Playlist

2 views
Skip to first unread message

Fantaw Tesema

unread,
Oct 30, 2015, 6:06:59 AM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com
ሰላም!

Playlist  ን በአማርኛ ምን ትሉታላችሁ? ተጨዋች ዝርዝር ማለት እንግዳ ያደርገዋል? //ፋተ

Eyob Fitwi

unread,
Oct 30, 2015, 6:13:26 AM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com
ተጠግተሃል። እኛ አጫዋች ዝርዝር ነው የምንጠቀመው። እንደኔ ከሆነ ከፈለግክ የጨዋታ ዝርዝር በለው።


On 30/10/2015 01:06 ከሰዓት, Fantaw Tesema wrote:
ሰላም!

Playlist  ን በአማርኛ ምን ትሉታላችሁ? ተጨዋች ዝርዝር ማለት እንግዳ ያደርገዋል? //ፋተ
--
You received this message because you are subscribed to the Google Groups "Gnu/Linux Ethiopia" group.
To unsubscribe from this group and stop receiving emails from it, send an email to linux-ethiopi...@googlegroups.com.
For more options, visit https://groups.google.com/d/optout.

Fantaw Tesema

unread,
Oct 30, 2015, 7:03:32 AM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com
ህምምምም .....
እንደተረዳሁት Playlist ማለት ለምሳሌ ለመጫወት ዝግጁ/የተሰናዱ/የተመረጡ የሙዚቃ ወይም የቪዲዮ ዱካወች ሊሆኑ ይችላሉ። ሁለቱም "አጫዋች ዝርዝር" ወይም "የጨዋታ ዝርዝር"  Playlist ን በትክክል የሚገልጹ አይመስለኝም። በተለይ "አጫዋች ዝርዝር" ከተባለ ስለ አጫዋቹ እንጂ ስለሚጫወቱት ዝርዝሮች የሚገልጽ አይመስለኝም። 

እረጂም ይሆናል እንጂ ለምሳሌ "ለመጫወት የተዘጋጁ ዝርዝሮች" ወይም ተመሳሳይ ቢሆን የተሻለ ይመስለኛል። አሁን እኔ የምለው ተቀባይነት ያለው ከሆነ እነዚህን ሶስት ቃላት Playlist ን እንዲያጸባርቁ እንዴት አድርጎ ማሳጠር ይሻላል? //ፋተ

Fantaw Tesema

unread,
Oct 30, 2015, 7:07:10 AM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com

ይቅርታ! ከላይ "እንዴት አድርጎ ማሳጠር ይላል?" የሚለው
"እንዴት አድርጎ ማሳጠር ይላል?" ተብሎ ይነበብልኝ!!  //ፋተ

Eyob Fitwi

unread,
Oct 30, 2015, 7:07:51 AM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com
እንዳልከው ይረዝማል። ሐሳቡን ከሚወክለው ቃልነቱ ይልቅ ወደ የፍቺ ዝርዝር ያመዝናል። እኛ ደግሞ ሐሳቡን የሚወክልልን ቃል ነው የምንፈልገው። እኔ አልመክረውም።

አጫዋች ዝርዝር ላይ ያልከው ነገር እኔም በከፊል እስማማለሁ። የስራ ነገር ሆኖብኝ ነው እንጂ እኔም ብዙም አሳምኖኝ አይደለም የምጠቀምበት። የጨዋታ ዝርዝር ግን ምኑ ቅር አሰኘህ?

Fantaw Tesema

unread,
Oct 30, 2015, 7:14:08 AM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com

ልክ ነህ! "የጨዋታ ዝርዝር" መጥፎ አይደለም። እንዳው ወሰን ለመግፋትና የተሻለ ይኖራል ብየ ስለገመትኩ ነው! አመሰግናለሁ። //ፋተ

Belay Tekalign

unread,
Oct 30, 2015, 1:34:25 PM10/30/15
to Gnu/Linux Ethiopia
Eyob:
I guess you are about 25. Are you married. Don't answer it here. Can we talk. I want you to marry my niece. she is a civil engineer and beautiful
Belay

tegegne tefera

unread,
Oct 30, 2015, 4:14:25 PM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com
Belay. You are something.:-)


playlist "የጨዋታ ሰልፍ" "የጨዋታ ቅደም ተከተል" ቢሆን እመርጠው ነበር እኔ ብሆን።
ከዛ ስቤ ወደ "ጨዋሰልፍ" ወይም "ጨዋተከል" እወስደው ነበር እኔ ብሆን ኖሮ።
  

Fantaw Tesema

unread,
Oct 30, 2015, 4:46:53 PM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com
አመሰግናለሁ ተገኝ!

ይገርምሃል ዛሬ ብዙ አልቆየም እያሰብኩ ነበርና "የጨዋታ ተራ" የሚለው መጣልኝ።
"የጨዋታ ሰልፍ" ም ቆንጆ ነው። ለነገሩ ሰለፍም ሆነ ተራ መጠበቅ ይመሳሰላል። 
ለማንኛውም ምን ይመስልሃል? ምክንያቱም   List =  ተራ። በፊት ግን List = ዝርዝር ተብሎ ተተርጉሞ ነበር። //ፋተ

tegegne tefera

unread,
Oct 30, 2015, 7:13:44 PM10/30/15
to linux-e...@googlegroups.com
ተራ እንደውም የተሻለ ይመስላል። እስቲ እዮብ አንድ በልበት።  ዝም ብለን እየፈጠርን የባሰ ግራ የሚያጋባ እንዳይሆን ነው እንጂ "ተራ" እንደውም የተሻለ ነው። 
ለማንኛውም ተቀባይነት የማግኘት እድል አለው ወይ ነው? 

እዮብ እኛ ስትል ማንን ማለትህ ነው። ስራ ቦታ ነው? የትኛውን መዝገበ ቃላት ነው የምትጠቀሙት። 

Belay Tekalign

unread,
Oct 30, 2015, 8:16:48 PM10/30/15
to Gnu/Linux Ethiopia
እየውላችላችሁ ይህ የቁውንቃ ፈጠራ ነገር አልተመችኝም ። 90 ሚሊዮን ሕዝብ ነው ያለው አገራችን ። ማን  ነን እኛ ። ለምን ጊዚያችንን እራሳችን አናሻልልበትም ። ለምሳሌ ፋንታው ወርድ ፕሬስ በማስተዋወቅ አንተ ደግሞ ተገኔ በሙያህ ። 

Fantaw Tesema

unread,
Oct 31, 2015, 4:48:09 AM10/31/15
to linux-e...@googlegroups.com
ሰላም!
የጥንቶቹ አባትና እናቶቻችን ቋንቋውን ፈጥረውታል። አሁን እኛ ቋንቋ እየፈጠርን ሳይሆን የተፈጠረውን እንደት አድርገን በትክክል ትርጉሙ ላይ መጠቀም እንደምንችል ነው እየተነጋገርን ያለነው። 
ጨዋታም ሆነ ተራ፣ ሰልፍ ወዘተ ከዚህ በፊት ተፈጥረው አልቀዋል። ሌሎቹም ቃላት እንደዚሁ። አሁን ስንተረጉም ተገቢውን የአማርኛ ቃል መርጠን መውሰድና መጠቀም ብቻ ነው እኔ እንደተረዳሁት። ትክክለኛውን ትርጉም ለማግኘት ደግሞ መነጋገር ያስፈልገዋል። አማርኛ ቋንቋ ውብ፣ ተጣጣፊና ሁለገብ ነው። ማወቅ፣ መማርና፣ ማሰብ ግን ያስፈልገዋል። አንድንድ ጊዜ You have not met them ለማለት "አላገኘሃቸውም" ወይም "አላገኘሻቸውም" ወይም "አላገኛችኋቸውም" ? ወዘተ እንላለን። አንዳንድ ጊዜ ብዙውን ባጭሩ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ትንሹን ረዘም አድርገን እናጠቃለዋለን። ሲተረጎምም ያንን ይከተላል። ገንቢ አስተያየት ከሰጠን፣ ያለንን ፈልገን ካገኘን በኋላ ትርጉሙ ላይ ከተጠቀምንበት ጥሩ ውጤት ላይ እንደርሳለን። //ፋተ   

tegegne tefera

unread,
Oct 31, 2015, 6:51:44 AM10/31/15
to linux-e...@googlegroups.com
በላይ
አልከራከርም። በሃሳብ እየተጫወትኩ ነበር እንጂ! 

Eyob Fitwi

unread,
Oct 31, 2015, 12:34:55 PM10/31/15
to linux-e...@googlegroups.com
ተራ፣ ሰልፍ፣ ወረፋ... እኔ አልቃወማቸውም። እንዲያውም በአማርኛው ካየነው ይበልጥ ወደ ሐሳቡ ሳይጠጉ አይቀሩም። እንግዲህ የትኛው ነው ተጠቃሚዎቻችን ይበልጥ የሚያዝላቸው የሚለውን አስተውለን መምረጥ ነው።

ተገኔ፦ ማለቴ ጉግልን ወደ አማርኛ ከሚተረጉሙት ቡድኖች ውስጥ አለሁበት። አንዳንዴም የማይክሮሶፍት ይመጣልኛል።

በላይ፦ አሄሄ፣ እኔስ ለነገሩ አርጅቻለሁ፣ 32።  :-)

ልክ ብለሃል፣ በእርግጥም ቋንቋውንና የትርጉም ሂደቱን በፈላጭ ቆራጭነት እንዳንመራው መጠንቀቅ አለብን። እየተመካከርን እና እያስተዋለን መሆን አለበት። በተለይ በዚህ ረገድ ገና ብዙ መገንባት ያለ ልምድ እና ክህሎት ስላለ አሁን ከመቸውም በላይ ስራችንን በጥንቃቄ መስራት አለብን። እኔም ስለው የነበረው ይሄ ነው፣ በኢሜይል ልውውጣችንንም እንደምታየው እያደረግን ያለነውም ይሄ ነው። በስፋትና ያለችግር እየተሰራባቸው ያሉ ትርጉሞች ካሉ አሳማኝ ምክንያት ከሌለ በስተቀር ማፈንገጥ አያስፈልግም። ነገር ግን የአይሲቲ ቃላት ትርጉም ኃላፊነቱን ወስጃለሁ የሚል የመንግስት መስሪያ ቤት C++ን «ሐ++» ብሎ ሲተረጉመው ምን ታደርገዋለህ? እኔ ከልምድ እንዳየሁት ከግል ይልቅ በቡድን ሆኖ ሲሰራ (አንዱ እየተረጎመ፣ ሌላ እየገመገመ፣ እንዲሁም አስተያየት የሚሰጡ ወዘተ.) ይበልጥ ውጤታማ ይሆናል።

ከሠላምታ ጋር፣
እዮብ

Fantaw Tesema

unread,
Nov 2, 2015, 2:33:12 PM11/2/15
to linux-e...@googlegroups.com

ሰላም!
በበኩሌ ተራ ን መርጫለሁ። ተጠቃሚወች ምን አንደሚመርጡ መገመት አስቸጋሪ ነው።
መልካም ምሽት ለሁላችሁም!! //ፋተ

Fantaw Tesema

unread,
Nov 3, 2015, 1:36:59 PM11/3/15
to linux-e...@googlegroups.com
Playlist = "የጨዋታ ተራ" የሚለውን እኔ መርጫለሁ። የተለየ አስተያየት ካላችሁ በሁለት ቀናት ውስጥ ብትነግሩኝ ቆንጆ ነው። መልካም ምሽት። //ፋተ

Eyob Fitwi

unread,
Nov 4, 2015, 1:21:34 AM11/4/15
to linux-e...@googlegroups.com
I'm not against it. Let's see how it looks like in the released version.

Fantaw Tesema

unread,
Nov 4, 2015, 3:36:11 AM11/4/15
to linux-e...@googlegroups.com

OK, thanks. BR //FT
Reply all
Reply to author
Forward
0 new messages