( Let The Truth Shine)

105 views
Skip to first unread message

Kabe

unread,
Apr 25, 2013, 4:04:26 AM4/25/13
to adama-university-a...@googlegroups.com



View Profile



(  Let The Truth Shine)
ወንድም  በረከት ማቴዎስ 1ጢሞቲዎስ 3:16
Quote from:1ጢሞ.3:16
እግዚአብሄርንም የመምሰል ምስጥር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው; 
በስጋ የተገለጠ,
በመንፈስ የፀደቀ,
ለመላእክት የታየ,
በአህዛብ የተሰበከ,
በአለም የታመነ,
በክብር ያረገ::

መግቢያ
ኤርሚያስ 8:8
Quote from:ኤር.8:8

ኤር.8:8 እናንተስ:: ጥበበኞች ነን የእግዚአብሄርም ህግ ከእኛ ጋር ነው እንዴት ትላላችሁ? እነሆ, የፀሀፊ ብርእ ሀሰተኛ ነው በሀሰትም አድርጎአል::


በኤርሚያስ መፅሀፍ ላይ እንደተገለፀው ባለፉት ዘመናት ብዙ የሀይማኖት ሰዎች በተለያየ የሀይማኖት ጉዳይ ላይ ብዙ ነገር ፅፈዋል.ፅሁፎቻችው የእግዚeብሄርን ህግ እስከ ካዱ ድረስ , የሚያሳየው የሚፀፉት ለእግዚeብሄር ቃል በቂ ጊዜ ባለመስጠት የራሳችውን የግል ሀሳብ ለመግለፅ ባላችው ፍላጎት ነው.በኤርሚያስ ትንቢት እንደተገለፀው , የዚህን eይነት ስሁፎች ሀሰተኛ ይላችዋል.በዚህ eጭር ፅሁፌ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ስለተፃፈው ሀሰተኛ ፅሁፍ " Global Good News Literature” (GGNL )ስለተባለው በጭፍንነት  ወይም በተሳሳተ መረዳት የፃፈውን አውጥቻለሁ
www.globalgoodnews.org/only_jesus.htm

በዚህ ጽሁፌ በአጭሩ  GGNL በፃፈው ላይ የራሴን መረዳት በሁለት አርስት አቅርቢያለሁ
    1.የእግዚአብሄርን አንድነት( Oneness of God )

    2.የአንዱ አምላክ ትምህርት የውሀ ጥምቀትን በተመለከተ(   Oneness doctrine concerning water baptism.)
ይሄኛው ፅሁፌ በመጀመሪያው አርስት ላይ ያተኮረ ይሆናል ሁለተኛውን አርስት  በሚቀጥለው ጊዜ አቀርባለሁ.

      1:1  የመፅሀፍ ቅዱስ ብዙ ቁጥር (  The plural words of the Bible)
GGNL እንደፃፈው ከሆነ በዘፍጥረት 1:36 ,3:22 እና ኢሳይያስ 6:8 መፅሀፍ የተፃፈው እግዚአብሄር በአካል ብዙ እንደሆነ የሚያሳይ ነው.የትኛውም የእብራዊ ፀሀፊም ሆነ በእነዚህ ጥቅሶች ላይ ጥናትን ያደረጉ ሊቆች  በፍፁም የ GGNL ን 21 ኛው ክፍለዘመን ሰሀፊዎች ያሉትን  አልደገፉትምም.
ዘፍጥረት 1:26,27


Quote from:ዘፍ.1.26

ዘፍ.1.26; እግዚአብሄርም አለ:: ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር; የባህር አሶችንና የሰማይ ወፎችን, እንስሳትንና ምድርን ሁሉ, በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ::


የዚህ ጥቅስ እውነተኛ አባባል ምን እንደሆነ ለመረዳት  በአራት የተለያዩ አቅጣጫዎች  አስቀምጫቸዋለሁ.
1.ብዙ ቁጥር  (  plurality of a word) የተለያዩ አካልን መኖራቸውን ያመለክታል ወይ?

መፅሀፍ ቅዱስ የሁሉንቻዩ አምላክ ሀሳብ , እቅድ,እና ትእዛዝ እስከ ሆነ ድረስ,የመፅሀፍ ቅዱስን ዘላለማዊ እውነተኛ ቃል በሰው አገላለፅ መተርጎም አዋቂነት አይደለም.በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የብዙ ቁጥሮችን በጠቃቀም ጥቂት  እንመልከት:
Quote from:ዳኔል 2:36

ዳአኔል 2:36  ህልሙ ይህ ነው; አሁንም ፍቺውን በንጉሱ ፊት እንናገራለን:

:
መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ቁጥሮች ሁልጊዜ የተለያየን አካል ያሳያሉ ብለን ካጠቃለልን,
ነብዩ ዳአኔል ሶስት ወይም የበለጠ  የተለያየ አካል አለው ማለት ነው?
Quote from:ዘፀአት 32:4

ዘፀአት 32:4. ዘፀ.32:4; ከእጃቸውም ተቀብሎ በመቅረጫ ቀረፀው, ቀልጡዋ የተሰራ ጥጃም አደረገው; እርሱም:: እስራኤል ሆይ, እነዚህ ከግብፅ ምድር ያወጡህ አማልክትህ ናቸው አላቸው:

:
በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ብዙ ቁጥሮች ሁልጊዜ የተለያየን አካላትን  ያሳያሉ ብለን ከደመደምን,
ይሄ ጥጃም ሶስት ወይም ከዛ በላይ የተለያየ አካል አለው ማለት ነው? እኔ ቀልጦ ከተሰራ ጥጃ ያነሰ ዋጋ ያለውን አምላክ አላገለግልም
Quote from:ዘፍ.21:7

ዘፍ.21:7፤ ደግሞም። ሣራ ልጆችን እንድታጠባ ለአብርሃም ማን በነገረው? በእርጅናው ልጅን ወልጄለታለሁና አለች


ብዙ ቁጥሮች የተለያየ አካላትን ያመለክታሉ ብለን ካልን,ይሽአቅ ሶስት ወይም ከዛ በላይ የተለያየ አካል አለው ማለት ነው?
በእነዚህ ምእራፎች ውስጥ ያሉት ቃላት የተለያዩ አካላትን እስካላሳዩን ድረስ,ከዳንኤል ከጥጃ,ይሽአቅም ከሚያመልከው አምላክ ያነሰ ሀይል ያለው አምላክ ማምለክ አልፈልግም,መፅሀፍ ቅዱስ ብዙ ቁጥሮችeን ለነብዩ ዳንኤል ,ለጥጃውና ለይሽአቅ ቢጠቀምም,የተለያዩ አካላት ናቸው ለማለት ምክንያት የለንም,ታድያ ምን አለበት መፅሀፉ  ለፈጣሪና ለሁሉ ነገር ባለቤት  ለሁሉን ቻዩ አምላክ  ቢጠቀምበት.
እነዚህን መፅሀፎች  እንዳየናቸው ከሆነ,ብዙ ቃላት የአካልን ብዛት አያመለክቱም
         2.ኤል-ኦ-ሂም(El-o-heem)የሚለውን ብዙ ቃል ትርጉሙን እንመልከት
የእግዚአብሄርን ቃል ብቻ የሚለውን  በትኩረት  ስናየው,በእብራውያን የቁዋንቅዋ ጥናት ኤል-ኦ-ሂም የሚለው ቃል ምንን ይገልፃል ብሎ ማጥናት ብልህነት ነው.የእግዚአብሄርን ቃል እኛ እንደፈለግነው ሳይሆን በማስተዋልና በእውነት ስንረዳው,የመፅሀፍ ቅዱስ ፀሀፊዎች ምን መግለፅ እንደፈለጉ መረዳትን እናገኝ ነበር ለመለኮት መባዛት  ምክንያት የተተረጎመውን በዘፍጥረት 1:26 "ኤል-ኦ-ሂም" የሚለውን የእብራዊያን ቃል ስናጥና የተለያየ አካል አያሳየንም.ሁሉን ቻይ አምላክ
(  Almighty God )የሚለውን ቃል በእብራዊያን ወይም በግሪክ ብሉይ እና አዲስ ኪዳን ያለውን ግንኙነት ስናየው,"በብዙ ቁጥር የተገለጥው ነጠላ ትርጉም የእግዚአብሄርን ታላቅነት የሚያሳይ ነው".በዘፍጥረት 1:26 የተፃፈው ብዙ ቁጥር ሁሉን ቻዩ አምላክ የተለያየ አካል እንዳለው የሚያሳይ ሳይሆን ,ብዙ ስልጣን እና ሀይል እንዳለው የሚያሳይ ነው.
            3. እግዚአብሄር በአካል  ብቻውን እንደሆነ የሚያሳዩ ጥቅሶች.
Quote from:ዘዳግም 32:39

ዘዳ.32:39; አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ, ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ እዩ; እኔ እገድላለሁ, አድንማለሁ; እኔ እመታለሁ, እፈውስማለሁ; ከእጄም የሚያድን የለም::


     ከእግዚአብሄር ጋ ሌላ   የተለየ አካል ያለው እግዚአብሄር የለም!
Quote from:ኢሳ.44:24

ኢሳ.44:24; ከማህፀን የሰራህ, የሚቤዥህ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል :: ሁሉን የፈጠርሁ, ሰማያትን ለብቻዬ የዘረጋሁ ምድርንም ያፀናሁ እግዚአብሄር እኔ ነኝ; ከእኔ ጋር ማን ነበረ?


    ሀያሉ እግዚአብሄር አጠገቡ ሌላ አካል ያለው እግዚአብሄር እንዳለ   
    አያውቅም !
Quote from:ኢሳ.44:6

ኢሳ.44:6; የእስራኤል ንጉስ እግዚአብሄር, የሚቤዥም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር እንዲህ ይላል:: እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ሁዋለኛ ነኝ, ከእኔ ሌላም አምላክ የለም

::
    በመለኮታዊ ሀይል እግዚአብሄርን የሚመስል ወይም የሚስተካከል
   ሌላ የተለየ አካል ያላቸው መለኮቶች ወይም እግዚአብሄሮች የሉም!     
Quote from:ኢሳ.44:8

ኢሳ.44:8; አትፍሩ አትደንግጡም; ከጥንቱ ጀምሬ አልነገርሁዋችሁምን? ወይስ አላሳየሁዋችሁምን? እናንተ ምስክሮቼ ናችሁ:: ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም; ማንንም አላውቅም

::
      ከእግዚአብሄር መለኮታዊ አካል አጠገብ ሌላ
      አካል ያላቸው አምላኮች የሉም በእግዚአብሄርም
      ዘንድ አይታወቁም!         
Quote from:ኢሳ.46:9

ኢሳ.46:9; እኔ አምላክ ነኝና, ሌላም የለምና የቀድሞውን የጥንቱን ነገር አስቡ; እኔ እግዚአብሄር ነኝ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም::


    እግዚአብሄርን የሚመስሉ ወይም የእግዚአብሄር
    ለላው አካል ተብለው የሚታወቁ አማልክት
     የሉም!               
Quote from:ነህ.9:6

ነህ.9:6; አንተ ብቻ እግዚአብሄር ነህ; ሰማዩንና የሰማያት ሰራዊታቸውንም  ሁሉ, ምድሩንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ, ባህሮቹንና በእነርሱ ውስጥ ያለውን ሁሉ, ፈጥረሀል, ሁሉንም ህያው አድርገኸዋል; የሰማዩም ሰራዊት ለአንተ ይሰግዳሉ:


    እሱ ብቻውን  ነው , የተለየ አካላት ያላቸው መለኮቶች የሉም!!
እውነቱን ለመቀበል ከፈለግን,ከነዚህ ጥቅሶች በግልፅ እንደምንረዳው  የተለያየ አካላት ያላቸውን አማልክቶችን  eናይም.እግዚeብሄር ሶስት የተለያዩ eካላት ካሉት,እንደት እነዚህ ሁሉ የመፅሀፍ ቅዱስ ጥቅሶች የታላቁን አምላክ ብቸኝነት ሊያንፀባረቁ ይችላሉ. ከላይ በተመለከትናቸው ምእራፎች እግዚeብሄር ራሱን ለመግልፅ የተጠቀመባቸውን ቃላት እና ግስ(   adverb ) ስንመለከት, እግዚeብሄር በመለኮት ብቻውን ያለ eምላክ እንደሆነ eጉልቶ ያሳያል እንጂ  የተለያየ eካላት ያላቸው መለኮቶች ወይም አምላኮች አሉ የሚል ትምህርትን አይፈቅድም እንግዲህ የeምላካችንን eንድነት ወይም ብቻውን መሆኑን እነዚህ ሁሉ ጥቅሶች በግልፅ እስከነገሩን ድረስ , GGNLበእራሳችን አእምሮ የፈጠርነው  ( ego-centric pagan doctrine. )
የሀያሉን  እግዚአብሄር  ቃል ለመቃረን ወይም  ለመፃረር የተፃፈ  የሰው ፈጠራ ትምህርት  ተብሎ የሚመደብ ነው.

ሁለተኛው ክፍል ይቀጥላል


Logged

ህምም
sis.by his mercy
Jr. Member
*
*
Posts: 12



View Profile
Re: answering to GGNL
« Reply #1 on: January 26, 2007, 04:45:37 PM »


    4.የሰው ልጅ በእግዚአብሄር eምሳል የተፈጠረበት ምክንያት.

Quote from:ዘፍ.1.27

ዘፍ.1.27፤ እግዚአብሔርም ሰውን በመልኩ ፈጠረ፤ በእግዚአብሔር መልክ ፈጠረው፤ ወንድና ሴት አድርጎ ፈጠራቸው።


ከላይ ካየናቸው ሶስት ነጥቦች በተጨማሪ, የሰው ልጅ አፈጣጠር ራሱ  እግዚአብሄር በአካል ብቻውን እንደሆነ የሚያሳይ የራሱ አስተዋፆ  አለው.የሰው ልጅ አንድ አካል, አንድ ህልውና ,አንድ ነፍስ እና አንድ  መንፈስ  ያለው ሆኖ እስከተፈጠረ ድረስ,መለኮት የተለያየ አካል አለው ብለን የምናምንበት ምንም ምክንያት የለም.የሰው ልጅ አካል,ነፍስ እና መንፈስ እስካለው ድረስ ሁሉን ቻዩ አምላክም አባት, ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ ተብሎ ሊገልፅ ይችላል,ነገር ጊን ልክ እንደ አዳም አንድ አካል ያለው ነው. GGNL ቢያንስ ይሄንን የመጀመሪያ የዘፍጥረትን እውነታ  ቢቀበል ራሱን እንደ እውነተኛ ዜና አሰራጪ አደርጎ ከማቅረብ የሚሻለው ነበር.
ስለ ዘፍጥረት 1:26 እውነታ ከላይ ባየናቸው አራት ነጥቦች ,በጣም ትልቅ እና ግልፅ የሆነ መረዳት እናገኛለን በተጨማሪም ነፍሳችንን ከ "ሀሰተኛ (ከከንቱ) ፀሀፊዎች " እንጥብቃለን .ጥቅሱ የተለያዩ መለኮታዊ አካላት ያላቸው አምላኮችን የሚያሳይ ሳይሆን የተለያየ ስልጣን እና ሀይል ያለው አምላክ መሆኑን ለማሳየት መሆኑን  GGNL ቢያውቀውና  ቢማርበት መልካም ነው.
         ዘፍጥረት 3:22..
Quote from:ዘፍ.3:22

ዘፍ.3:22፤ እግዚአብሔር አምላክም አለ። እነሆ አዳም መልካምንና ክፉን ለማወቅ ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ፤ አሁንም እጁን እንዳይዘረጋ፥ ደግሞም ከሕይወት ዛፍ ወስዶ እንዳይበላ፥ ለዘላለምም ሕያው ሆኖ እንዳይኖር


የዘፍጥረት  ሶስት እውነታ አዳም በቅዱስ እግዚአብሄር ላይ ሀጢአት እንደሰራ ያሳየናል, ይህ ማለት የመጀመሪያው አዳም በእግዚአብሄር አምሳል ተፈጥሮ እያለ ,በተፈጥሮው ላይ ባለመታዘዝ ሀጥያትን እንደጨመረ እናያለን.
Quote from:መክ.7:29

መክ.7:29፤ እግዚአብሔር ሰዎችን ቅኖች አድርጎ እንደ ፈጠራቸው፥ እነሆ፥ ይህን ብቻ አገኘሁ፤ እነርሱ ግን ብዙ ብልሃትን ፈለጉ።


ይሄ ጥቅስ  የሰው ልጅ የእግዚአብሄርን ሀሳብ ለመፈፀም ተፈጥሮ እያለ ለእራሱ ብዙ ነገሮችን ሲፈልግ  ያሳየናል.በዘፍጥረት ሶስት አዳም ከኛ እንደ አንዱ ሆነ የሚለውን ቃል  ሁሉን ቻዩን አምላክ የተለያየ አካል  እንዳለው ያሳያል ማለት በእግዚአብሄር ላይ ማመፅና መሳደብ ነው.አዳም ቅዱሱን አምላክ  አልታዘዝም ብሎ እንዳመፀ እና እንደተጠመደ ዘፍጥረት ሶስት  በሰፊው አሳየቶናል.  የመጀመሪያው ሰው አዳም  በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረው በዘፍጥረት 1:27ነበር , ነገር ግን በዘፍጥረት ሶስት ላይ እንደምናየው አዳም አንድ  በአመፅ ወይም በአለመታዘዝ  የጨመረው መለኮታዊ አካል አለ, ሀጢያተኝነትን በተፈጥሮው ጨመረ. አዳም የተለየ ህልውና ካላቸው መላክቶች እንደ አንዱ ሆነ ሆነ ማለት አዳም ባለመታዘዝ  ከመውደቁ በፊት በ ትክክል በእግዚአብሄር አምሳል የተሰራ ሰው አልነበረም ወይ?እንደ GGNL ትምህርት ከሆነ   በዘፍጥረት ሶስት ባለው እውነታ መሰረት  አዳም በእግዚአብሄር ላይ ባለመታዘዝ ተፈጥሮው ላይ ሀጥያት ከመጨመሩ በፊት  አንዱ የእግዚአብሄር አካል  በራሱ ላይ አመፀ (ተነሳ)  ማለት ነው?
እግዚአብሄር ይሄንን አባባል ይቃወመዋል!!!!!
የዘፍጥረት ሶስት ጥቅስ እንደሚያሳየን ,ከእግዚአብሄር ጋር የነበረ ህልውና ያለው አካል  በእግዚአብሄር ላይ ያመፀ , ከአዳም በፊት ካለ ቀጥሎ ደግሞ አዳም ክእነእዚህ መለኮታዊ አካሎች አንዱ ከሆነ በሀጥያት ሲወድቅ .ከአዳም በፊት  ባለመታዘዝ  በእግዚአብሄር ላይ ያመፀ  የትኛው አካል እንደሆነ እና ይህንን አካል  ለማሳየት ብለን የግድ  የራሳችንን መዝገበ  ቃላት ወይም መመሪያ መጥቀም ሚያስፈልገን አይመስለኝም.በተጨማሪም እነዚህ ጥቅሶች ቃሉን ግልፅ ያደርጉታል.
Quote from:ኢዮ.4:18

ኢዮ.4:18፤ እነሆ፥ በ ባሪያዎቹ አይታመንም፤
መላእክቱንም ስንፍና ይከስሳቸዋል፤


Quote from:ይሁ.1:6

ይሁ.1:6 መኖሪያቸውንም የተዉትን እንጂ የራሳቸውን አለቅነት ያልጠበቁትን መላእክት በዘላለም እስራት ከጨለማ በታች እስከ ታላቁ ቀን ፍርድ ድረስ ጠብቆአቸዋል።


          ዘፍጥረት 11:7
Quote from:ዘፍጥረት 11:7,8

ዘፍጥረት 11:7,8ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።
እግዚአብሔርም ከዚያ በምድር ሁሉ ላይ በተናቸው፤ ከተማይቱንም መሥራት ተዉ።


መፅሀፍ ቅዱስ ሚስጥር ወይም የተሰወረ እስካልሆነ ድረስ, እነዚህ ምእራፎች eይምታቱብንም.ምንም እንኩዋን GGNL እነዚህን ምእራፎች በ ፍፁም ባይጠቅሳቸውም የተወሰኑት የስላሴ eማኞች ይሄ ጥቅስ  የተለያዩ eካላት እንዳሉ ያሳያል ብለው ለትምህርታቸው ማረጋገጫ ነው ብለው እስከጠቀሱት ድረስ,የዘፍጥረት 11:7 ትክክለኛ ትርጉም ለአንባቢዎች ማስወቅ አለብኝ ብዬ አምኛለሁ .በግልፅ እንደምናየው ሌላው በተሳሳተ አስተሳሰብ የተተረጎመው የእግዚአብሄርን ሀይል የሚቃወም ወንጀል ,"እግዚአብሄር የራሱን አንዱን አካል ወደ ምድር ወርዶ የባቢሎንን ግንብ የሰሩትን  ሰዎች ቁዋንቁዋ እንዲደባልቅ  ሲጠራው,"እነዚህ መለኮታዊ አካላት ,በአንደኛው መለኮት አካል ተጠርተው እስኪመጡ ድረስ በምን ያህል ርቀት  ተራረቀው ይኖሩ ነበር?

እግዚአብሄር ይህንን  አባባል ይቅር  ይበለው! ! ! !

የእግዚአብሄር ቃል eንድ ነገር ለመስራት ወይም ለመፈፀም ሲያስፈልግ ተጠራርተው eንድ ላይ የሚሰሩ  የተለያዩ መለኮታዊ eካሎች እንዳሉ eይናገርም .እስኪ መፅሀፍ ቅዱስ ምን እንደሚል እንመልከት:-
Quote from:ዮሐ.16:27,28

ዮሐ.16:27 እናንተ ስለ ወደዳችሁኝ ከእግዚአብሔርም ዘንድ እኔ እንደ ወጣሁ ስላመናችሁ አብ እርሱ ራሱ ይወዳችኋልና። ከአብ ወጥቼ ወደ ዓለም መጥቻለሁ፤ ደግሞ ዓለምን እተወዋለሁ ወደ አብም እሄዳለሁ።


Quote from:ዮሐ.16:30

ዮሐ.16:30 ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን አሉት።


Quote from:ዮሐ.8:42

ዮሐ.8:42 ኢየሱስም አላቸው። እግዚአብሔርስ አባታችሁ ከሆነ በወደዳችሁኝ ነበር፤ እኔ ከእግዚአብሔር ወጥቼ መጥቻለሁና፤ እርሱ ላከኝ እንጂ ከራሴ አልመጣሁምና።


ከላይ የተጠቀሱት ጥቅሶች  እንደሚያስረዱን ,ወልድ ቃሉን ስጋ አደርጎ ከአባቱ ወጥቶ የመጣ ነው እንጂ , የተለየ መለኮታዊ አካል ያለው አይደለም.
Quote from:ዮሐ.20:22

ዮሐ.20:22 ይህንም ብሎ እፍ አለባቸውና። መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ።


Quote from:ኢዮ.33:4

ኢዮ.33:4፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥
ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ


Quote from:ህዝ. 37:6 ,14

ህዝ. 37:6 ,14.፤ጅማትም እሰጣችኋለሁ ሥጋንም አወጣባችኋለሁ በእናንተም ላይ ቁርበትን እዘረጋለሁ ትንፋሽንም አገባባችኋለሁ በሕይወትም ትኖራላችሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ። መንፈሴንም በውስጣችሁ አሳድራለሁ፥ እናንተም በሕይወት ትኖራላችሁ፥ በገዛ ምድራችሁም አኖራችኋለሁ፤ እኔም እግዚአብሔር እንደ ተናገርሁ እንዳደረግሁም ታውቃላችሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


Quote from:ዮሐ.15:26

ዮሐ.15:26 ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ ስለ እኔ ይመሰክራል፤


ከላይ በተመለከትነው ጥቅስ መሰረት, መንፈስ ቅዱስ ከእግዚአብሄር የሚወጣ  ሀይል ነው እንጂ ከእግዚአብሄር  ተለየቶ ለብቻው አካል ያለው እንዳይደለ በግልፅ እናያለን.
የእግዚአብሄር ቃል ምን ለመግለፅ እንደፈለገ ትክክለኛውን  እውቀት ለማግኘት ልባቸንን እና አእምሮአችንን መክፈት ያስፈልገናል.እግዚአብሄር መንፈስ እስከሆነ ድረስ, "እንሂድ ,እንውረድ "ሲል ምን ለማለት ፈልጎ ነው? ሁሉም ቦታ የሚገኝ አምላክ(omni present God) , ምድር ላይ አልነበርም ማለት ነው. ከነዛ መለኮታዊ አካሎች ጋ ተጠርቶ እስኪመጣ ድረስ ምድር ላይ አልነበርም ብሎ ማሰብ መፅሀፍ ቅዱሳዊ ነው ? የእግዚአብሄርን  ቃል  ለማክበር  ከፈለግን, መፅሀፍ ቅዱስ ራሱን እንዲገልፅ መፍቅድ አለብን የዘፍጥረትን መፅሀፍ ስናጠና እግዚአብሄር" ለመውረድ " የፈለገበት ሁለት ምክንያቶች , በምእራፍ 11 እና 18 ተጠቅሱአል ; ከእነዚህ ጥቅሶች እንደምንረዳው ሰማይ እና ምድርን የሞላው ጌታ "እንውረድ " የሚለውን ቃል ሲጠቀም ,የሚገልፀው ሁሉን ቻዩ አምላክ ከመላእክቶቹ ጋ ያለውን ህብረት ነው. ዘፍጥረት 18:21 ማየት ይቻላል.
Quote from:ዘፍጥረት 18:20-22

ዘፍጥረት 18:20-22፤ እግዚአብሔርም አለ። የሰዶምና የገሞራ ጩኸት እጅግ በዝቶአልና፥ ኃጢአታቸውም እጅግ ከብዳለችና፥ እንግዲህስ ወደ እኔ እንደ መጣች እንደ ጩኸትዋ አድርገው እንደ ሆነ ወርጄ አያለሁ፤ እንዲሁም ባይሆን አውቃለሁ።ሰዎቹም ከዚያ ፊታቸውን አቀኑ፥ ወደ ሰዶምም ሄዱ፤ አብርሃም ግን በእግዚአብሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር።

ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ አላቸውም።
Quote

Quote from:ዘፍ.11:7

ዘፍ.11:7፤ኑ፥ እንውረድ፤ አንዱ የአንዱን ነገር እንዳይሰማው ቋንቋቸውን በዚያ እንደባልቀው።


ማጠቃለያ:እግዚአብሄር  ወደ ሰዶምና ገሞራ  ሲወርድ ከሱ ጋራ የመላእክቱ  ህብረት በተግባር ነበ ር, እግዚአብሄር በሁሉ ቦታ የሚገኝ  መንፈስ እስከሆነ ድረስ ,”ወረደ “ ወይም “ወጣ” ወይም ታች ነው ላይ ነው የሚገኘው ማለት አንችልም.
ዮሀ.4:24;መዝ,139:7-12,ኤርሚ.23:23-24.
              ኢሳይያስ  6:8
Quote from:ኢሳ.6:8

ኢሳ.6:8፤ የጌታንም ድምፅ። ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም። እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አ ልሁ


ነብዩ ትንቢቱን በራእይ የሳለው (ያስቀመጥው) ከመጀመሪያው የኢሳይያስ መፅሀፍ ጀምሮ  ነበር.GGNL እንደሚለው ወይም ሊያሳመንን እንደሚሞከርው,በኢሳይያስ 6:8 የተፃፈው ብዙ ቃላት የሚያሳየን 
እግዚአብሄር በተለያየ አካል መገለጡን ወይም መለኮት ብዙ አካል እንዳለው ያሳያል ይለናል.እኛ  የእግዚአብሄር ቃል የሚነግረንን ለመቀበል   ልባችንን ካላጠነከርን በስተቀር,ኢሳይያስ በራእይ ያያቸው እነማነን እንደሆኑ በግልፅ ተቀምጠዋል.የመላክ ሰልጣን ያለው አንድ አካል እንደሆነ ኢሳይያስ 8ኛው ቁጥር ግልፅ ያደርግልናል,ከዛ አንድ  ቀላል ጥያቄ መጠየቅ እንችላለን,ለመላክ ሰልጣን ያልነበራቸው እነኛ መለኮታዊ አካሎች እነማን ነበሩ?
ኢሳይያስ 6 ያለውን እውነተኛውን አባባል ሳያሳይ ቁጥር “8” ን ብቻ  የሚያሳየንን  የGGNLን ወጥመድ (ማሳሳቻ) ለማምለጥ ከፈለግን ሙሉውን ቃል እንመልከተው.
Quote from:ኢሳ.6:1-9

ኢሳ.6:1-9 ንጉሡ ዖዝያን በሞተበት ዓመት እግዚአብሔርን በረጅምና ከፍ ባለ ዙፋን ላይ ተቀምጦ አየሁት፥ የልብሱም ዘርፍ መቅደሱን ሞልቶት ነበር።ሱራፌልም ከእርሱ በላይ ቆመው ነበር፥ ለእያንዳንዱም ስድስት ክንፍ ነበረው፤ በሁለት ክንፍ ፊቱን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ እግሮቹን ይሸፍን ነበር፥ በሁለቱም ክንፍ ይበር ነበር። አንዱም ለአንዱ። ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ ቅዱስ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ ምድር ሁሉ ከክብሩ ተሞልታለች እያለ ይጮኽ ነበር። የመድረኩም መሠረት ከጭዋኺው ድምፅ የተነሣ ተናወጠ፥ ቤቱንም ጢስ ሞላበት።እኔም። ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው በመሆኔ፥ ከንፈሮቻቸውም በረከሱባቸው ሕዝብ መካከል በመቀመጤ ዓይኖቼ የሠራዊትን ጌታ ንጉሡን እግዚአብሔርን ስለ አዩ ጠፍቻለሁና ወዮልኝ! አልሁ። ከሱራፌልም አንዱ እየበረረ ወደ እኔ መጣ፥ በእጁም ከመሠዊያው በጕጠት የወሰደው ፍም ነበረ። አፌንም ዳሰሰበትና። እነሆ፥ ይህ ከንፈሮችህን ነክቶአል፤ በደልህም ከአንተ ተወገደ፥ ኃጢአትህም ተሰረየልህ አለኝ።የጌታንም ድምፅ። ማንን እልካለሁ? ማንስ ይሄድልናል? ሲል ሰማሁ። እኔም። እነሆኝ፥ እኔን ላከኝ አልሁ።


እእርሱም። ሂድ፥ ይህን ሕዝብ። መስማትን ትሰማላችሁ አታስተውሉምም፤ ማየትንም ታያላችሁ አትመለከቱምም በላቸው።
Quote

የዚህን ምእራፍ አጠቃላይ እውነታ በስፋት ስናየው,በእግዚአብሄር ዙፋን አካባቢ ያሉት የመላክ ስልጣን የሌላቸው መለኮታዊ አካላት  እነማን እንደሆኑ ለመግለፅ ቀላል ያደርግልናል.ይህንን ከሚክያስ ራእይ ጋ እናስተያየው:-
Quote from:1ነገስት 22:19

1ነገስት 22:19 ሚክያስም አለ። እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።



ባለራእዩ ሚክያስ  በመንግስተ ሰማይ ግዛት  በእግዚአብሄር ዙፋን አካባቢ የነበረው  መለኮታዊ አካል ማን እንደነበር አይትዋል .እንጂ እንደ  GGNL ትምህርት መለኮታዊ አ ካላትን እግዚአብሄር ልጅ (የእግዚአብሄር 2 ኛ አካል) ወይም, እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ (የእግዚአብሄር 3 ኛው አካል) የሚባል ከእግዚአብሄር እኩል ወይም የተለያየ አካላትን አላየም.ከእዚህ መፅሀፍ ቅዱሳዊ  መነሻሀሳብ ኢሳይያስ 6 ላይ በተሰጠን ጥቅስ “ ለመላክ “ሰልጣን የሌላቸው ሱራፌል ከተባሉት መላእክት ሌላ ማንንም አናይም.

ማሳሰቢያ :ቃሉ ላይ አንጨምር!

ሶስተኛው ክፍል ይቀጥላል




Logged

ህምም
sis.by his mercy
Jr. Member
*
*
Posts: 12



View Profile
Re: answering to GGNL
« Reply #2 on: January 27, 2007, 05:16:17 PM »


1:2  ( with ) የሚለው አያያዥ ቃል.አማርኛው “ጋር “ "ዘንድ"ወይም "እና(ና)" በተባለው አያያዥ ቃል ይተረጉመዋል ,ቀጥተኛ ትርጉሙ የተለያየ አካላትን የሚያሳይ ነውን?
በእዚህ ደርጃ  GGNL የሰውን መዝገበ  ቃላት ለመጠቀም ከመመርጥ ,እና ከመፅሀፍ ቅዱሱ የበለጠ  አውቃለሁ ብሎ ማጠቃለያ ከመስጠቱ በፊት ” ጋር “ "ዘንድ"ወይም "እና(ና)"(with ) የሚለውን አያያዥ ቃል ምንን ይገልፃል ብሎ የእግዚአብሄርን ቃል ማጥናት ይኖርበታል.ከመፅሀፍ  ቅዱስ "ውስጥ ጋር" ስለሚለው አያያዥ ቃል አጠቃቀም እስቲ እንመልከት:-
Quote from:ኢዮ.25:2

ኢዮ.25:2፤ ገዢነትና መፈራት በእርሱ ዘንድ ናቸው፤


በከፍታውም ሰላም አድራጊ ነው።
Quote from:ዘፍ.9:4

ዘፍ.9:4፤ ነገር ግን ነፍሱ ደሙ ያለችበትን ሥጋ አትብሉ


Quote from:ዮሐ.14:17

ዮሐ.14:17 እርሱም ዓለም የማያየውና የማያውቀው ስለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በ ውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።


Quote from:መዝ.93:1

መዝ.93:1 እግዚአብሔር ነገሠ ፥ ክብርንምለበሰ፤ እግዚአብሔር ኃይልን ለበሰ፥ ታጠቀም፤ ዓለምን እንዳትናወጥ አጸናት።


Quote from:መዝ.95:2

መዝ.95:2 በምስጋና ወደ ፊቱ እንድረስ፥ በዝማሬም ለእርሱ እልል እንበል፤


ከላይ ባየናቸው ጥቅሶች”ጋር “ የሚለው አያያዥ ቃል የተለያየ መለኮታዊ አካላትን እስካላሳየን ድረስ,ከዚህ እውነታ በመነሳት “ጋር “ የሚለው አያያዥ ቃል ቀጥተኛ ትርጉም  ሁልጊዜ የተለያየ አካል እንዳለ ያረጋግጥልናል ማለት አንችልም.
1:3 .የግል አጠራር (  Personal pronouns)  አዘውትረን የተለያየ አካላትን ለመግልፅ እንጠቀምበታለን?
Quote from:መዝ.18:30

መዝ.18:30 የአምላኬ መንገድ ፍጹም ነው፥ የእግዚአብሔር ቃል የነበረ ነው፥ በእርሱ ለሚታመኑት ሁሉ ጋሻ ነው።


Quote from:ምሳ.30:6

ምሳ.30:6 እንዳይዘልፍህ፥ ሐሰተኛም እንዳትሆን በቃሉ አንዳች አትጨምር።


Quote from:ምሳ.4:13

ምሳ.4:13 ተግሣጽን ያዝ፥ አትተውም፤ ጠብቀው፥ እርሱ ሕይወትህ ነውና።


ከላይ ባየናቸው ጥቅሶች የግል ተውላጣ  ስም (Personal pronouns)) የተለያየ መለኮታዊ አካልን እስካላሳየን ድረስ,ከእዚህ እውነታበመነሳትየግል  የግል ተውላ�  ስም የተለያየ አካላትን ያሳያል ብልን ቀጥተኛ ትርጉም ሁልጊዜ ልንሰጠው እንደማንችል በቀላሉ እንረዳለን.
1:4 “እና “ (and) የሚለው አያያዥ ቃል  በቀጥታ የተለያየ መለኮታዊ � ካላት እንዳለ ያሳያል?
Quote from:ኤር.23:9

ኤር.23:9 ስለ ነቢያት፤ ልቤ በውስጤ ተሰብሮአል አጥንቶቼም ሁሉ ታውከዋል፤ ከእግዚአብሔር የተነሣ ከቅዱስ ቃሉም የተነሣ የወይን � ጅ እንዳሸነፈው እንደ ሰካራም ሰው ሆኛለሁ።


Quote from:ሐዋ.20:32

ሐዋ.20:32 አሁንም ለእግዚአብሔርና ያንጻችሁ ዘንድ በቅዱሳንም ሁሉ መካከል ርስትን ይሰጣችሁ ዘንድ ለሚችል ለጸጋው ቃል አደራ ሰጥቻችኋለሁ።


Quote from:ኤፌ.6:10

ኤፌ.6:10 በቀረውስ በጌታና  በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ።


Quote from:1ዮሐ.5:20

1ዮሐ.5:20  የእግዚአብሔርም ልጅ እንደ መጣ፥ እውነተኛም የሆነውን እናውቅ ዘንድ ልቡናን እንደ ሰጠን እናውቃለን፤ እውነተኛም በሆነው በእርሱ አለን፥ እርሱም ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ እውነተኛ  አምላክና የዘላለም ሕይወት ነው።


Quote from:ኢሳ.44:6

ኢሳ.44:6፤ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር፥ የሚቤዥም የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እኔ ፊተኛ ነኝ እኔም ኋለኛ ነኝ፥ ከእኔ ሌላም አምላክ የለም።


Quote from:ራዕ.20:1-2

ራዕ.20:1-2 የጥልቁንም መክፈቻና ታላቁን ሰንሰለት በእጁ የያዘ መልአክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ። የቀደመውንም እባብ ዘንዶውን እርሱም ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን ያዘው


Quote from:ዮሐ.20:28

ዮሐ.20:28 ቶማስም። ጌታዬ አምላኬም ብሎ መለሰለት።


Quote from:ዮሐ.14:6

ዮሐ.14:6 ኢየሱስም። እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።


ከላይ ባየናቸው ጥቅሶች “እና “ የሚለው አያያዥ ቃል  የተለያየ አካላትን እስካላሳየን ድርስ ከዚህ እውነት በመነሳት  “እና “ የሚለው  ቃል ሁልጊዜ
የተለያየ መለኮታዊ አካል እንዳለ ያሳየናል ወይም ቀጥተኛ ትርጉሙ ነው ማለት አንችልም.የአንድን ሰው ወይም የአንድን ነገር  የተለያየ ተፈጥሮ አጉልቶ ለማሳየት የምንጠቀምበት ቃል ነው.
1.5 : ማን ለማን ሰጠ?
Quote from:ዮሐ.3:16

ዮሐ.3:16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።


እንደ GGNL አባባል ከሆነ ይሄ ጥቅስ የሚያሳየን “እግዚአብሄር አባት እግዚአብሄር ልጅን ለአለም መድሀኒት  ሰጠ  “ተብሎ ይተርጎማል እንግዲህ እንደዚህ ብለን ለመጠይቅ እንገደዳለን,እግዚአብሄር አምላኩን አምላኩን(ልጁን)ለእኛ መድሀኒት አሳልፎ ሰጠ ? GGNL እዚህ ሁሉ ግራ መጋባት (መወናበድ )ውስጥ የገባው መፅሀፍ ቅዱስ ራሱ እንዲናገር (እንዲገልፅ) እድሉን ስላልሰጠው ነው ይልቁን GGNL የወሰደው አማራጭ እግዚአብሄሮችን  መጨመር(ማባዛት ) ነው.እንደ GGNL እግዚአብሄር አባት ( the first person God) ሁለተኛውን አካል እግዚአብሄርን (  God the Son) ከሰጠ , GGNL በትክክል ማለት የፈለገው እግዚአብሄር አምላኩ እግዚአብሄርን (  his God) ለመዳናችን ሰጠን ማለት ነው.አሁን GGNL ያለምንም ጥያቄ ከእንደዚህ አይነቱ  መረዳት ወይም ማጥቃለያ መውጣት ይኖርበታል,አለበለዛ “አምላክ አምላኩን ሰጠ  ወይም እግዚአ ብሄር ሁለተኛ አካሉን ሰጠ  “  His second person God የሚለው የ GGNL ፍልስፍና ወይም መገለፅ ግን በቀጥታ ያለምንም ማጋነን ሁለት አምላኮችን ወደማምልክ ይመራል.
ማሳሰቢያ :መፅሀፍ ቅዱስ እግዚአብሄር እግዚአብሄርን ሰጠ  ሳይሆን;ልጁን ሰጠ ነው የሚለው
ዮሐ.3:16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና። ይሄጥቅስ ምን መልእክት አለው?መፅሀፍ ቅዱስ  ልጁን ሰጠን ይላል እንጂ እግዚአብሄር ሌላውን ሁለተኛ አካል የሚባለውን (አምላኩን )ለመዳናችን ሰጠ  የሚል ትርጉም ይለውም.
“ልጅ “ወይም ወልድ የሚለውን ቃል ትርጉም  ከመፅሀፍ ቅዱስ አያይዘን  እናጥናለን.
Quote from:ሮሜ.5:10

ሮሜ.5:10 ጠላቶች ሳለን ከእግዚአብሔር ጋር በልጁ ሞት ከታረቅን፥ ይልቁንም ከታረቅን በኋላ በሕይወቱ እንድናለን፤


Quote from:ቆላ.1:21-22

ቆላ.1:21-22 እናንተንም ነውርና ነቀፋ የሌላችሁና ቅዱሳን አድርጎ በእርሱ ፊት ያቀርባችሁ ዘንድ፥ በፊት የተለያችሁትን ክፉ ሥራችሁንም በማድረግ በአሳባችሁ ጠ ላቶች የነበራችሁትን አሁን በሥጋው ሰውነት በሞቱ በኩል አስታረቃችሁ።


ከላይ ያሉትን ጥቅሶች ትኩረት ሰጥተን ብናያቸው,ሮሜን እንዲፅፍ  እግዚአብሄር የተጠቀመበት ሀዋሪያ ቆላስያስንም የፃፈው እሱ ነበር.በእነዚህ ምእራፎች,ሀዋሪያው ጳውሎስ በግልፅ እንዳስቀመጥው “ልጅ “ማለት  “የእግዚአብሄር የሰጋው ሰውነት ” መሆኑን በትክክል እንረዳለን.
የራሳችንን መዝገበ  ቃላት በፈለግነው መንገድ ተጠቅመን በሌላ መንገድ መተርጎም ትክክለኛ አካሄድ አይመስልኝም.
Quote from:ዮሐ.6:51

ዮሐ.6:51 ከሰማይ የወረደ ሕያው እንጀራ እኔ ነኝ፤ ሰው ከዚህ እንጀራ ቢበላ ለዘላለም ይኖራል፤ እኔም ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው።


Quote from:ዮሐ.3:16

ዮሐ.3:16 በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።


ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሀ. 3:16 ምን ማለትእንደፈለገ በዮሀንስ 6:51  በግልፅ እንረዳለን.
GGNL ማድረግ ያለበት ነገር ቢኖር” እግዚአብሄር ሁለተኛውን እግዚአብሄርን (የራሱን አምላክ) ለአለም ህይወት ሰጠ ” የሚለውን የራሱን ፈጠራና ግምት ቃሉ ከሚለው በላይ ማስፋፋቱን አቁሞ ,ቃሉ ስለ ራሱ የሚሰጠውን ትርጉም (መረዳት) እና  ህያውነት መቀበል አለበት በተጨማሪም ከላይ ከተጠቀሱት ጥቅሶች በግልፅ እንደምናየው  መፅሀፍ ቅዱስ “እግዚአብሄር ለአለም መድሀኒት ልጁ እንዲሞት ሰጠ  ስንል”ከላይ ከተጠቅሱት ጥቅሶች ጋር ስናስተያየው “እግዚአብሄር ስጋውን (አካሉን) ለአለም ህይወት ለሞት ሰጠ ” ማለት ነው:
Quote from:1ቆሮ.8:4-6

1ቆሮ.8:4-6 እንግዲህ ለጣዖት የተሰዋውን ሥጋ ስለ መብላት፥ ጣዖት ሁሉ በዓለም ከንቱ እንደ ሆነ ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን።
መቼም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ፤ ነገር ግን በሰማይ ሆነ በምድርም ሆነ አማልክት የተባሉ ምንም ቢኖሩ፥
ለእኛስ ነገር ሁሉ ከእርሱ የሆነ እኛም ለእርሱ የሆንን አንድ አምላክ አብ አ ለን፥ ነገር ሁሉም በእርሱ በኩል የሆነ እኛም በእርሱ በኩል የሆንን አንድ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ አለን


ከዚህ ጥቅስ እንደምናየው ,አንድ አምላክ ብቻ አለ,አባት,ልጅ ወይም እግዚአብሄር አባትን ወክሎ ሊጠራ የሚችል በልጁ የተገለፅውን  ነገርግን በመለኮታዊ አ ካል  ከአባት ያልተለየውን,ዮሀ:5:19 እንደሚለው “ወልድ ከራሱ ሊያደርግ ምንም  አይችልም”:ወልድ” የሚለው ቃል በቀጥታ “አብን”ከወከለ እና”ወልድ” ለሀጢያታችን ሞተ ካለ,እግዚአብሄር በቀራንዮ መስቀል ሞተ ማለት እንችላለን.ነገር ግን እግዚአብሄር መንፈስ እንደሆነ እና እንደማይሞት አለማቀፋዊ እና መፅሀፍ ቅዱሳዊ እውነታ ነው.ከመፅሀፍ ቅዱስ እውነት እና አጠቃላይ መነሻ ሀሳብ ለመስማማት “ወልድ “ የሚለው ቃል ለሀጢአታችን ሞቶ የነበረው የሁሉን ቻዩ አምላክ ስውነት አካል (ስጋ) ነው ወደሚለው ቀጥተኛ ማጥቃለያ ያደርሰናል. ከ GGNL ፀሀፊዎች  ለመረዳት የቻልኩት አንድ ተጨማሪ ነጥብ,“  the inside by the out side” የውስጡን � ውጩ የሚለውን ለአለም አቀፍ ደርጃ በጋራ የሚጥቀሙበትን መመሪያ ባለማወቅ ወይም አውቆ በመዝለል (በመሸፋፈን) ያልፈዋል.ይሄ መመሪያ በመፅሀፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚሰራ ላሳያችሁ.የሚቀጥሉትን ምሳሌዎች እንመልከት:-
በብዙ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይ(ህዝ 13:9,ራእ.ዮሀ 16:3 ) ሰዎች የሌሎች ሰዎችን ነፍስ እንደሚገሉ ያሳያል,በማቴዎስ ወንጌል ላይ ስጋን እንጂ ነፍስን ማንም መግደል እንደማይችል መፅሀፍ ቅዱስ ከነገረን,ይሄ የሚያሳየን “the inside by the out side” የሚለው መመሪያ በመፅሀፍ ቅዱስ ላይም መጠቀም መጀመሩን ነው ማቴ 10:28.
Quote from:ዘሌ.5:2,

ዘሌ.5:2፤ ማናቸውም ሰው ሳይታወቀው ርኩስ ነገር ቢነካ፥ የረከሰም አውሬ በድን፥ ወይም የረከሰ ከብት በድን፥ ወይም የረከሰ የተንቀሳቀሰ እንስሳ በ ድን ቢሆን፥ እርሱም ርኩስ ቢሆን ነገሩ በታወቀው ጊዜ በደል ይሆንበታል፤
ዘሌ.17:10፤ ከእስራኤልም ልጆች ወይም በመካከላቸው ከሚኖሩ እንግዶች ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብድበታለሁ፥ ያንንም ሰው ከሕዝቡ ለይቼ አጠፋዋለሁ።


“ the inside by the out side” በሚለው መመሪያ ወይም ህግ ካልሆነ በስተቀር” ነፍስ” እንዴት ”ደምን”ስጋዊ(ቁሳካልን)ይበላል?
Quote from:ማቴ.23:21

ማቴ.23:21 በቤተ መቅደስም የሚምለው በእርሱና በእርሱ በሚኖረው ይምላል፤


Quote from:ዮሐ.2:19-21

ዮሐ.2:19-21 ኢየሱስም መልሶ። ይህን ቤተ መቅደስ አፍርሱት፥ በሦስት ቀንም አነሣዋለሁ አላቸው።
ስለዚህ አይሁድ። ይህ ቤተ መቅደስ ከአርባ ስድስት ዓመት ጀምሮ ይሰራ ነበር፥ አንተስ በሦስት ቀን ታነሣዋለህን? አሉት። እርሱ ግን ስለ ሰውነቱ ቤተ መቅደስ ይል ነበር።


መፅሀፍ ቅዱስ የክርስቶስ አካል “ቤተመቅደስ “ ነው ይለናል,ስለዚህ በዮሀ 14:10 ኢየሱስ አብ በእኔ አለ እንዳለው.“ወልድ “ “አብ” ሆነ ስንል
“አብ  በወልድ “ ውስጥ እንዳለ በትክክል እንስማማለን .

አራተኛው ክፍል ይቀጥላል


Logged

ህምም
sis.by his mercy
Jr. Member
*
*
Posts: 12



View Profile
Re: answering to GGNL
« Reply #3 on: January 28, 2007, 09:06:55 AM »


 
አጭር ማጠቃለያ

የመፅሀፍ ቅዱስ ፀሀፊዎች በቀጥታ የእግዚአብሄር ቃል እንደሚለው አንድ አምላክ ብቻ አለ ብለው ቢያምኑ ኖሮ,የስላሴን ( trinity) ሀሰተኛ ወይም ልብ ወለድ ትምህርት ፅንሰ ሀሳብ የ4 ኛው ክፍለዘመን እና የ21 ኛው ክፍለዘመን ሰው ሰራሽ ዶክትሪን “በእግዚአብሄር አካል ላይ ሁለት ራስ”( Twins in the God Head),�  GGNL የተዘጋጀው (የተፈጥረው)እንዲስፋፋ ለመፍቀድ ወይም  ግፊት ለማድረግ ቤተክርስቲያን ምንም የጋራ የሆነ ነጥብ የላትም ነበር.እግዚአብሄር ራሱን አንድ ,ብቻውን ያለ, የማይነጣጥል ,እና የሚመስለው የሌለ አድርጎ እስከገለጠ  ድረስ,የመንትዮች (ሁለት ) ዶክትሪን መፍጠር አ ይን ያወጣ የእርግማን (አፀያፊ) ትምህርት ነው በተጨማሪም GGNL, የአንድ አምላክ (አንድ አካል ) አማኞች መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሄር በተግባር ሲስራ ነው ብለው ያስተምራሉ ብሎ ገልፅዋል ,መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሄር ራሱ በስራ (በተግባር )ላይ ብለን እስካላመንን ድረስ.ይሄንን ነጥብ የ GGNL ያለመረዳት ወይም የትርጉም እጥረት ነው ብዬ ትቼዋልሁ.

  • 1. መንፈስቅዱስ ከአብ የተለየ አካል ካለው,ለምን መፅሀፍ ቅዱስ መንፈስ ቅዱስ ከአብ ይወጣል አ ለ? Meንፈስ ቅዱስ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል  እንደሌለው አያረጋግጥም? ዮሀ. 15:26


  • 2. መንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ  የተለየ መለኮታዊ አካል ቢኖረው,መፅሀፍ ቅዱስ ኢየሱስ ደቀመዛሙርቶቹ ላይ መንፈስ ቅዱስን እፍ አለባቸው ለምን አለን, መንፈስ ቅዱስ  ከየሱስ የተለየ መለኮታዊ አካል እንደሌለው አያሳኢየንም ?ዮሀ. 20:21


  • 3. መንፈስ ቅዱስ ከኢየሱስ የተለየ አካል ያለው ከሆነ, ለምን መፅሀፍ ቅዱስ “ allos“የሚለውን የግሪክ ቃል (አንድ ነገር በተለያየ መልኩ ሲገለጥ ) ተጠቀመ ,“  hetros” ወይም (የተለያየ ነገር ከተለያየ አካል ) አ ላለም , መንፈስ ቅዱስ ወልድ(እግዚአብሄር) በተለያየ መልኩ ሲገለጥ ነው እንጂ ሌላ የተለየ አካል ያለው አለመሆኑን እያረጋግጥልንም ? ዮሀ. 14 :16.


  • 4. ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል ካለው ,ለምን መፅሀፍ ቅዱስ ወልድ በራሱ ምንም ሊያደርግ አይችልም አለ,ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል እንደሌው በትክክል አ ያሳይም? ዮሀ. 5:9


  • 5.ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል ካለው ,ኢየሱስን ( አባትህ የት አለ ? ) ብለው ሲጥይቁት  “ እኔ እሱ ነኝ “ብሎ እንዴት መለሰላቸው ,ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል እንደሌለው አያረጋግጥልንም ? ዮሀንስ 8: 29 እና 24


  • 6. ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል ካለው, ለምን መፅሀፍ ቅዱስ ወልድ ከአብ ወጣ ይላል , ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል እንደሌለው በሚገባ አያሳየንም ? ዮሀንስ 8: 42


  • 7. ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል ካለው ; መፅሀፍ ቅዱስ ኢየሱስ ራሱ አባት ነው አለው , ኢየሱስ ከአብ የተለየ አካል  የሌለው እንደሆነ ማረጋገጫ አይደለም ? ኢሳ 9:6


  • 8. ወልድ ከአብ የተለየ አካል ካለው ,ለምን መፅሀፍ ቅዱስ “ የመለኮት ሙላት  ሁሉ በሰውነት ተገልፆ ይኖራል “ ካለን ,ይሄ ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል እንደሌለው በ ትክክል አያሳየንም ? ቆላ 2 :9


  • 9. ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል ካለው ,እንዴት  መፅሀፍ ቅዱስ  ኢየሱስ ብቻ የሚያውቀው ስም አለ ይለናል  እዚህ ላይ አብን አላዋቂ  አደረግነው ማለት ነው , ወልድ ከአብ የተለየ አካል እንደሌለው አያረጋግጥልንም ? ራ.ዮሀ 19:11


  • 10. ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል ካለው,መፅሀፍ ቅዱስ ለምን የእግዚአብሄር ሙላት ሁሉ በኢየሱስ ነው አ ለን ,አሁንስ ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል እንደሌለው አላሳመነንም ? ቆላ 1 :19


  • 11. የተለያዩ  መለኮታዊ አካላት (አማልክቶች ) አሉ ካልን , መፅሀፍ ቅዱስ አንድ ዙፋን እና አንድ ተቀማጭ አለ አለን , ይሄስ አማልክቶች ወይም የተለያየ አካላት ያላቸው እግዚአ ብሄሮች እንደሌሉ በእርግጥኝነት አያሳየንም ? ራእይ 4 :2 ,21 :6


  • 12. ወልድ ከአብ የተለየ አካል አለው ካልን ,መፅሀፍ ቅዱስ እንዴት  ኢየሱስ ራሱን ከሞት አስነሳለሁ ሊል ይችላል,ወልድ ከአብ የተለየ (ለብቻው ) አካል  የሌለው እንደሆነ በግልፅ አያሳመንም ? ዮሀ 2 : 19.


  • 13. ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል ካለው , መፅሀፍ ቅዱስ በወልድ የሚያመን አብ ደግሞ አለው እንዴት አለን , ወልድ ከአብ ልዩ የሆነ መለኮታዊ አካል እንደሌለው አ ይገልፅልንም ? 1 ዮሀ 2:23.


  • 14. ወልድ ከአብ በአካል ከተለየ , መፅሀፍ ቅዱስ እግዚአብሄር በክርስቶስ ሆኖ አለሙን ከራሱ ጋ ያስታረቅ ነበር ለምን ይለናል , ወልድ እና አብ በአካል የተለያዩ እንዳልሆኑ አ ያሳየንም ? 2 ቆር 5 : 19.


  • 15. ወልድና አብ በአካል የተለያዩ ከሆኑ , መፅሀፍ ቅዱስ ለምን በእኔ(በኢየሱስ )የሚያምን በላከኝ(በእግዚአብሄር )ማመኑ ነው አለ , ኢየሱስ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል እንደሌለው  አያስተምረንም ? ዮሀ 12 :44.


  • 16. የተለያዩ  መለኮታዊ አካላት (አማልክቶች ) አሉ ካልን ,መፅሀፍ ቅዱስ ለምን ከአንድ በላይ ሚስት ማግባት ማመንዘር ነው ብሎ ያስተምረናል ? ቤተክርስቲያን ሙሽራ  እስከሆነች ድርስ ,  ሙሽራችንን ( ሁሉን ቻዩ አምላክ ) ከአንድ በላይ ነው ብለን እንዴት  እንጥብቃለን ?  ኢሳ 54 :5 , 2ቆሮ 11 : 2.


  • 17. ወልድ ከአብ የተለየ አካል አለው ካልን, ኢሳ 44.6-8  እነዚህን ቃላቶች (ጥቅሶች ) በቀጥታ ለአብ ወይም ለእግዚአብሄር ብቻ  እስከተጠቀምንባቸው ድረስ , መፅሀፍ ቅዱስ ኢየሱስን አልፋ ኦሜጋ ወይም መጀመሪያና መጨረሽያ (ራእ.ዮ 22 :12 ) ነው ለምን ይለዋል ?


  • 18. ወልድ ከአብ የተለየ መለኮታዊ አካል ቢኖረው ,ለምን መፅሀፍ ቅዱስ ኢየሱስ ራሱን የእስራኤል ንጉስ(እግዚአብሄር አባት ወይም አብ ኢሳ 46 :8 ) እና የእግዚአብሄር ልጅ ብሎ ይጠራዋል ወይም ይገልፀዋል, ይሄ የመለኮት በአካል አንድ መሆንን ያሳያል,ኢየሱስ ራሱ ሁለት መልክ አካል  መገለጫ አለው ? ዮሀ 1 : 50.


  • 19. ወልድ ከአብ የተለየ  መለኮታዊ አካል ቢኖረው,መፅሀፍ ቅዱስ እኔ (ኢየሱስ ) በአብ (እግዚአብሄር ) አለሁ ብሎ  ለምን ያስተምረናል ,ወልድ ከአ ብ የተለየ አካል የሌለው እንደሆነ አያረጋግጥልንም ? ዮሀ 14 :10


  • 20. አብ , ወልድ , መንፈስ ቅዱስ ,የተለያየ አካል ወይም የየራሳቸው ህልውና ካላቸው,ለምን መፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፎች ስለ ኢየሱስ ይመስክራሉ ወይም ይናገራሉ ለምን ይልናል, ብቻውን ያለ አንድ መለኮታዊ አካል ኢንዳለ በትክክል አያረጋግጥልንም ? ዮሀ 5 .39.




ማጠቃለያ :ሌላው የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል ማለት የፈለገውን በሙሉ ትተን,የእግዚአብሄርሄርን ቃል በእኛ መዝገበቃላት መተርጎም አዋቂነት አይደለም.የዚህ አይነቱ አቀራረብ ወይም ዘዴ 
የእግዚአብሄርን ቃል እኛ ማለት የፈለግነውን ብቻ እንዲልልን ማስገደድ ነው .ስላሴ (   trinity ) የሚለው ቃል የሌለ ወይም የማይታውቅ ከተነሳበት ትምህርት ጋር የማይሄድ እስከሆነ ድረስ ,በየትም ቦታ በእውነት የማይታወቀውን ወይም ያልተገለፀውን ካላወቅክ ብሎ ሰው ላይ መፍረድ ይሄ ምህረት የማይገኝለት በደል ወይም ህገ ወጥነት ነው.መፅሀፍ ቅዱስ ስለ ተለያዩ መለኮታዊ አካላት አያስተምረንም, ነገር ግን ስለ አብ (የማይታየው የእግዚአብሄር ባህርይ ,ሮሜ 1 :20 ) ወልድ, (የማይታየው አምላክ ምሳሌ ቆላ 1:15 ) እና መንፈስ ቅዱስ ,(እግዚአብሄር ራሱ በስራ ወይም በተግባር  ላይ 1 ቆሮ 1 :10.
ፍፁሙን እና እንደብረት የጠነከረውን የአንድ አምላክ መሰረታዊ እውነት ከመቃውምና ከመካድ, የGGNL ፀሀፊዎች  ራሳቸውን ለእዚአብሄር ቃል አ ዋርደው እውነቱን እንዲረዱና እንዲያውቁ  በትህትናና (በእግዚአብሄር ፍርሀት )ፀሎቴ ነው.
የማይለዋወጥውንና የማይከፋፍለው አንድ አምላክ የመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት ያብራ!!!!

ሰው ሰራሽ ትምህርት ወይም ፍልስፍናን ሳይሆን “የእግዚአብሄርን ቃል ሰበኩ!! “ 2ጢሞ 4:2
Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages