ትዝታ - ቅዳሜ ፣ ግንቦት 24 ቀን ከምሽቱ 12 ሰዓት፣ በብሔራዊ ቲያትር የኢትዮጵያ ዘመናዊ የሙዚቃ ኦርኬስትራ ባንድ ማንነት የተቀዳው ብዙም ቅርብ ከማይባል ምንጭ ነው። ምንጩም በአርመንያ በተፈጸመው የዘር ጭፍጨፋ ወላጆቻቸውን ያጡ እና ንጉሰ ነገስት ሐይለስላሴ ኢየሩሳሌም አግኝተዋቸው ወደ ኢትዮጵያ ያመጧቸው አርባ ልጆች ናቸው። የእነሱ በኢትዮጵያ መኖር በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ኢምፔርያል ባንድ እንዲቋቋም፣ የኢትዮጵያ የመጀመሪያው ብሔራዊ መዝሙር እንዲቀናበር እና የትንፋሽ የሙዚቃ መሳሪያዎች በስፋት እንዲታወቁ አስችሏል። ከዛ ጊዜ አንስቶ በነበሩት አስርተ ዓመታት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ የጃዝ አብዮት የተጥለቀለቀበት ጊዜ እንደነበረ እና የደርግ አስከፊ የኮሚኒስት አገዛዝ ጥላ እስኪያጠላበት ድረስ እንደቀጠለ በኢትዮጵያ ጃዝ ወስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸው እነ አለማየሁ እሸቴ. ሙላቱ አስታጥቄ.፣ ግሩም መዝሙር፣ እና ሳሙኤል ይርጋ እንዲሁም በአዲስአበባ ብቸኛው አርመናው ድምጻዊ እና ሙዚቀኛ ቫሄ ይመሰክራሉ። ትዝታ፡ በአብዛኞች ዘንድ በመረሳት ላይ ላለው የኢትዮጵያ ወርቃማ የሙዚቃ ዘመን ፣ ተወዳጅ የሙዚቃ መምህራን እና የጃዝ ክለብ ትዝታዎች ላይ ብርሃን እንዲያርፍ የሙዚቃ በርን የሚከፍት ነው። | |
TEZETA: SATURDAY, JUNE 1ST 6:00PM AT THE NATIONAL THEATER Modern Ethiopian big band orchestra music finds its unlikely origins in the royal adoption of 40 Jerusalem orphans of the Armenian Genocide by Emperor Haile Selassie. Their presence as the first royal imperial band would make way for the composed music of Ethiopia's first national anthem, the popularization of brass instruments, and in later decades, a jazz revolution that swept the country before descending into the throes of the communist Derg regime. Told through first-hand accounts with Ethiopian jazz greats such as Alemayehu Eshete, Mulatu Astatke, Girum Mezmur, as well as Sammy Yirga and while following Vahé, the only performing Armenian singer / musician in Addis Ababa, TEZETA opens the musical door to a light of memories of a jazz club, a beloved teacher, and a golden musical era forgotten by many. |