WP to Amharic reached 90% now. Green zone!!!

10 views
Skip to first unread message

Fantaw Tesema

unread,
Nov 11, 2014, 4:42:58 PM11/11/14
to linux-e...@googlegroups.com
ታዲያስ ሁላችሁም!
ወርድፕሬስ ትርጎማው አሁን 90% ደርሷል። 90% ከደረሰ በኋላ በአረንጓደ ምልክት ይደርገበታል። ጥሩ እየሄደ ነው። 98% አካባቢ እስከሚደርስ አልተረጎምኩም ግን እቀጥላለሁ። እስካሁን ከሄድኩባቸው ቀደም ብየ ልጠይቃችሁ ብየ ነው። ከትንሽ ጊዜ በኋላ ሌላ ተጨማሪ ጥያቄ ይኖረኛል። በተረፈ ጊዜያችሁን ተጠቀሙ።
ትርጎማን በተመለከተ ስታንዳርድ የሚባል ነገር እስካሁን አላየሁም። ምናልባት እየተነጋገርን ስታንዳርዱን እንሰራው ይሆናል!!!

እንዲሁ ለመግለጽ ያህል እንደነገሩ ለመጨረስ ቢሆን ኖሮ እስካሁን ጨርሼ ነበር። ትልቅ ዋጋ መሰጠት ያለበት ትርጉሙን ለመረዳት ቀላል፣ ግልጽና ለመጠቀም የሚገፋፋ መሆን አለበት ብየ አምናለሁ።

1ኛ) ተያያዡ ሰነድ ላይ አንዳንድ ቃላት ሌላ ቦታ የተተረጎሙት ሳያረኩኝ ሲቀሩና አደናጋሪ ስለሆኑ በተቻለ መጠን በርካታ ነገሮች አገላብጨና ፈልጌ ሰነዱ ላይ የምታዩት አይነት ድምዳሜ ላይ ደርሻለሁ። ብዙ አይደሉም። በዛውም ቀጥያለሁ። ሆኖም ግን የበለጠ ትክክል እንዲሆን አስተያየታችሁን እፈልጋለሁ። ሌላ ትርጉም የምትሰጡ ከሆነ ከማብራሪያ ጋር ምክንያታችሁን እንደምትገልጹ ተስፋ አለኝ።

2ኛ) ከዚህ በታች ደግሞ ምሳሌ ነው።
አቀማመጣቸው ተቀይሮ የተተረጎሙ ምሳሌወች፤
Your account is now activated. Log in or go back to the homepage.     አሁን መለያወ ተቀስቅሷል። ይግቡ ወይም ወደ መነሻ ገጽ ይመለሱ።

Please upgrade WordPress to a current version, or downgrade to version 2.4 of the Akismet plugin.

ወደ ወቅታዊው ስሪት ወርድፕሬስን አሳድግ ወይም ወደ አህክስመት ውታፍ ስሪት 2.4 አሳንስ።.

Akismet has protected your site from %3$s spam comments.

አህክስመት ከ %3$s አይፈለጌ አስተያየቶች ድረገጽወን ተከላክሉወለታል።

msgid "Basics of Rich Editing"
msgstr "መሰረታዊ ምርጫ የበዛበት አጻጻፍ "

msgid "Advanced use of the Rich Editor"
msgstr "የረቀቀ ምርጫ የበዛበት ማደቻ አጠቃቀም "

msgid "Rich Editing Basics"
msgstr "መሰረታዊ ምርጫ ያለበት አጻጻፍ "

msgid "Sorry, that file cannot be edited."
msgstr "ይቅርታ፤ ያ ሰነድ መታደት አይችልም።"

msgid "%s exceeds the maximum upload size for the multi-file uploader when used in your browser."
msgstr "%s የኢንተርኔት ማሰሻወ ጥቅም ላይ በሚውል ጊዜ በርካተ ሰነዶች ጫኙ መጫን ከሚችለው ከፍተኛ መጠን ድንበር ያልፋል።"

3ኛ)
ከዚህ በታች ያሉትስ እንደት ይተርጎሙ? አስተያየት አላችሁ?
Jan_January_abbreviation
Feb_February_abbreviation
Mar_March_abbreviation
Apr_April_abbreviation
Your key has been cleared.
navigate
//ፋተ
some-translation.xls

tegegne tefera

unread,
Nov 12, 2014, 3:48:37 PM11/12/14
to linux-e...@googlegroups.com
ሰላም ፋንታው፣ utmarket:-) አስተያየቶቼ በየሓረጉ ስር እነሆ

> 2ኛ) ከዚህ በታች ደግሞ ምሳሌ ነው።
> አቀማመጣቸው ተቀይሮ የተተረጎሙ ምሳሌወች፤
> Your account is now activated. Log in or go back to the
> homepage. አሁን መለያወ ተቀስቅሷል። ይግቡ ወይም
> ወደ መነሻ ገጽ ይመለሱ።
http://am.wiktionary.org/wiki/computer_glossary_A ይህንን መዝገበ ቃላት ምን ያህል
እንደምትጥቀምበት አላውቅም ግን ትርጓሜዎቹ ጥሩ ናቸው። በሁሉም ባልስማማም። ከዚያም በላይ በሳይንስና ቴክኖሎጂ
ባለስልጣን ድጋፍ የተሰራ ስለሆነ በአብዛኛው ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከዚያ ውጪ ያሉ የ ሶፍትዌር ኩባንያዎች
ለአማርኛ ትርጉም ስለሚጠቀሙበት የኛ ያንን ትርጉም መቀየሩ ባንወደውም ምንም ለውጥ አያመጣም ስራ ከማብዛት
በስተቀር። አልፎተርፎ አንድ ቃል የሆነ ትርጉም ይዞ ከተለመደ ቆይቶ ውጤቱ ያው ነው። ይህንን ያልኩበት
"account" ለሚለው "መለያ" ብለህ ስላልክ ነው። ሃሳብህ ቢገባኝም መዝገበ ቃላቱ ላይ ያለውን "መዝገብ"
ብትጠቀም ይሻላል ባይ ነኝ።

> Please upgrade WordPress to a current version, or  href="%s">downgrade to version 2.4 of the Akismet plugin.

> ወደ ወቅታዊው ስሪት ወርድፕሬስን አሳድግ ወይም ወደ አህክስመት ውታፍ
> ስሪት 2.4 አሳንስ።.

እዚህም "ዝርያ" በሚለው ቢተካ

> Akismet has protected your site from %3$s
> spam comments.

> አህክስመት ከ %3$s አይፈለጌ አስተያየቶች ድረገጽወን
> ተከላክሉወለታል።

"አላስፈላጊ" ወይም "ስርዓት ያልጠበቁ" አስተያየቶች በሚል ቢተካ።

> msgid "Basics of Rich Editing"
> msgstr "መሰረታዊ ምርጫ የበዛበት አጻጻፍ "

እዚህም ጋ ትንሽ ቅሬታ አለኝ ግን የተሻለ ትርጉም አፌ ላይ አልመጣም ብሎኛል። ለማንኛውም ትኩረት ለመሳብ ስል

> msgid "Advanced use of the Rich Editor"
> msgstr "የረቀቀ ምርጫ የበዛበት ማደቻ አጠቃቀም "

> msgid "Rich Editing Basics"
> msgstr "መሰረታዊ ምርጫ ያለበት አጻጻፍ "
ልክ እንደ ከላይኛው

> msgid "Sorry, that file cannot be edited."
> msgstr "ይቅርታ፤ ያ ሰነድ መታደት አይችልም።"
ማረም፣ መታረም፣ ቢባልስ

> msgid "%s exceeds the maximum upload size for the multi-file uploader when
> used in your browser."
> msgstr "%s የኢንተርኔት ማሰሻወ ጥቅም ላይ በሚውል ጊዜ በርካተ ሰነዶች ጫኙ መጫን ከሚችለው ከፍተኛ መጠን ድንበር
> ያልፋል።"

አላማረኝም፣ እስቲ እናስብበት ለተሻለ።

> 3ኛ)
> ከዚህ በታች ያሉትስ እንደት ይተርጎሙ? አስተያየት አላችሁ?
> Jan_January_abbreviation
> Feb_February_abbreviation
> Mar_March_abbreviation
> Apr_April_abbreviation
የመጀመሪያው ጥያቄ ወሮቹ እንደለ ይቀመጡ ወይስ ወደ አማርኛ ይተርጎሙ። ጥር፣ የካቲት ወዘተ

> Your key has been cleared.
ቁልፉ ተሰርዟል ወይም ተለቋል፣ እንደአገባቡ

> navigate
ቃኝ

> //ፋተ

> You received this message because you are subscribed to the Google Groups
> "Gnu/Linux Ethiopia" group.
> To unsubscribe from this group and stop receiving emails from it, send an
> email to linux-ethiopi...@googlegroups.com.
> For more options, visit https://groups.google.com/d/optout.

መልካም ስራ
ተገኝ

Fantaw Tesema

unread,
Nov 12, 2014, 4:55:05 PM11/12/14
to linux-e...@googlegroups.com
ታዲያስ ተገኝ!
ከላይ ያቀረብኳቸው ከአስቸጋሪወቹ ትርጓሜወች ውስጥ አውጥቼ ነው። እኔም ስላልረካሁበት። አስተያየት እንዲትሰጡበት። እንደጠቀስኩት ሌሎችም አሉ።
የላከውንም አገናኝ ከዚህ በፊትም ልከኸው ስለንበር በየቀኑ እጠቀምበታለሁ። ያ ማለት ደግሞ አንዳንድ ጊዜ አንዳንድ ቃላት አተረጓጎማቸው ትንሽ ቅር ያሰኛል። አካውንት መዝገብ ወይስ መለያ?
በሰፊው አስቦ ምናልባት አካውንት መለያ ከሆነ አይዲ ደግሞ መታወቂያ ይሆናል የሚል ግምት ስላደረብኝ ነው። ኤዲት አዲት ከሆነ ኤዲቶር ማደቻ ይሆናል። አባባሉ በእንግሊዘኛ ሲቀየር አማርኛውም በዛው አዲት ዘመድ እየተቀያየረ ይሄዳልና አንድ አይነት ወጥ ይዞ ይሄዳል። አርም ካልክ ግን ኤዲቶርን ምን ልትለው ነው? ለእንደዚህ አይነት ሁኔታወችና ተያያዦች ላይ ለመወሰንና ትክክል ለማድረግ ጊዜ መጠቀም ያስፈልጋል።

navigate ስንል ደግሞ አቅጣጫ እንደመምራት ማለት ነው። ለዚህ ትርጉም እስካሁን ምንም አላገኘሁም። ሊለመድ ይችላል ተብሎ ትንሽ እንኳን ለተጠቃሚው የማይስብ ከሆነ ሰወች ትርጉሙን ላይጠቀሙበት ይችላሉ። እንግሊዘኛውን ይመርጣሉ። ያ አላማችን አይደለም።

ዝርያ ያልከው ትርጉም ግን አማራች ከሌለ በጣም ጥሩ ነው።

መልስ በምትሰጥ ጊዜ፤ ጊዜ ተጠቀምና እነዚህ አስቸጋሪ ናቸው ብዬ የላኳቸውን በሙሉ ትክክል ነው በምትለው መንገድ ተርጉመህ ሁላችንም ብናየው የተሻለ አማራጭ ነው። ከተቻለ ክምክንያት እና ከማብራሪያ ጋር። ምክንያቱም ምናልባት ለወደፊት ይረዳናል። እኔም እርዳታ ስጠይቅ ይህንን ነው የተመኘሁት። በተጨማሪ ደግሞ ተያያዥ ልኬአለሁ። እሱም ጋ አስተያየት ያስፈልገው ይሆናል። እዛም ላይ የአስተያየት ቦታ ከጎኑ ተዘጋጅቷል።

ትርጉማቸው ተያያዡ ላይ አለ ግን እንግሊዘኛው ይህን ይመስላል። ብዙወቹ የሚተረጎመው ውስጥ በብዛት አሉ። ሁለቱ ወይም ሶስቱ ወይም አራቱ በተቃራኒ ወይም በዝምድና ይጎራበታሉ ወይም ይቃረናሉ። የሚከተሉት ናቸው። ትርጉማቸው ተያያዡ ላይ።
Invalid
Valid
Disabled
Enable
Edit
Editor
cannot be edited
Draft
Pending
Network
update
upgrade
Plugin
Server
client
Browser
Version
revision
category
Taxonomy
database
Failed
Enter
Insert
Add
optional
Options
Item
install
installation
Not installed properly
To install
Load
upload
download
Spam
Junk
Log out/off
Sign up

በተረፈ የምጠቀመው፤
1) ወረቀት መዝገበ ቃላት። ሜሪት ይባላል።
2) ከላይ የላከውን አድራሻ።
3) http://amharicdictionary.com/
4) ስፈታትች ኢንተርኔት ላይ ያገኘሁት። https://glosbe.com/en/am/account
5) ሰወችን በመጠየቅ ነው።

ሁላችሁም ጊዜ ኖሯችሁ የላኳቸውን አስቸጋሪ/አስፈላጊ ትርጉሞች እንደምታዩአቸው አምናለሁ።
//ፋተ

Fantaw Tesema

unread,
Nov 13, 2014, 1:44:33 PM11/13/14
to linux-e...@googlegroups.com
ተገኝ፤
ዛሬ ቀኑን ስለ Account (መዝገብ) ያልከውን እያሰላለስኩ ነበር። ለምሳሌ፤
Register ተመዝገብ ወይም መዝግብ (እንደ አመጣጡ)
Account መዝገብ
Check your account  መዝገብወን ያጣሩ
Your account is enabled መዝገብወ ተቀስቅሷል
Your account is disabled መስገብወ ቦዝኗል (ለግሟል/ተኝቷል/አይሰራም) ምርጫወቹ ብዙ ናቸውና እዚህ ላይ መወሰን ተቸግሬአለሁ!
Your account is closed መዝገብወ ተዘግቷል
The account is active መዝገብወ ንቁ ነው
etc
እና ምናልባት መለያ ወይም መለያወ ከሚለው ይሻል ይሆናል። ትላንትና ወዲያውኑ ስላልገባኝ ይቅርታ።
የሌሎቹን ትርጓሜ ግን እየጠበኩ ነው። እንዳው ሁላችሁም እንድታውቁት ጊዜ ሲኖራችሁ እናንተም አስተያየት ብትሰጡ አሪፍ ነው። ቀስ እያልኩ ልክ እንዳለፈው ሳላበዛ አንዳንድ ጊዜ መላኬ አይቀርም። አስተያየትና እርማት ከናንተ ሲደርሰኝ ፈልጎ መተካት ስለሆነ ለኔ ምንም አያስቸግርም። //ፋተ

Fantaw Tesema

unread,
Nov 13, 2014, 1:48:01 PM11/13/14
to linux-e...@googlegroups.com
The account is active መዝገብወ ንቁ ነው
ያለፈው መልእክት ላይ 'መዝገቡ ንቁ ነው' ለማለት ነው። //ፋተ

Best regards

ለሚሰሩ እጆች፣ ለሚያስቡ አዕምሮወችና ለሚወዱ ልቦች፡፡
Improvement is always possible if you take action.
www.ethiopiawakeup.net

JOB

unread,
Nov 13, 2014, 2:16:32 PM11/13/14
to linux-e...@googlegroups.com
Hi,

There is an official glossary, which I've attached. I've also commented on the translations in the excel file here.

Also here are my comments for the other ones:

Register ተመዝገብ ወይም መዝግብ (እንደ አመጣጡ)
Account መለያ
Check your account  መለያዎን ያጣሩ
Your account is enabled መለያዎ ነቅቷል
Your account is disabled መለያዎ ተሰናክሏል (ለግሟል/ተኝቷል/አይሰራም) ምርጫወቹ ብዙ ናቸውና እዚህ ላይ መወሰን ተቸግሬአለሁ!
Your account is closed መለያዎ ተዘግቷል
The account is active መለያዎ ገቢር ነው

Best regards,
Eyob
ICT Glossary_Amharic-Tigrigna-Oromifa Languages.pdf

tegegne tefera

unread,
Nov 13, 2014, 4:48:30 PM11/13/14
to linux-e...@googlegroups.com
ምስጋና እዮብ
አማርኛ ውክሽነሪ ላይ ያለው ይኼ ያያያዝከው መድብለ ቃላት ናቸው። አሳዛኙ ነገር ያንን የሰሩት ሰዎች ብዙም ወይ አላሰቡበትም ወይም ስለክምፑተር ብዙም የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ያሳብቅባቸዋል። በዚህ ደረጃ አንድ ስራ ሲሰራ ትንሽ የተሻለ ቅንብር ሃላፊነት ሊሰማ ይገባ ነበር። ለዚህ ብዙ ገንዘብ እንደወጣበትም ጥርጥር የለውም።
ለምሳሌ አንድ ምሳሌ ብሰጥህ "ድረገጽ" የሚለውን ቃል ብትወስደው የቋንቋውን መሰረታዊ ህግ ያልተከተለ ጸያፍ ሊባል የሚችል ነው።
ብዙ ጊዜ አማርኛ ሁለት ዓይነት አገላለጾችን ይጠቀማል። አንዱ የግዕዝ ሲሆን ሌላው የአማርኛ ነው። ለምሳሌ መጽሐፍቅዱስ የግዕዙ ተወራሽ ሲሆን አማርኛ ግን ቅዱስ መጽሐፍ ሊልም ይችላል። ውዳሴ ማርያም የሚለውን የማርያም ውዳሴ ቢባል ለቋንቋው ትክክል ይሆናል።

ድር የሚለው ራሱ ትክክል አይደለም። ዌብ የሚለው የንግሊዘኛ ቃል መረብ ለሚለው እንጂ ድር ሊሆን ባልተገባው። ከዛም አልፎ ወይ "የድርገጽ" አለዚያ "ገጸድር" እንጂ ድረገጽ ብሎ ቃል ሊኖር አይችልም።

አዲስ ቃላት መፍጠር ወይ መውረስ አንድ ነው እንዲህ ዓይነት ስህተት መስራት በተለይ እንደኮምፑተር የሁሉንም ሰው ህይወት ሊነካ የሚችል ነገር ላይ ትንሽ ሃላፊነት ያለመሰማት ይመስለኛል።

ይህንን ይህንን እንዴት እንደሚሆን በውነት መልስ የለኝም። ነገርግን ምን አልባት ሁሉም ሰው የራሱን ትርጉም ይዞ ብይመጣም ሁሉም ሰው ሌላው ቢቀር ይኼ ተሻለኝ ቢል ለአብዛኛው ሰው የተሻለው እንደ ተመራጭ ቢወሰድ ጥራት ያለው ስራ ሊሰራ ይችላል። ይቺን ወደድኳት ማለት እንኳን ትልቅ አስረዋጽዖ ነው።

አሁን የኛ ችግር የሆነው ወይ ትልቅ አስተዋጽዖ ማድረግ አለብን ያ ካልሆነ እጃችንን አጣጥፈን እንቀመጣለን። እውነቱ ግን ካንድ አዋቂ ትልቅ አስተዋጽዖ የብዙ የሚደማመጡ ሰዎች ትትንሽ አስተዋጽዖ የበለጠ ጠቀሜታና ጥራት እንዳለው እንዴት ላሳይ እንደምችል ግራ ግብት ይለኛል።

ለማንኛውም እስቲ የመረብ ገጹ ሲሰራበት እንዴት እንደሚመስል ብናየው ተግባር ላይ መልስ ሊሰጠን ይችላል።

መልካም ስራ

Eyob Fitwi

unread,
Nov 14, 2014, 6:36:29 AM11/14/14
to linux-e...@googlegroups.com
ውድ ተገኝ፣

ልክ ብለሃል። እኔም እኮ ችግር እንዳለበት ሳላስተውል ቀርቼ አይደለም። ነገር ግን የአገሪቱን የትርጉም መስፈርት ተብሎ በይፋ የታወጀ ነገር ስለሆነ እያቻቻልን ከእሱ ጋር ማስታረቅ ይኖርብናል። አለበለዚያ ከእነጉግል፣ ማይክሮሶፍት እና ሌሎች ትልልቅ የአይቲ ኩባንያዎች የአማርኛ ትርጉም ጋር ላንጣጣም ነው። ግን በራሳችን እንቅስቃሴ እና ምርት ላይ የራሳችን አካሄዶች መከተል አንችልም ማለት አይደለም። በጣም አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እሱን ትተን የራሳችንን መንገድ መከተል ግድ ሊሆን ይችላል። ግን በጥንቃቄ ነው እንደዚህ አይነት ውሳኔዎችን መውሰድ ያለብን። እየከፈሉ የአማርኛ ትርጉም የሚያሰሩ ድርጅቶች ሁሉ አንዳንድ ጊዜ ሌላው ምን ብሎ ተረጎመ ብለው ማየታቸው አይቀርም፣ የሚያስተረግሙት ነገር ወጥነት ያለውና ሰዉ ሌላ ቦታ ላይ ሊረዳው የሚችል እንዲሆን ስለሚፈልጉ። ግን እነሱም ቢሆኑ አንዳንድ ጊዜ በጣም የማያስኬድ ነገር ሲያጋጥማቸው በመሰላቸው መንገድ በቋንቋ ኃላፊው አማካኝነት የራሳቸውን አካሄድ ይሄዳሉ።

ያለው ሌላ ችግር ደግሞ ከአገራችን እና ከቋንቋው እድገት ጋር የተያያዘ ነው። የኃላፊነት ስሜት ማጣት ትልቅ ችግር እንዳለ ሆኖ ኃላፊነቱ የተሰጠው የመንግስት አካል ፈተና የሚሆንበት ከቋንቋ ተናጋሪው እንደ ግብዓት ሊወስዳቸው የሚችለው በተለይ አኅዘቦት ያላቸው ብዙ ቃላት ወይም መርጃዎች የሉም። ስለዚህ ብዙዎቹ ቃላት እንደ አዲስ መፈጠር አለባቸው፣ እና ይህ ደግሞ ዕድገት ለሚያስፈልገው ቋንቋ ፈተና ይሆናል። የእንግሊዝኛው ቀጥተኛ ትርጉም እንውሰድ ወይስ ስሜቱን በአማርኛ የሚገልጽ ቃል እንፈልግ? አየህ፣ ቃሉ ተፈጥሯዊ ሳይሆን ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ ነው የተፈጠረው፣ እና አኅዘቦት ለማግኘት እርዳታና ጊዜ ያስፈልገዋል፣ በተለይ የቃሉን ተጋላጭነት በመጨመር ረገድ። ለምሳሌ፣ አንዱ ተርጓሚ ኡቡንቱ ላይ "install"ን "መትከል" ብሎ ተርጉሞት አይቸው ነበር። በእርግጥ የቃሉን ስርወ ቃል ከተመለከትከው ትክክል ነው። ነገር ግን አስቀድሞ በሕዝቡ ልሳን የገባ ቃል አለ፦ "መጫን"። እንዲህ ያሉ አጋጣሚዎችን ምንም ልታደርጋቸው አትችልም። በቃ የቋንቋው ተፈጥሯዊ አካል ሆነው ዘልቀዋል። ድረ-ገጽም እንዲሁ።

ደግሞም ብዙ የትርጉም ልምድ ያለው ሰው የለም፣ በበጎ ፍቃድ ልሳተፍም ቢል። ምናልባት የሆነ ጦማር ቢጤ አዘጋጅተን ይህን እውቀታችን እና ልምዳችን ለማጋራት ብንንቀሳቀስ ሳይሻል አይቀርም። በአይቲ ላይ ብቻ ሳይሆን ስለአጠቃላይ ትርጉም። ካስፈለገም በበጎ ፍቃድ ትርጉም ላይ ልናተኩረው እንችላለን። ይሄ ከክፍት ምንጭ ሶፍትዌር ባሻገርም እንደ global voices online ባሉ ቦታዎች ላይ መሳተፉ የሚፈልጉ ወገኖቻችንን እንድናበቃ ሁላ ያስችለናል።

እኔ ትርጉም እንጀራዬ ነው። ለዚያውም ውዱ ነፍስ ጠባቂ እንጀራዬ! ያለኝን ልምድ ባካፍል ደስ ይለኛል። ያው የጊዜ መጣበብ ሆኖብኝ ነው እንዲህ የሚያስጠፋኝ። ከፈለጋችሁ የሆነ ነገር አደራጁና በማንኛውም ነገር ያላችሁን ጥያቄ ብትልኩልኝ ጊዜ ወስጄ ሁለገብ የሆነ መልስ ልሰጣችሁ እችላለሁ። እንዲያውም እንድትጀምሩ ሁሉ አበረታታችኋለሁኝ። እስቲ ተነጋገሩበት።

ከሠላምታ ጋር፣
እዮብ

Fantaw Tesema

unread,
Nov 14, 2014, 3:06:40 PM11/14/14
to linux-e...@googlegroups.com
ታዲያስ!
ለአስተያየትህና ለላከው ተያያዥ ትርጉም አመሰግናለሁ እዮብ። አንዳንድ የሚስተካከሉትን ሰሞኑን አርማለሁ። Account = መለያ ተብሎ ስለተተረጎመ ያንን መቀየር አያስፈልገኝም። አሁንም ትንሽ ግር እያለኝ ነው። በተለይ Edit  = አርትዕ እንደአስፈላጊነቱ የሚተጣጠፍ ሆኖ አላገኘሁትም። ለምሳሌ "Sorry, you are not allowed to edit posts in this post type" ለመተርጎም ሁለት ቃላት መጠቀም ያስፈልጋል ማለት ነው?  በተረፈ ከታችም እንደሚከተለው አስተያየት አለኝ።

ተገኝ።
በትክክል ከተረዳሁህ ባለፈው ጽሁፍ ላይ ስለተለያዩ ጉዳዮች አስተያየት ሰጥተሃል።
ለሁሉም ምክንያት መልስ መስጠት ባልፈልግም ከትርጉሙ ጋር የተያያዙ ዋና ዋናወች ጉዳዮችን ግን ትንሽ ልጥቀስ። ባለፈው ጊዜ የሚያስቸግሩኝን አተረጓጎሞች ለእርዳታ መላኬ አይቀርም ስል አንተም እዚሁ አቅርባቸውና እናያቸዋለን አልክ። እኔም ካስቸገሩኝ ውስጥ አንዳንዶቹን አቀረብኩ። ከቀረቡት ውስጥ አንተ በጣም ጥቂቶቹን ብቻ እና አለፍ አለፍ እያልክ መልስ ሰጠህ። እና የትኛውን መመረጥና መያዝ ስላልስቸገረኝ ጊዜ ተጠቅሞ ሁሉም አስተያየት የሚያስፈልጋቸው እንዲታዩ ጠየኩ። እኔም ምናልባት ለማብራራት ብዬ ብዙ ከምጽፍ ባጭሩ "ለሁሉም ጥያቄወች መልስ አልተሰጠም" ማለት መቻሌን አሁን ትዝ አለኝ። ለወደፊቱ ባጭሩ እጽፋለሁ። በርግጥ እንዳልከው ሁሉም ትንሽ ትንሽ ያቅሙን ሲያበረክት መጨረሻ ላይ ውጤቱ ያምራል። ነገር ግን ለምሳሌ እዛው ሲስተሙ ጋራ ከሆነ አንድ ሰው በፈለገበት ጊዜና አቅም ሲመቸው ሲስተሙ ውስጥ መተርጎም ይችላል። መልእክቱ በኢሜይል ሲመጣ ግን በተቻለ መጠን በአንድ ጊዜ እልባት ካላገኘ ተዘንግቶ ይቀራል ወይም ስራ ይጓተታል። ነካ ነካ ይሆናል። ከዚህ በፊት እዚህ ስንጻጻፍ የተጠየቁ ጉዳዮች ወዲያውኑ መልስ ሳያገኙ ሲቀሩ በዛው ተረስቶው ወይም የሚከታተላቸው ባለቤት አጥተው የቀሩ ጉዳዮች እንዳሉ አስታውሳለሁ።

ሌላው ደግሞ https://am.wiktionary.org/wiki/Comp_Glossary ላይ ብዙ የምፈልጋቸው ቃላት ተተርጉመው አላገኘሁም። ሌሎችንም አድራሻና ፍንጮች እንደተጠቀምኩኝ ጠቅሻለሁ። አንዳንድ ትርጉሞች ደግሞ ለሁለት ወይም ለሶስት እንግሊዘኛ ቃላት አንድ የአማርኛ ቃል ብቻ ሆኖ ተተርጉሟል። የሚሰጠው መልእክት ግን የተለያየ ነው። ለምሳሌ upload እና install አንድ አይነት ሊሆን አይችልም።  Enter እና እንሰርት አንድ አይነት ሊሆኑ አይችሉም። ሌሎችም አሉ። ይህ አማርኛው ላይ ብቻ እንዳልሆነ አይቻላሁ። ኦፐን ሶርስ ውስጥ ሌሎች ቋንቋወች ላይም በተለይ አሻሚ ትርጉም ያላቸው ቃላት አሉ።  የተሰራውን ስራ ዋጋ አለመስጠት ሳይሆን ያጋጠመኝን ሁኔታ ተባብሮ ለመፍታት ወይም ለማሻሻል ነበር የጠየኩት።  የቀረ ወይም ያነሰ ነገር ሲያጋጥም በዛው መቀጠል ያስቸግራል። ሁል ጊዜ ለመሻሻል ቦታ አለ። እርግጠኛ ነኝ ያንን የተረጎሙ ሰወች ትርጉሙ ውስጥ የሌሉ ቃላት እንዲጨመሩ፣ አንዳንድ የተተረጎሙም ቃላት ደግሞ እንዲሻሻሉ ሃሳብ ቢቀርብላቸው አይጠሉትም። ሁል ጊዜ መደጋገም፣ መተባበርና መነጋገር ለሚሰራው ስራ እንዲሻሻል ይረዳናል ለማለት እንጂ ችግር አለን ብዬ አላምንም። ምናልባት ወርድፕሬስ ተተርጉሞ ሲያልቅ ስለ አንዳንድ ቃላትና አባባሎች አስተያየት እንልክላቸው ይሆናል?  ምን ይታወቃል! ብቻ ለዛ ያብቃን።

እንደሚታወቀው እኔ አዲስ መጤ ነኝ። መተርጎም የጀመርኩትም ዘንድሮ ነው እና አንዳንድ ነገሮችን በጉጉትና በአዲስ አይን ስለማያቸው በርካታ ጥያቄወች ሊኖሩኝ ይችላሉ። ከሁሉም በላይ ግን ይህን የጀመርነውን ስራ ለማሳመር በመስራት፣ በመደጋገምና አብሮ መፍትሄ በማግኘት አምናለሁ።  አንዳንድ ጊዜ ደግሞ አንዳንድ የእንግሊዘኛ ቃላትን ሳይተረጉሙ እንዳሉ መጠቀሙ ከውዥንብር ሊያድን ይችላል። አማርኛውንም ደካማ ያደርገዋል ብዬ አላስብም። ምክንያቱም እንደ እንግሊዘኛው አግባብ ባለው ቦታ ላይ መተጣጠፍ መቻላቸውን እስካሁን አላየሁም። የትኞቹ ቃላት እንደሆኑ ወደ ክለሳው ስንመለስ እነማን እንደሆኑ ይቀርባሉ።

የወርድፕሬስ ትርጎማ ጥራቱን በተመለከተ ለምሳሌ 100 እጅ ትርጉም አካባቢ ሲደርስ እንደገና ቢያንስ ሁለት ጊዜ ለመከለስ አስቤአለሁ። ከገጽ አንድ ጀምሮ እስከ መጨረሻው ድረስ። ልክ አልፋና ቤታ እንደሚሉት ሊሆን ነው ማለት ነው። ክለሳወቹ ላይ አልፎ አልፎ እርዳታ መጠየቄ አይቀርም። የምጠይቀውም ትንሽ ትንሽ ቆንጠር እየደረኩ ስለሚሆን ሁሉም ጥያቄወች በጊዜው መልስ እንዲያገኙ እድሉ ይሰፋል። ሁላችንም ስንካፈልና ስናርመው  ውጤቱ የተሻለ ይሆናል ብየ አስባለሁ። ምናልባት ባለፈው ጊዜ አብዝቼ ይሆናል። እኔም ምናልባት ለማብራራት ብዬ ብዙ ከምጽፍ ባጭሩ "ለሁሉም ጥያቄወች መልስ አልተሰጠም" ማለት መቻሌን አሁን ትዝ አለኝ። ለወደፊቱ ባጭሩ እጽፋለሁ።   //ፋተ

tegegne tefera

unread,
Nov 15, 2014, 3:45:53 AM11/15/14
to linux-e...@googlegroups.com
ሰላም ፋንታው
መጀመሪያ ለለጥፍካቸው ጥያቄዎች መልስ የሰጠሁ መስሎኝ ነበር። የቻልኳቸውን። ቀጥሎ የለጠፍካቸውን እያየሁ ነው።
ትንሽ የጊዜ እጥረት እያወዛገበኝ ስለሆነ ነው። በርግጥ እንዳልከው የተነሱ ጥያቄዎች፣ መሰራት ያለባቸው ስራዎች፣
መልክቶች ስር ይገቡና ተወሽቀው ይቀራሉ። ሁሉንም ስራ ባንድ ጊዜ መስራት መቼም አይቻልም። ባለበት ሁኔታ
ከተተወም ጥሩ አይደለም። ስለዚህ የሚያስፈልገው የሆነ ስርዓት ማበጀት ያለብን ይመስለኛል።

እዮብ
መወያያት መልካም ነገር ነው። ስራህ ከትርጉም ጋር የተገናኘ መሆኑን አላውቅም ነበር። ስራችንን የበለጠ
የሚያቀላጥፍ ነገር ካንተ ብጠብቅ ኣልሆነ ጫና ማድረግ እንዳይመስልብኝ። እውነቴን ነው ግን ረፍት ነው የተሰማኝ።
ብዙ የሚገርም ሞያ ያላቸው ግን ያደፈጡ ሰዎች እንዳሉ ይሰማኛል።

ተገኝ
እመለሳለሁ

Fantaw Tesema

unread,
Nov 15, 2014, 5:19:59 AM11/15/14
to linux-e...@googlegroups.com
እሺ፤ አመሰግናለሁ ተገኝ።
የሆነ ስርዓትም ማበጀት ካለብን ያን እናደርጋለን። እስከዛ ድረስ ግን ለጊዜውና ለሚቀጥሉት ዙሮች ትንሽ ትንሽ እልካለሁ።
መልካም ቀን!
እዮብ፤
ባለፈው ለላከው ተያያዥ አመሰግናለሁ። ፒዲኤፍ ወደ ኤክሰል የሚቀይር እየፈለኩ በትክክል የሚሰራ እስካሁን አላገኘሁም። ፒዲኤፉን ወደ ፊደል ከቀየሩ በኋላ እንደገና ወደ ኤክሰል ኢምፖርት ባደርግም በደንብ አልሰራም። ይህን ማድረግ የፈለኩት ተያያዡ ላይ ብዙ ነገሮች ስላሉ በፊት የተተረጎመው ሳይነካ ከጎኑ አንድ አምድ አክሎ እዛ ላይ አንዳንድ ማረሚያ ትርጉም እንድናስገባበት አስቤ ነበር። የዚህን ሰነድ ኤክሰል ስሪት የት ማግኘት ይቻላል? //ፋተ

Fantaw Tesema

unread,
Nov 15, 2014, 5:01:08 PM11/15/14
to linux-e...@googlegroups.com
Hello,

Have managed to convert the attached pdf glossary to excel on http://online2pdf.com/. 50 pages per time. I am confident this is allowed to convert and edit the glossary. //FT

tegegne tefera

unread,
Nov 16, 2014, 9:59:31 AM11/16/14
to linux-e...@googlegroups.com
While we are at it, do you think it is possible to update the glossary
on .am.wiktionary.org and create an entry there too. It is one project
that could be tremendous help for any student.
Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages