ከአዳ=ስ ከ=ዳን የተበረዘ< ጥቅሶች በከፊል

ሉቃ. 1፡48 «የባርያይቱን ውርደት» -ወደ- «የባርያውን ትሕትና»

2ቆሮ.6፡16፡- «ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው᐀» -ወደ- «የእግዚአብሔር ታቦትንስ በጣዖት ቤት ውስጥ የሚያኖር ማን ነው?»

ራእ.14፡1 «ስሙና የአባቱ ስም» -ወደ- «ስሙና የአባቱ ስም የመንፈስ ቅዱስ ስም»

ራእ.22፡15፡- «ውሻዎችና አስማተኛ­ች ሴሰኛችም ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትንም የሚያመልኩት ውሸትንም የሚወዱና የሚያደርጉ ሁሉ በውጭ አሉ፡፡» -ወደ- «አምስቱ ውሾች ግን ከዚያች አገር ወጥተው ይሄዳሉ፡፡ እሊህም ሥራይን የሚያደርጉ ሴሰኞች ነፍሰ ገዳዮችም ጣዖትን የሚያመልኩና የሐሰትን ሥራ የሚወዱት ሁሉ ናቸው፡፡»

ስለ እስራኤል ታቦት

1ኛ. ወደ ባቢሎን ወሰዱት፡-  «እግዚአብሔርን የሚያገለግሉበት ንዋየ ቅዱሳቱን ጥቃቅኑንምና ታላላቁንም ዕቃ ሁሉ የእግዚአብሔር ማደሪያ ታቦትንም ከቤተ መንግሥት ዕቃ ቤትም ያለውን ሣጥኑን ሁሉ ማርከው ወደ ባቢሎን ወሰዱ» መጽሐፈ ዕዝራ ካልዕ 1፡54 አስተያዩት 2ዜና 36፡19፡፡

2ኛ. ምድርም ተቀብላ ዋጠችው፡- ተረፈ ኤርምያስ 8፡13 «ባሮክና ኤርምያስም ወደ ቤተ መቅደስ ገቡ የሚያገለግሉበትንም ዕቃ ሁሉ ጌታ እንዳዘዛቸው ለምድር ሰጧት ምድርም ያንጊዜ ተቀብላ ዋጠችው፡፡ ቁ.18 «ያንጊዜም ኤርምያስ የቤተ መቅደሱን መክፈቻ ይዞ ከከተማ ወደ ውጪ ወጣ፡፡» ቁ.19 «ይህንንም መክፈቻ ፀሐይ የእግዚአብሔርን ማደሪያ የቤተ መቅደስን መክፈቻ ተቀበል ብሎ በፀሐይ ፊት ጣለው፡፡» ይላል፡፡ የእስራኤልን ታሪክ ከአክሱም ጽዮን ማሪያም ታቦት ጋር አነጻጽሩት፡፡ ታቦቱ ኢትዮጵያ ገብቶአል ከሚባልበት ከብዙ ዘመናት በኋላ እስራኤል የነበረው ታቦት ወይ ወደ ባቢሎን ተወስዶአል ወይ ምድር ውጣዋለች አልያም አልታወቀም፡፡

♦♦ ስለ ሥላሴ፡- «ሥላሴ ከሰው ይልቅ የገለጡልህ ምሥጢር የለምና ከግብር ገብተህ ባሕርየሥላሴን አትመርምር፡፡» መጽሐፈ ሲራክ 3፡23  ሥላሴ ከሰው ይልቅ የበለጠ የገለጡት ነገር ከሌለ ከሰው በምን ይሻሉ ይሆን᐀ «አትመርምር» ከተባለስ ሥላሴ እግዚአብሔር አለመሆኑን ማሳየት አይሆንም ወይ ለምን ቢባል ሐዋ. 17፡26 እግዚአብሔርን እየመረመሩ እንዲያገኙት ቃሉ ፈቅዶአልና፡፡

♦♦ ስለ መጽሐፈ ሄኖክ  (ሄኖክ ከተወሰደ በኃላ በመላ እንደ ተጻፈ ሲናገር)፡- «ሄኖክ ተሠውሮ ያየው በዚህ መላ ተፈጸመ» ይላል መ.ሄኖክ 42፡16፡፡

♦♦ 66 አመታት በእንቅልፍ፡- ተረፈ ኤርምያስ 9፡1 «አቤሜሌክም… በለስ ያለባትንም ሙዳይ ተንተርሶ ስድሳ ስድስት ዓመት ተኛ ከመኝታውም አልነቃም፡፡»

♦♦ 1.5 ኪ.ሜትር ቁመት ያላቸው ሰዎች፡- «እነሱም ፀንሰው ረጃጅሞች አርበኞች ልጆችን ወለዱ ቁመታቸውም ሦስት ሦስት ሺህ ክንድ ነው» መጽሐፈ ሄኖክ 2፡12

በመጨረሻም ሊዘነጋ የማይገባው ነጥብ፡- ከ66ቱ መጽሐፍት ውጭ ለሆኑት መጽሐፍት የተሰጣቸው የጋራ ርዕስ «ተጨማሪ» የሚል መሆኑን ልብ ይሏል፡፡ በራእይ 22፡18 ያለውን ቃል የመሠለ ከባድ ማስንቀቂያ ባለበት  መጽሐፍ ብቻ ከሃያ ሦስት የማያንሱ የቃላት ለውጦችና ጭማሪ­ች ተደርገዋል፡፡

Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages