What do you think about this guys?

9 views
Skip to first unread message

Fantaw Tesema

unread,
Nov 16, 2014, 2:12:20 PM11/16/14
to linux-e...@googlegroups.com
Your web host or server administrator has disabled PHP's fsockopen or gethostbynamel functions. Akismet cannot work correctly until this is fixed. Please contact your web host or firewall administrator and give them this information about Akismet's system requirements.

ትርጉም፤
የድረገጽዎ አስተናጋጅ ወይም አገልጋይ አስተዳዳሪ የፒኤችፒ ኮዱን fsockopen ወይም የgethostbynamel ተግባሮችን አቦዝኟቸዋል።  ይህ እስካልተጠገነ ድርስ አህክስመት በትክክል አይሰራም።  የድረገጽ አስተናጋጅዎን ወይም የእሳት ግድግዳ አስተዳዳሪውን ተገናኝተው ስለ አህክስመት የተጠየቁትን የስርዓት መስፈርት  መረጃወች ይስጧቸው።

A network problem or firewall is blocking all connections from your web server to Akismet.com. Akismet cannot work correctly until this is fixed. Please contact your web host or firewall administrator and give them this information about Akismet and firewalls.

ትርጉም
ከድረግጽዎ አገልጋይ ወደ አህክስመት ዶት ኮም ያሉትን ግንኙነቶች የአውታረ መረብ ችግር ወይም እሳት-ግድግዳ እያገደው ነው። ይህ እስካልተጠገነ ድርስ አህክስመት በትክክል አይሰራም። የድረገጽ አስተናጋጅዎን ወይም የእሳት ግድግዳ አስተዳዳሪውን ተገናኝተው  ስለ እዚህ የአህክስመትና እሳት ግድግዳ መረጃ ይስጧቸው።

ማሳሰቢያ፤
ግሎሰሪው ላይ firewall "ኬላ" ትብሏል። ኬላ ትክክል ነው? ለጊዜው እሳት ግድግዳ ብየዋለሁ።  //ፋተ

Eyob Fitwi

unread,
Nov 16, 2014, 2:24:45 PM11/16/14
to linux-e...@googlegroups.com
I would prefer this:

የእርስዎ የድር አስተናጋጅ ወይም የአገልጋይ አስተዳዳሪ የፒኤችፒ fsockopen ወይም gethostbynamel ተግባራትን አሰናክለዋል። ይህ እስካልተጠገነ ድረስ አኪስመት በትክክል ሊሰራ አይችልም። እባክዎ የድር አስተናጋጅ ወይም የኬላ አስተዳዳሪዎን ያግኟቸውና ይህን የአኪስመት ስርዓት ማሟያዎች መረጃ ይስጧቸው።

አንድ የአውታረ መረብ ችግር ወይም ኬላ ከእርስዎ ድር አገልጋይ ወደ Akismet.com የሚሄዱ ሁሉንም ግንኙነቶች እያገደ ነው። ይህ እስካልተጠገነ ድረስ አኪስመት በትክክል ሊሰራ አይችልም። እባክዎ የድር አስተናጋጅ ወይም የኬላ አስተዳዳሪዎን ያግኟቸውና ይህን የAkismet እና ኬላዎች መረጃ ይስጧቸው።

Somethings cannot be translated into Amharic. In this case we need to give accurate information which the user can make of, so we need to leave Akismet.com untouched because he/she will not be entering a translated አኪስመት.ኮም in the address bar. Others that cannot be translated are product names or product version names; this is the general practice as they are considered trademarks.

Also,
Website - ድር ጣቢያ
Webpage - ድረ-ገጽ
Web - ድር

We need to differentiate between these as they represent different things and we must uphold our accuracy. I know, it can be tricky sometimes :-).

I hope I helped.

Best regards,
Eyob

You received this message because you are subscribed to the Google Groups "Gnu/Linux Ethiopia" group.
To unsubscribe from this group and stop receiving emails from it, send an email to linux-ethiopi...@googlegroups.com.
For more options, visit https://groups.google.com/d/optout.

Fantaw Tesema

unread,
Nov 16, 2014, 3:00:23 PM11/16/14
to linux-e...@googlegroups.com
አመሰግናለሁ። ልክ ነው ስሞችን እንዳሉ መጻፍ ይሻላል። አባባላችውም ላይ ከመንተባተብ ያድናል። በጣም ምክንያታዊ ባልሆንም አማርኛ ብቻ እንዲታይ አስቤ ነው። ከዛም ተጠቃሚው በራሱ አድራሻ እንዲጽፍ። ሰውን ማልፋት!
ለነዚህም አመሰግናለሁ።

Website - ድር ጣቢያ
Webpage - ድረ-ገጽ
Web - ድር

አሁን እንደሚከተለው ሆኖ ተስተካክሏል። ፋየርወልንስ ምን እንበለው?
Your web host or server administrator has disabled PHP's fsockopen or gethostbynamel functions. Akismet cannot work correctly until this is fixed. Please contact your web host or firewall administrator and give them this information about Akismet's system requirements.

ትርጉም፤
የድር አስተናጋጅዎ ወይም አገልጋይ አስተዳዳሪ የፒኤችፒ ኮዱን fsockopen ወይም የgethostbynamel ተግባሮችን አቦዝኟቸዋል። ይህ ከመስተካከሉ በፊት Akismet በትክክል አይሰራም።  የድር አስተናጋጅዎ ወይም የእሳት ግድግዳ አስተዳዳሪውን ተገናኝተው ስለ Akismet የተጠየቁትን የስርዓት መስፈርት  መረጃወች ይስጧቸው።

A network problem or firewall is blocking all connections from your web server to Akismet.com. Akismet cannot work correctly until this is fixed. Please contact your web host or firewall administrator and give them this information about Akismet and firewalls.

ትርጉም
ከድር አገልጋይ ወደ Akismet.com ያሉትን ግንኙነቶች የአውታረ መረብ ችግር ወይም እሳት-ግድግዳ እያገደው ነው። ይህ እስካልተጠገነ ድርስ Akismet በትክክል አይሰራም። የድር አስተናጋጅዎን ወይም የእሳት ግድግዳ አስተዳዳሪውን ተገናኝተው ስለ እዚህ Akismet እና እሳት ግድግዳወች መረጃ ይስጧቸው።

tegegne tefera

unread,
Nov 16, 2014, 3:14:56 PM11/16/14
to linux-e...@googlegroups.com
ይኼስ
server ተጠሪ ወይም አዳይ
client ጠሪ ወይም ታዳይ

የድር አዳይ = መረብአዳይ= web server
ፋይል አዳይ፣ ሰነድ አዳይ፣ መረጃ አዳይ= file server, document server, data server
ጠሪ አስሊ፣ ታዳይ አስሊ = clint computer

tegegne tefera

unread,
Nov 16, 2014, 3:25:42 PM11/16/14
to linux-e...@googlegroups.com
firewall የሳት አጥር
ፈረንጆቹ እንደ አጥር የሚጠቀሙበት ብዙ ግድግዳ ስላላችው ምን እንደሆነ ይገባቸዋል። ለኛ ከፈረንጆቹ wall ጋር
የሚመሳሰለው አጥር ነው ብዬ እገምታለሁ።

tegegne tefera

unread,
Nov 16, 2014, 3:30:07 PM11/16/14
to linux-e...@googlegroups.com
ኬላ ትክክል አይሆንም። የይለፍቃል ጽፈህ የምታልፍበትን ኬላ ብትለው ትክክል ሊሆን ይችላል። firewall ግን
አጥር ነው። ያንን ለማሳለፍ መሸንቆር፣ ቀዳዳ መክፈት አለብህ። opening a port ይባላል.

Fantaw Tesema

unread,
Nov 16, 2014, 3:47:02 PM11/16/14
to linux-e...@googlegroups.com
አመሰግናሁ!

Firewall = የሳት አጥር። ትክክል ነው ብዬ አስባለሁ። ይህን አስተካክላለሁ።

እነዚህ ከታች ያልካቸው፤
server ተጠሪ ወይም አዳይ
> ይህ (ግሎሰሪው ላይ አገልጋይ ተብሏል)
client ጠሪ ወይም ታዳይ
> ይህ (ግሎሰሪው ላይ ተገልጋይ ተብሏል)
ግሎሰሪው ላይ የተባለው ትክክል ይመስለኛል። ምናልባት ሌሎቻችሁም አስተያየት ስጡበት! //ፋተ

Fantaw Tesema

unread,
Nov 17, 2014, 1:14:11 AM11/17/14
to linux-e...@googlegroups.com

Hey Tegegne.
Sorry did you mean Firewall translated to only Atir? That sounds perfect. Please let me know and I will go back again and correct it. Nice day. FT

tegegne tefera

unread,
Nov 17, 2014, 2:38:00 AM11/17/14
to linux-e...@googlegroups.com
ሳስበው "የአሳትአጥር" ቢባል ከንግሊዘኛው ትርጉም ጋር በቅርጽም በይዘትም ይመሳሰላል። በዛው ላይም ቃሉ
ድራማ አለው። አገላለጹ ስራውን ይስለዋል። አንዲህ አአይነት ነገር ጽንሰ ሃሳቡን ለመረዳት ይጠቅማል።
server ለሚለው አገልጋይ የሚለው ምንም አንክዋን በቅርጽ ቢመስልም ይዘቱ ግን ሌላ ነው። አገልጋይ የሚለው
በአማርኛው አገላለጽ የከፍታና ዝቅታ ልዩነትን ሲያሳይ server የሚለው የስራ ድርሻን ብቻ ነው
የሚያመለክተው። ስለዚህ አስሊዎቹ ምን ሥራ አንደሚሰሩ የተሳሳተ መልአክት ያስተላልፋል።
ለዚህ ነው ቀደም ስል መድብለ ቃላቱን የጻፉት ሰዎች የቁዋንቁውን ቅርጽ ብቻ አይተው ከሥራው ጋር ብዙም ተዛምዶ
የሌለው ቃል የሸነቆሩበት ብዬ የማምነው። ባለሙያዎቹ ለቅዋንቅዋው ቦታ አልሰጡትም የቁዋንቁዋ አዋቂዎቹ ስራውን
ለማወቅ ጥረት አላሳዩም ያልኩት። ስለዚህ በሂደት አንዲህ አየተነጋገርን ብናሻሽለው ጥሩ ነው ብዬ አገምታለሁ።

Fantaw Tesema

unread,
Nov 17, 2014, 2:55:22 PM11/17/14
to linux-e...@googlegroups.com
Firewall = የእሳትአጥር ወይስ አጥር?
የእሳትአጥር እንግሊዘኛውንም የሚወክል ይመስለኛል። ስለዚህ ክለሳው ላይ እስከዛሬ የተተረጎሙትን አስተካክላለሁ።
አጥር ባጭሩ ጥሩ ነው ግን የተለምዶ አጥርና ሌላም ትርጉም ሰጥቶ ምናልባት ውዥንብር እንዳይፈጥር የእሳትአጥር የሚሻል ይመስለኛል። ሌላ የሚቃወም ከሌለ!

በዚሁ አጋጣሚ እንደዚህ አይነት ሁለት ቃላት ያላቸው ሆነው ግን አንድ ቀጥተኛ ትርጉም የሚሰጡ ከሆነ ነጥሎ "የእሳት አጥር" ከማለት "የእሳትአጥር" ማለቱ በአማርኛ ብዙም ያልተለመደ ቢሆንም ሳይለያይ ቢተረጎም ደህና ይመስላኛል። ሌሎችም ይህን የመሰሉ ሲመጡ እንደዛው። ለምሳሌ Website = ድረገጽ። ድረ-ገጽ ከማለት። የዚህ አይነት ደንብ ከተከተልን አንድ አይነት ደንብ ስለምንከተል ይቀላል። ለተጠቃሚውም አንድ አይነት ይሆንለታል። እናንተስ ምን ትላላችሁ?

Server ፈረንጆቹም ምናልባት ከምግብና መጠጥ አቅራቢ ጋር አዛምደውት ይሆናል። ዞሮ ዞሮ ያው ከፍና ዝቅ ሊያደርግ ይችላል። አዳይ ማለትም ጥሩ ነው። ለኔ አገልጋይ ማለቱ በጣም ጥሩ ቢሆንም አገልጋይ አይተጣጠፍም። ለምሳሌ File server ለማለት ሰነድ አገልጋይ ወይም የሰነድ አገልጋይ ብሎ መተርጎም ትንሽ ይከብዳል። ግን እንደጠቀስከው "ሰንድ አዳይ" ከተባለ በቀላሉ ሊረዱት ይችላል።

አሁንም Document እና File እየተምታቱ "ሰነድ" ተብለው ተተርጉመው የተለያየ ቦታ አይቻለሁ። ይህም እልባት ማግኘት አለበት።

ሌላው ደግሞ Computer ለማለት አስሊ ካልን Calculator ምን ሊባል ነው? ይህንንም መነጋገር አለብን። //ፋተ

tegegne tefera

unread,
Nov 18, 2014, 9:16:56 AM11/18/14
to linux-e...@googlegroups.com
ጥሩ ጥሩ ጥያቄዎችን ነው እያነሳህ ያለኸው። እንግሊዘኛው መቼም የመጀመሪያው የአስሊ ቋንቋ ስለሆነ አንዳንዴ
ስህተቶች ይፈጠራሉ። የሥስነገር ምንጭ ድርሰት (software source code) ሊሻሻልና እንደ አዲስ ሊጻፍ
ሲችል ገጽታውና ከሰው ጋር የሚግባባበት ቃላት በቀላሉ መለወጥ አስቸጋሪ ነው። ሰው የያዘውን ነገር አይለቅም።
ስለዚህ ስህተቶቹ ተያይዘው ይዘልቃሉ። computer እና calculator እንደምሳሌ መውሰድ እንችላለን። ቃሉም
ስራውም አንድ ነው። calculator computer ነው computer ደግሞ calculator ነው። እኛ ያንን
ስህተት መውረስ ያለብን አይመስለኝም። የቋንቋ ስህተት የጽንሰ ሃሳብ ስህተት ይፈጥራል። አንድ ሰው አንዱን
ከሌላው የተለየ አድርጎ እንዲያስብ ያደርገዋል። ትክክል ያልሆነ እውቀት ያስተላልፋል። ስለዚህ ሁለቱንም አስሊ
ብንላቸው ትክክል ይሆናል፣ የተሻል ትርጉም ይሰጣል እንጂ አይጎዳም።

የfileና የdocument እንደዚሁ ትንሽ አውናባጅ የሆነ ነገር ነው። በተለይ ከኛ አገር ካለው የፋይል
አጠቃቀም ጋር ሲገናኝ።
እኔ እንደምረዳው (አርሙኝ ከተሳሳትኩ) ሁሉም document፣ file ነው። ግን ሁሉም file፣ document
አይደለም። ስለዚህ "ሰነድ" የሚለውን document ብንጠቀምና file የሚለውን "ፋይል" ብንለው ትክክል
ይመስለኛል።

ልብ አድርጉ። ይኼ ለኔ sense የሚሰጠኝን ነገር ነው የምጽፈው። ለአንድ ሰው መሰለው ማለት ትክክል ይሆናል
ማለት አይደለም። ስለዚህ የግድ ሌሎችም ሲያነቡት የመቻቸው እንደሆን ወይም አንዳልሆነ ቢገልጹ ጥሩ ነው። ብዙ
ሰው ከተመቸው ትክክል ነው ማለት ነው። ካልተመቸው ደግሞ ትክክል አይደለም ማለት ነው። ስለዚህ ውድ አድፋጮች
አልተመቸኝም ብትሉ ተርጓሚዎቹ አይበሽቁም። ደስ ይላቸዋል እንጂ። የሚለፋበት ነገር ጠፍጦ እንዲበላ እንደሚፈልግ
ወጥ ቤት ማለት ነው።
ሃሃሃሃሃ

Fantaw Tesema

unread,
Nov 18, 2014, 2:58:28 PM11/18/14
to linux-e...@googlegroups.com
ማብራሪያህ በጣም ጥሩ ነው! አነበብኩት።

ትርጉሙን በተመለከተ ደግሞ፤
calculator እና computer አንድ አይነት ሆነው መተርጎም የለባቸውም ባይ ነኝ። የተለያየ ስም መጠት ወይም calculator ን አስሊ  computer
ን ኮምፕዩተር ማለትም አንድ ምርጫ ነው።

ፋይልና ዶክመንት ደግሞ፤
ይህ አባባልህ "ሁሉም document፣ file ነው። ግን ሁሉም file፣ document አይደለም።" ትክክል ነው። ምናልባት የሁለቱም አተረጓጎም በአማርኛ ምን እንደሚሆን የሚሻሻል ነገር አለ?
ትንሽ ፍንጭ የሚሰጥ ከሆነ ማብራሪያ ከታች ቀርቧል።
File
A collection of information that is stored on a computer under a single name.

Document:
Any self-contained piece of work created with an application program and, if saved on disk, given a unique filename by which it can be retrieved.
//ፋተ

tegegne tefera

unread,
Nov 19, 2014, 4:24:18 AM11/19/14
to linux-e...@googlegroups.com
On Nov 18, 2014 8:58 PM, "Fantaw Tesema" <fan...@gmail.com> wrote:
ማብራሪያህ በጣም ጥሩ ነው! አነበብኩት።

ትርጉሙን በተመለከተ ደግሞ፤
calculator እና computer አንድ አይነት ሆነው መተርጎም የለባቸውም ባይ ነኝ።
ሃሃሃ
ለምን?? ጥሩ ምክንያት እኛ ብቻ ነን የምንጠየቀው?

Fantaw Tesema

unread,
Nov 19, 2014, 2:45:46 PM11/19/14
to linux-e...@googlegroups.com
ለምን ማለት ጥሩ ጥያቄ ነው!!
ምክንያቱም እንደሚመስለኝ calculator እና computerአንድ አይነት ስም ካላቸው የትኛው የቱ እንደሆነ መለየት ያስቸግራል። ለምሳሌ አንድ ሰው ለጓደኛው ዛሬ አስሊ ገዛሁኝ ቢል calculator ወይም computer መሆኑን እንደገና ማስረዳት አለበት ማለት ነው። ሌላው ደግሞ ለምሳሌ አንድ የኮምፕዩተር ተጠቃሚ ደስክቶፑ ላይ ኮምፕዩተርና ካልኩሌቶር ሲከፍትም ሆነ ሲጠቀም የተለያዩ ናቸው። ተመሳሳይና አንድ  ኮምፕዩተር ላይ የcalculator እና computer ስማቸው አንድ አይነት መሆን ያለብት አይመስለኝም። ለምሳሌ የኮምፕዩተር ስም ደስክቶፕ ላይ አለ። calculator ደግሞ መጠቀም ሲያስፈልግ ተጠቃሚው አክሰሶሪስ የሚለው ጋ ሄዶ calculator የሚለውን ስም እንጂ computer የሚለውን ስም ጠቅ አያደርግም። ምሳሌ ብዙ ነው!!! //ፋተ
Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages