1) Choke speed
ፍጥነት ቀንስ
ከዚህ በታች ያሉትን አልሞከርኳቸውም። በተለይ ሶስተኛው የሕግ ባለሞያ ርዳታ ያስፈልገናል። ፈቃዱ እንዳለ
ተተርጉሞ መሆን ይኖርበታል። ይህ ፈቃድ እስካሁን በአማርኛ ስለሌለ አርዕስቱን ብቻ መተርጎሙ ብዙም ጥቅም
የለውም። ስለዚህ እንዳለ ቢቀመጥ ይመረጣል ባይ ነኝ።
በነገራችን ላይ አንዳንድ ሀረጎች እንዳለ መቀመጥ ሊኖርባቸው ይችላል. በተለይ ለመተርጎም አስቸጋሪ ሲሆኑና
ተጠቃሚውን ችግር ውስጥ የማይችሉ ከሆኑ ቢተው ከጊዜም ከአጠቃቀምም አንጻር ተመራጭነት አለው። ይኼ ሲሆን ግን
አንድ መገንዘብ ያለብን የንግሊዘኛውን ሐረግ መገልበጥ አይኖርብንም። የትርጉሙን ቦታ ክፍት ማድረግ ያስፈልጋል።
ምክንያቱም ፕሮግራሙ የአማርኛውን ትርጉም ካላገኘ ሁለተኛ ሆኖ እንዲያገለግል ወደተመረጠው ቋንቋ ስለሚወስደው
ነው። በተለምዶ ይኼ እንግሊዘኛ ወይም ፕሮግራሙ የተጻፈበት ቋንቋ ሲሆን ምሳሌ አንዳንድ ሰዎች ፈረንሳናይኝ
ሊቀላቸው ይችላል። የ እንግሊዘኛውቅ ሓረግ ከተገለበጠ ግን ፕሮግራሙ ተተርጉሟል ብሎ ስለሚያስብ ወደፈረንሳይኛ
እንደመውሰድ እንግሊዘኛውን ያሳያል። በአጠቃላይ አንዳንድ ያልተተረጎሙ ሓረጎች መኖር በተጠቃሚነት ላይ ብዙም
ለውጥ አያመጣም።
ለመተርጎም በጣም አስቸጋሪ የሆኑት ላይ ጊዜ ከማጥፋት (በጣም ነው ጊዜ የሚበሉት) ሌላ ጥቅም ላይ የሚወል ስራ
ላይ ጊዜን ማሳለፍ ይሻላል።
በነገራችን ላይ ዎርድፕረስ ካሁን በኋላ ለዘላለም ወደ አማርኛ ለመተርጎም ብዙ ጊዜ አይወስድም ማለት ነው።
ስለሚወራረስና በሚቀጥለው ዝርያ የሚኖሩት ለውጦች ትንሽ ስለሚሆኑ በአመት አንድ ጊዜም ቢሆን እነዚያን ለማየት
አንድ ሰው መጎብኘቱ አይቀርምና ያልተተረጎሙትም ምን አልባት በዚያን ጊዜ መልስ ያገኙ ይሆናል። ፋንታው፣ አንድን
ነገር ሳተጠናቅቅ አንጠልጥሎ መሄድ እንደሚደብርህ አውቃለሁ። ነገርግን አንዳንድ ስራዎችን ፺% ተሰርተው ሙሉ
በሙሉ እንደተሰሩ የምንቆጥራቸው ነገሮች አሉ ብዬ አምናለሁ።
2) Streamed rtsp resources should be added to the QT Src field under
the advanced tab.
3) GNU Library General Public License